የወያኔ ውድቀት፣ የወያኔን ማስፈራርያ ውድቅ በማድረግ የትግራይ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች አማራ ክልል እየተጓዙ ነው!!!!
Posted: 21 Oct 2019, 17:10
በቅድሚያ የትህነግ አሉባልታና የጥላቻ ዘመቻን አሽቀንጥራችሁ በመጣል ወደ ጅግናውና በኢትዮጵያዊነቱ በማይደራደረው ከወንድሙ ከትግራይ ህዝብ ጋር በደምና በአጥንት ወደ ተጋመደው ወደ ጀግናው የአማራ ህዝብ ይህንን ቆራጥ ውሳኔ ወስናችሁ ለሄዳችሁ ጀግኖች የትግራይ ወጣቶች ይህንን ዜና ስሰማ ምን ያህል እንደ ኮራሁባችሁ እኔና ፈጣሪ ነው የምናውቀው። የተከበርከውም የአማራ ህዝብም እጅህን ዘርግተህ ስለተቀበልካቸው ባህል ሆኖ አመሰግናለሁ ልበል እንጂ ልጆቹ የሄዱት የራሳቸው አገርና የሚኮሩበት ህዝብ ነው ስለዚህ ገና ወደፊትም ትህነግ የዘረጋውን የመለያየት ግድግዳ ደረማምሰን በድል የምንኖርበት ዘመን ሩቅ አይሆንም።

