Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

አብይ ዛሬ ቦንብ አፈንድቶ ከመድረክ ወርዷል!!!

Post by Hameddibewoyane » 19 Oct 2019, 14:39

አሁን ነውኮ ገና የአብይን የዛ ንግግር ማየው ጎበዝ! ሰውዬው ዛሬ ድምፅ የሌለው ቦንብ እኮ ነው የጣለው። በተለይ ህውሃት ላይ ጓ ብሏል። የአይዲዮሎጂዎቻቸውን አፍላቂዎች ሞግቷል! በላይፍ ስታየላቸው ተሳልቋል። የመደመር ፍልስፍናን ከኦዳ ዛፍ ላይ ቀድቶ ተንትኗል። ንግግሩን ላልሰማችሁ አለፍ አለፍ እያልኩ ያለውን ልፃፍላችሁ ..

አብይ በአጭር ደቂቃ ንግግሩ እነስታሊንና ካርል ማርክስን ሞግቷል።
«በዚህ ዘመን የሚኖር ሰው ኮምፒውተር እንኳ አይቶ የማያውቀው ሌኒን ከ 101 አመት በፊት ከፃፈው ሃሳብ ጋር እንዴት ተቸንክሮ ይቀራል? ብሎ ተሳልቋል። ፕላቶ የተባለው ፈላስፋ “ሰው ጤነኛ መሆን አለበት ምክኒያቱም ጤነኛ ካልሆነ ሊያመርት አይችልም” የሚለው ፍልስፍና ሰውን ከሰውነት አውርዶ ወደሮቦትነት የሚቀይር ደካማ ፍልስፍና ነው ብሎ ተችቶታል።

አብይ የመደመርን ፍልስፍና ከ “ኦዳ” ዛፍ ጋር አስተሳስሮ ተንትኖታል። (እዚህ ጋር አንድ ኦሮሞ ጓደኛዬ የኦሮሞን ፖለቲካ ኦዳ ዛፍ ስር ፈልገው ያለችኝ ትዝ አለኝ)

አብይ ቀጥሏል ባሻዬ ... ረገጥ አርጎ እንዲህ አለ ...
«አማራ ሲጠቃ የማይደነግጥ ኦሮሞ፣ ኦሮሞ ሲጠቃ የማይደነግጥ አማራ፣ ትግሬ ሲጠቃ የማይደነግጥ አማራ እንዴት ሊኖር ይችላል?» ብሎ ጠይቋል!

«ከዚህ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን የማይችል ሱማሌ፣ መሪ መሆን የማይችል አፋር ኢትዮጵያ ውስጥ አይኖርም» ብሎ የውህደቱን እውንነት አስረግጧል። (ይሄ ለአጋር ፓርቲዎች ትልቅ የምስራች ነው)

አብይ የመደመር ተቺዎቹን «እስቲ መጀመሪያ መፅሃፉን አንብቡትና ሞግቱን። ሳታነቡ ብትተቹት እሱን ብትጥሉ እሱን አትጥሉት እናንተም አታድጉም» ብሎ መክሯል። ለጥቆም እንዲህ አለ ...

«አልደመርም የሚሉ ሰዎች በብቸኝነት ከመዳከር ውጪ የሚያመጡት ነገር የለም» ብሎ በአጭር ቃል አርድቷቸዋል።
«ከተዋሃድን እንጠፋፋለን የሚሉ ሰዎች አሉ። በመጀመሪያ ደረጃ በሃሳብ መሟገት እያለ መጠፋፋትን ምን አመጣው?» ብሏቸዋል።
«ዛሬ እንጠፋፋለን የሚሉ ሰዎችም የኔ ሃሳብ ካልሆነ ብለው መድረቅ የለመዱ የነማርክስን የድሮ ፖለቲካ የሚያራምዱ ባረጀ ፍልስፍና የተጠመቁ ሰዎች ናቸው» ብሎ ይወርፋቸዋል።

ቀጥሎም መቀሌ ለተቀመጡት ሰዎች በሚመስል መልኩ ጠንከር አርጎ መልእክት እንዲህ በማለት አስተላልፏል ....

«ጀግና ሰው ውስኪውን አስቀምጦ ማባዛት የሚል ሃሳብ ይዞ መምጣት ነው። በአዲሳባና በአውሮፓ በዘመዶቻቸው ስም ፎቅ ገንብተው መብላት የናፈቀውን ህዝብ አስብልሀለሁ ማለት ስላቅ ነው። በ5 ሺ ደሞዝ ካመት እስካመት ሆቴል ተቀምጠው (ምንጩን እግዜር ይወቀው) ዳቦ ለራበው ህዝብ እንደሚጨነቅ መምሰል በህዝብ መቀለድ ነው። በተሰጠው እድል መጠቀም ሲያቅተው በጀነሬሽን እድል መቀለድ ነውር ነው» ብሏቸዋል!

አብይ ስለኖቤል ሽልማቱም ጓደኛዬ አለኝ ብሎ የተናገራት ነገር ኢንተረስቲንግ ነች።
«አንተ ኖቤሉ አንዴ ተሰጥቶሃል ኢትዮጵያውያን ግን ካላወቁበት ይወሰድባቸዋል» ብሎኛል ብሏል። አስከትሎም
«እኔ ከበሻሻ የወጣሁ የደሃ ልጅ ነኝ። ሽልማቱ የኔ አይደለም የኢትዮጵያውያን እንጂ። ይልቅ ቁጭ ብሎ ሽልማቱን ቁጭ ብሎ ከማጣጣልና ለሽልማቱ ከመዝፈን ውጡ። ይልቅ በቅርቡ ኢትዮጵያ የህዋ ላይ ሳተላይት ታመጥቃለች» ብሎ ሰበር መረጃ ተናግሯል። አቦ ይቅናው!!

በመጨረሻም አብይ እንዲህ በማለት ንግግሩን ደምድሟል ....!

«አብይና ኢትዮጵያ ኢትዮጵያና አብይ የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። ዛሬም በድጋሜ ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው ኢትዮጵያ ትበለፅጋለች። ታድጋለች። ይሄን የማይፈልጉ ይጠፋሉ እንጂ ኢትዮጵያ አትጠፋም!

ሰላም ሰላም የምንለው ጦርነትን ስለምንፈራ ሳይሆን ሰላምን አብዝተን ስለምንወድ ነው!! ሬሳ አንቆጥርም እንጂ ከወንድም የኤርትራ ህዝብ ጋር ተጣልተን ያጠፋነው ህይወት እንኳ ታሪካዊ ቁስል ነው!

በተደጋጋሚ ፈጣሪ ስንል ሰዎች ይገረማሉ እኛ በማርክስና ሌኒን ፍልስፍና ስላልታወርን በፈጣሪ እናምናለን! በዚህም አናፍርም! 98 ፐርሰንት በፈጣሪ የሚያምን ህዝብ ይዞ በፈጣሪ አለማመን የሚመሩትን ህዝብ አለማወቅ ነውና!»

ብሎ ከመድረኩ ወርዷል!! አብዬ እግዜር ይጠብቅህ!!


Fiyameta
Senior Member
Posts: 19847
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: አብይ ዛሬ ቦንብ አፈንድቶ ከመድረክ ወርዷል!!!

Post by Fiyameta » 19 Oct 2019, 15:24

መደመር - Synergy (in English)
  • Syn·er·gy
    /ˈsinərjē/
    Definition:
    The cooperation of two or more organizations to produce a combined effect greater than the sum of their separate effects.


PM Abiy is a genius. Unfortunately, a genius is never understood in its own time. But he is undoubtedly one of God's greatest gifts to the Ethiopian people.

Post Reply