መደመር ወይስ መደርመስ ????
Posted: 19 Oct 2019, 10:07
በኢህአዴግ ፅ/ቤት መግለጫ ከተፃፉት ማደናገርያ ነጥቦች
1. የሚመሰረተው ውሁድ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ ነው
2. የምንከተለው የፌደራል ስርዓት ነው
3. ህወሓት አምኖበታል በሃዋሳ ጉባኤ ፀድቋል ወዘተ በሚል የቀረቡ ነጥቦች ሁሉም ውሸት ናቸው
፩- ውሁድ ብሎ ህብረ ብሄራዊ የሚባል ነገር የለም ከተወሃደ
ብሄር የሚል ይጠፋና ሰው በግሉ ነው አባል የሚሆነው፣ ስለ ብሄር የሚል ጉዳይ አይነሳም፣ ብሄር አይወክልም ልክ እንደ ኢሰፓ፣ ልክ እንደ ኢዜማ•• የብሄር ውክልና የለውም ከሌለው ደግሞ ህብረ ብሄራዊ የሚባል ውሸት ነው
፪- የምንከተለው የፌደራል ስርዓት ነው የተባለውም ማደናገርያ ነው ምክንያቱም ውህደት ከተፈፀመ መንግስትን የሚመራ ድርጅት ነው ያው ድርጅቱ ደግሞ ተዋህዷል ብሄር የሚባል የለውም። ስለዚህ ክልሎች ሊኖሩ ይችላሉ ብለን እንኳ ብናስብ ሊመራቸው የሚመደብላቸውና የሚያስተዳድራቸው ከውሁዱ ፓርቲ ነው፣ ምደባው በህዝብ ወይ በብሄር ይሁንታ ሳይሆን ከላይ ነው ልክ እንደ ደርግ አሃዳዊ ስርዓት ስለሆነም ውሁድ ብሎ ፌደራዊ ስርዓት አይኖርም ማደናበርያ ነው እየቀረበ ያለው።
፫-ሀዋሳ ላይ በነበረ ጉባኤ አንደኛ ይጠና ተጠንቶ ለጉባኤ ይቅርብና እንወያይበት ነው የተባለው እንጂ እንወሃድ ያለ ድርጅት የለም ህወሓትም አላለም ፣ሁለተኛ ጥናቱ የተካሄደው ድርጅቶቹ ተቀራርቦና እየተደማመጡ ሲሰሩ ነበሩ በሚባልበት ጊዜ ነው ሆኖም ውጤቱ የሚያሳየው የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት የለም ነው የሚለው የዚህ መፍትሄ ደግሞ ውህደት ሊሆን አይችልም ፣ ጥናቱ የተካሄደው ለውጥ ከሚባለው በሁዋላ ቢሆን ደግሞ ምን ውጤት ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ግልፅ ነው።