
-
Hameddibewoyane
- Member
- Posts: 3890
- Joined: 25 Sep 2019, 02:42
በትግራይ በግፍ የተገደሉት ታላላቅ የአገር ባለአባቶች ተጋሩ!
"በትግራይ በግፍ የተገደሉት ታላላቅ የአገር ባለአባቶች ተጋሩ ብዙ ናቸው።በተለይ መሳፍንቶች ናችሁ ተብለው የተረሸኑ በግፍ ተሰቃይተው ከሚገደሉበት የእንደርታ አከባቢ ይበዛል ከነዚህ ውስጥም አንዱ ፊተውራሪ ብፁዕ ናቸው።ፊተውራሪ ብፁዕ በጣም ሐብታም በአከባቢያቸው ተሰሚነት የነበራቸው ታላቅ ሰው ነበሩ የተቸገረ በመርዳትም ይታወቃሉ። ህወሓት ወደ አከባቢያቸው ሲመጣ የህወሓት ደጋፊ ቢሆኑም አንድ የህወሓት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረ ለትግራይ አባቶች በነበረው ጥላቻ ፊተውራሪ ብፁዕ" እቤትዎ ያለችውን ሰራተኛ ደምዎዝ አይከፍሉም" በማለት ከሰሳቸው። በዚህ ሳያበቃ ከህወሓት ጋር ደርግን ለመታገል የገባውን ልጃቸውንም ሄዶ "አባትህ የሰራተኛ ደምዎዝ አይከፍሉም በዝባዥ ነው" እያለ ሁሌ ወላጅ አባቱን ያጣጥልበታል ልጃቸው ትእግስቱ አለቀ። የፊተውራሪ ብፁዕ ልጅም "አባቴን የማያከብር ድርጅት በከንቱ ነው የምታገለው ብሎ ይህንን የአከባቢው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አመቺ ሰአትና ጊዜ ጠብቆ በማታ ገድሎት ከአከባቢው በመሰወር ለደርግ ሄዶ እጁን ሰጠ። ከእዛም የህወሓት ኃላፊዎች" ልጅዎን ያምጡት"ሲባሉ "ከአቅሜ በላይ ነው እናንተ ጋር ነው ሲታገል የነበረው ደርግ ያለበት ቦታ መሄድ አልችልም" ብለው መለሱ። በመጨረሻም ስብሐት ነጋ "ለዚህ ፊተውራሪ ጥይት አታባክኑ በገመድ አንቃችሁ በገደል ውስጥ ጣሉት" ብሎ ትእዛዝ አስተላለፈ በትእዛዙም መሰረት ፊተውራሪ ብፁዕ ታንቀው በገመድ ተጣሉ።ይህንን ታሪክ ማወቅ ለሚፈልግ ሰው ትግራይ ሳምረ በመሄድ የአከባቢው ሰው ሆነ ቤተሰቦቻቸውን መጠየቅ ይቻላል"

