Page 1 of 1

መደመር፣ የአብሮ መስራት ቲኦሪ ! መደመር ሰይፍ ነው ! መለኪያው ምንድን ነው? አቢይ እንደ ምኒልክ ወይስ እንደ ከማል አታቱርክ ?

Posted: 15 Oct 2019, 13:33
by Horus
ሲ ን እ ር ጂ ማለት አብሮ መስራት፣ ቱ ወርክ ቶጌዘር ማለት ነው ! በቃ ! ቃሉ ግሪክ ቢሆንም እጅግ የጥንት ኢትዮጵያ ቃል ነው። ስራ ማለት ነው። በባህልም በታሪክም ደቦ፣ ጅጊ፣ ዎጀ፣ ዉሳቻ፣ ሌላ በመላ ኢትዮጵያ ሚሰራበት የህበረት አሰራር ባህል ና ክህሎት ነው።

ጸንሰ ሃሳቡን የምወደው የቃሉ እምብርት ስራ ወይም ኤርጎን (ወርክ) ስለሆነ ነው። እኔ ብዙ ግዜ እንዳልኩት አንዱ ትልቁ የዘመናችን ኢዮጵያዊ እሴት መሆን ያለበት በስራ ክቡርነት ማመን ነው። መደመር የአብሮ መስራት ፍልስፍና እና ካልቸር ሆኖ መተርጎሙ አሜን የሚያሰኝ ነው።

አንድ አገር ወደ ስልጣኔ ሚሄደው በስራ ክቡረት ፍልስፍና ሲመራ ብቻ ነው።

አሁን ትልቁ የምሁራን ተግባር ይህ የመደመር ሃሳብ ወይም ሲ ነ ር ጂ፤
ፍልስፍናዊ ይዘቱን መተንተንና ማየት፣
ንድፈ ሃሳቡ ምን እንደ ሆነ በታትኖ ማየትና ማጥራት፣
ክህሎታዊ ወይም እስትራተጂው (ሜትዶሎጂው) ምን እንደ ሆነ ጸሃይ ላይ ማውጣትና
መደመር በተግባር ሲገለጽ ምን አይነት ውጤትና ፋይዳ እንደ ሚወልድ ማሳየት አለባቸው ።

ቁም ነገሩ የጽንሱ ዝርዝር ይዘት ላይ ነው። ማለትም
በፖለቲካ፣
ኢኮኖሚ፣
ሶሺያል፣
ካልቸር፣
ዲፕሎማሲ፣
ሚሊታሪ ፣
ወዘተ መስኮች መዘርዘር ማለት ነው

ግ ን የፍልስፍናው እምብርት ስራ መሆኑ እጅግ ትክክል እና ፋና ወጊ ነው !

ሰዎች የመደመር ፍልስፍናም እንበለው ፕሮግራምን ለመመዘን እንዴት ይችላሉ? ምን አይነት መለኪያ መጠቀም ይችላሉ?

አንዱና ብቸኛው መለኪያ የኢትዮጵያ አጀንዳ ነው ። የሚጠይቁት ቀጥተኛ ጥያቄ ፤ ይህ ፕሮግራም የኢትዮጵያን አጀንዳ ከግብ ያደርሳልን የሚለው ነው ። አጀንዳው የሚከተሉትን 4 ግቦች አሉት ።

አንድ፣ የኢትዮጵያን አንድነት፣ መረጋጋት እና ጥንካሬ እውን ማደርግ ፤

ሁለት፣ ዴሞክራሳዊ፣ ነጻ እና ፍትሃዊ ህብረተሰብ እውን ማደረግ፤

ሶስት፣ ኢትዮጵያዊያንን የበለጸጉ፣ የተማሩ እና ጤናማ ሕዝብ ማድረግ ፤

አራት፣ በኢትዮጵያ የሚፈጥር፣ ከባቢ ሚጠብቅ እና መንፈሳዊ ካልችር መገንባት ናቸው ።

መደመር እነዚህን አላማዎች ካነገበ ፍጹም ተደጋፊና ስኬታማ ሃሳብ ይሆናል ፣ መለኪያውን የህው ነው ።

Re: መደመር፣ የአብሮ መስራት ቲኦሪ ! ያቢይ መጽሃፍ ወጣ

Posted: 15 Oct 2019, 14:07
by Horus
እንደ ሚታየው መደመር የሚያስበው ስለ አንድነት ነው። ይህ አንድነት አንድ መቆሚያ ጽኑ መሰረት ፣ ጽኑ ኢትዮጵያዊ እምነት ወይም ካልቸር እንዲኖረው ግድ ነው ። በኔ ግምት ይህ መሰረት በአራት የመሰረት ድንጋዮች ላይ ይቆማል ።

አንደኛ፣ በአንድ ፍጣሪ ማመን ነው፣ ኢትዮጵያዊያን በሃይማኖት ቢለያዩም ማለት ነው ።

ሁለተኛ ፣ በግለሰብ ፍጹም ልዕልና ማመን ነው ፣ ከፈጣሪ ቀጥሎ ያለው ክቡር ነገር ሰው ነው፣ አንድ ግለሰብ ። ይህ ግለሰብ ነው ያገርም፣ የስራትም መሰረት ።

ሶስተኛ ፣ በስራ ክቡርነት ማመን፣ ለዚህ ነው ሲ ን እ ር ጂ የሚስማማኝ ።

አራተኛ ፣ በኢትዮጵያዊያን ሁሉ ወንድማማችነት ማመን ነው ።

እነዚህ ናቸው መቆሚያ እሴት የሚባሉት፣ ያንድ ኢትዮጵያዊ ካልቸር መስረቶች ።

Re: መደመር፣ የአብሮ መስራት ቲኦሪ ! ያቢይ መጽሃፍ ወጣ

Posted: 15 Oct 2019, 14:12
by Ethoash
ስራ ፈት ጉራጌ ስራ አገኘ አሁን ይህንን መፅሐፍ ይዞ ሱቅ በደርቴ አዛ ሊያረጉን ነው በየትራፊክ መብራቱ ላይ።

Re: መደመር፣ የአብሮ መስራት ቲኦሪ ! ያቢይ መጽሃፍ ወጣ

Posted: 15 Oct 2019, 14:32
by Horus
ሰዎች የመደመር ፍልስፍናም እንበለው ፕሮግራምን ለመመዘን እንዴት ይችላሉ? ምን አይነት መለኪያ መጠቀም ይችላሉ?

አንዱና ብቸኛው መለኪያ የኢትዮጵያ አጀንዳ ነው ። የሚጠይቁት ቀጥተኛ ጥያቄ ፤ ይህ ፕሮግራም የኢትዮጵያን አጀንዳ ከግብ ያደርሳልን የሚለው ነው ። አጀንዳው የሚከተሉትን 4 ግቦች አሉት ።

አንድ፣ የኢትዮጵያን አንድነት፣ መረጋጋት እና ጥንካሬ እውን ማደርግ ፤

ሁለት፣ ዴሞክራሳዊ፣ ነጻ እና ፍትሃዊ ህብረተሰብ እውን ማደረግ፤

ሶስት፣ ኢትዮጵያዊያንን የበለጸጉ፣ የተማሩ እና ጤናማ ሕዝብ ማድረግ ፤

አራት፣ በኢትዮጵያ የሚፈጥር፣ ከባቢ ሚጠብቅ እና መንፈሳዊ ካልችር መገንባት ናቸው ።

መደመር እነዚህን አላማዎች ካነገበ ፍጹም ተደጋፊና ስኬታማ ሃሳብ ይሆናል ፣ መለኪያውን የህው ነው ።

Re: መደመር፣ የአብሮ መስራት ቲኦሪ ! መለኪያው ምንድን ነው?

Posted: 15 Oct 2019, 23:20
by Horus

Re: መደመር፣ የአብሮ መስራት ቲኦሪ ! መለኪያው ምንድን ነው?

Posted: 16 Oct 2019, 01:27
by Horus
የመደመር ግንዶች ሰላም፣ ይቅርታ፣ ፍቅር ወይም ሰይፍ !! ይህ አስፈሪ ነው ። ይህም ማለት ወይ በሰላም፣ ይቅርታና ፍቅር አንድ መሆን እንችላለን ። ይህን እምቢ ካሉ ግን በሰይፍ በሃይል አንድ እንድንሆን ይሆናል ። ስለዚህ አቢይ ግልጽ ነው። ኢትዮጵያ በሰላም ይቅርታ ፍቅር አንድ ልትሆን ትችላለች ። ይህ ካልሆነ በሰይፍ አንድ ትሆናለች ። ትክክል ነው !!!

Re: መደመር፣ የአብሮ መስራት ቲኦሪ ! መደመር ሰይፍ ነው ! መለኪያው ምንድን ነው? አቢይ እንደ ምኒልክ ወይስ እንደ ከማል አታቱርክ ?

Posted: 16 Oct 2019, 02:34
by Horus

Re: መደመር፣ የአብሮ መስራት ቲኦሪ ! መደመር ሰይፍ ነው ! መለኪያው ምንድን ነው? አቢይ እንደ ምኒልክ ወይስ እንደ ከማል አታቱርክ ?

Posted: 21 Mar 2023, 11:24
by eden
wey gud

Re: መደመር፣ የአብሮ መስራት ቲኦሪ ! መደመር ሰይፍ ነው ! መለኪያው ምንድን ነው? አቢይ እንደ ምኒልክ ወይስ እንደ ከማል አታቱርክ ?

Posted: 21 Mar 2023, 12:46
by Horus
ኤደን፣
በጣም አመሰግናለሁ ! ይህን እኔ መለጠፌንም ረስቼዋለሁ ። ይህ ነው ሆረስ ማለት! በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ እንደ ብርሃን የጸዳ መርህ፣ ንድፍና አመለካከት ያለኝ ፍጡር ነኝ ! ይህን ስጽፍ የዛሬ 3 አመት ተኩል አቢይ እንኳ መደመር ከማለት ያለፈ ምን ማለቱ እንደ ሆነ አያውቅም ነበር ። ዛሬም ምን ማለቱእንደ ሆነ አያውቅም !

Re: መደመር፣ የአብሮ መስራት ቲኦሪ ! መለኪያው ምንድን ነው?

Posted: 24 Jul 2023, 14:48
by eden
Horus wrote:
16 Oct 2019, 01:27
የመደመር ግንዶች ሰላም፣ ይቅርታ፣ ፍቅር ወይም ሰይፍ !! ይህ አስፈሪ ነው ። ይህም ማለት ወይ በሰላም፣ ይቅርታና ፍቅር አንድ መሆን እንችላለን ። ይህን እምቢ ካሉ ግን በሰይፍ በሃይል አንድ እንድንሆን ይሆናል ። ስለዚህ አቢይ ግልጽ ነው። ኢትዮጵያ በሰላም ይቅርታ ፍቅር አንድ ልትሆን ትችላለች ። ይህ ካልሆነ በሰይፍ አንድ ትሆናለች ። ትክክል ነው !!!
wey gud

Re: መደመር፣ የአብሮ መስራት ቲኦሪ ! መደመር ሰይፍ ነው ! መለኪያው ምንድን ነው? አቢይ እንደ ምኒልክ ወይስ እንደ ከማል አታቱርክ ?

Posted: 24 Jul 2023, 15:08
by Horus
ኤድን ደግሜ ላመስግንህ!!!

የዛሬ 4 አመት ስለ መደምር ሆነ ስለ ከማል አታቱርክ ያልኩት ይህ ነው ። ዛሬ አቢይ እንኳን አታቱርክ ፈስ አለሆነም የወረሙማ ፓርክ ማኔጀር ነው ! እኔ ዝንፍ አልልም!

"ሰዎች የመደመር ፍልስፍናም እንበለው ፕሮግራምን ለመመዘን እንዴት ይችላሉ? ምን አይነት መለኪያ መጠቀም ይችላሉ?

አንዱና ብቸኛው መለኪያ የኢትዮጵያ አጀንዳ ነው ። የሚጠይቁት ቀጥተኛ ጥያቄ ፤ ይህ ፕሮግራም የኢትዮጵያን አጀንዳ ከግብ ያደርሳልን የሚለው ነው ። አጀንዳው የሚከተሉትን 4 ግቦች አሉት ።

አንድ፣ የኢትዮጵያን አንድነት፣ መረጋጋት እና ጥንካሬ እውን ማደርግ ፤

ሁለት፣ ዴሞክራሳዊ፣ ነጻ እና ፍትሃዊ ህብረተሰብ እውን ማደረግ፤

ሶስት፣ ኢትዮጵያዊያንን የበለጸጉ፣ የተማሩ እና ጤናማ ሕዝብ ማድረግ ፤

አራት፣ በኢትዮጵያ የሚፈጥር፣ ከባቢ ሚጠብቅ እና መንፈሳዊ ካልችር መገንባት ናቸው ።

መደመር እነዚህን አላማዎች ካነገበ ፍጹም ተደጋፊና ስኬታማ ሃሳብ ይሆናል ፣ መለኪያውን የህው ነው ።"

Re: መደመር፣ የአብሮ መስራት ቲኦሪ ! ያቢይ መጽሃፍ ወጣ

Posted: 24 Jul 2023, 21:39
by Selam/
+R.I.P.+

ነፍስህን ይማረው!

Ethoash wrote:
15 Oct 2019, 14:12
ስራ ፈት ጉራጌ ስራ አገኘ አሁን ይህንን መፅሐፍ ይዞ ሱቅ በደርቴ አዛ ሊያረጉን ነው በየትራፊክ መብራቱ ላይ።

Re: መደመር፣ የአብሮ መስራት ቲኦሪ ! መደመር ሰይፍ ነው ! መለኪያው ምንድን ነው? አቢይ እንደ ምኒልክ ወይስ እንደ ከማል አታቱርክ ?

Posted: 06 Nov 2024, 04:18
by Selam/
Again RIP to Ethoash! ጭልፊቱ to follow suit!

Re: መደመር፣ የአብሮ መስራት ቲኦሪ ! መደመር ሰይፍ ነው ! መለኪያው ምንድን ነው? አቢይ እንደ ምኒልክ ወይስ እንደ ከማል አታቱርክ ?

Posted: 06 Nov 2024, 14:25
by Horus
የዛሬ 5 አመት የጻፍኩት ይህ ነበር!
ዛሬም ደግሜ እጽፈዋለሁ ! ሃሳብ ያለው ፣ አቋም ያለው እንደዚህ ነጻ ሃሳቡን የሚገልጸው!!!

"Horus » 15 Oct 2019, 13:33