Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by Horus » 11 Oct 2019, 00:36

አንደኛ፣ የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ትክክለኛ ስም እና አጻጻፍ ምኒልክ ነው እንጂ ሚኒሊክ ወይም ምልሊክ ወይም ምንልክ ወዘተ አይደለም ።

ሁልተኛ፣ አንድነት ፓርክ ፈጽሞ ጥሩ ስም አይደለም። አንደኛ ፓርክ ማለት የእንሰሶች መሰብሰቢያና የዱር አራዊት የሚታይበት ማለት ነው። ቃሉ ከዚያ የመጣ ብቻ ሳይሆን ራሱ ቃሉ የተውሶ ነው። አንድ ክቡር የኢትዮጵያ ምልክት ቦታ በተውሶ መጥራት ያሳፍራል ። ላቢይም ቢሆን አለው አለውና ሳይመታው ቀረ እንዳይሆን ከዛሬ ጀምሮ ፓርክ የሚለው ቃል አንጠቀም ።

ሶስተኛ ፣ ፕሬዚዳንቷ እንዳሉት ይህ ቦታ ታላቅ ሆኖ የኢትዮጵያ ገዢዎች ማእከል የሆነው በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ስራና ምክኛት ነው ። ለማንም ፍትሃዊ ሰው ግልጽ እንደ ሚሆነው ይህ ቦታ ምንም ሆነ ምን የሚጠራው እና መሰየም ያለበት መጀመሪያ በፈጠረው ሰው ስም ነው ። ያም ሰው አጼ ምኒልክ ይባላል።

ስለሆነም ይህ አዲስ ያንድነት ፓርክ ትክክለኛ ስሙ
ምኒልክ መስክ ነው፣ መሆንም አለበት፣ የአለም ቱሪስቶችም የሚሳቡት ምኒልክ መስክ ቢባል ነው።

አዲስ አበቤ ከዛሬ ጀምሮ ምኒልክ መስክ እንጂ ሌላ ቃል አትጠቀሙ


Horus
Senior Member+
Posts: 39924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by Horus » 11 Oct 2019, 02:03


Horus
Senior Member+
Posts: 39924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by Horus » 11 Oct 2019, 12:56

ፕረዘንት፣

ይህ ደሞ አይቀርም። ልብ በል፣ ተዲ አፍሮ ጥቁር ሰው ከማለቱ በፊት ምኒልክ የተረሳ ቃል ነበር ። አሁን አቢይ ለታሪክ ሆነ ለቱሪዝም ባመጠአው ሃስብ በየቀኑ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ምኒልክን ያነሳሉ ። የሚቀጥለው ደሞ ስለ ፍትህ ነው ። ይህ ፓርክ ማን ጀመረው? ምኒልክ ነው !! በእኛ እድሜ ምኒልክ መስክ ተብሎ ይጠራል ። ይህ አሁን ያለው የዘር ግርግር ባ10 አመት ውስጥ ይሞታል ። ዘመናዊ ኢኮኖሚና ትምህርት ነው የዘር ፖለቲካን የሚገድል !

EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by EPRDF » 11 Oct 2019, 20:51

መስክ ማለት ለጥ ያለ ሳርማ ሜዳ ነው። ፓርክ ትክክለኛ የኣማርኛ ትርጉሙ መናፈሻ ነው፣ ስለዚህ ተብሎ መጠራት የነበረበት አንድነት መናፈሻ ነበር።

Horus
Senior Member+
Posts: 39924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by Horus » 11 Oct 2019, 22:04

እኔ መስክ። መናፈሻ ወይም ሌላ የተሻለ ኢትዮፒክ ቃል ግድ የለኝም ። ግ ን ይህን የዘመናዊ ኢትዮጵያ ማእከል ፓርክ ብሎ በፈረንጅ ተውሶ መሰየም ነውር ነው ።

ቦታው ግን መናፈሻ ብቻ አይደለም ። በመሰረቱ ወመዘክር (ቤተ መዘክር) ነው፣ ከሁሉም ነገር በላይ ማለት ነው። ሌላ ይዘቱ የሕዝብ መናሀሪያ ወይም መናፈሻ ወይ መሰባሰቢያ መስክ መሆኑ ነው ። ለምሳሌ ብሄር ብሂረ ሰቦች ተይንት ስብስብ ወዘተ ።

እንግዲህ ሁሉንም ታሳቢ ብናደርግ ቤተ ዝክር ወይም ቤተ መዘክር ዋነኛ ሃሳቡ መሰለኝ ። ስለምን ቢሉ ያሉት ነገሮች ታሪኮች ቅርሶች ሁሉ በአንድነት ማሳያ ቦታ ስለሆነ ፣ እጽዋቶቹም ቢሆን እንደ ቦታኒካል ሙዚየም ነው ሚታዩት ። ብቻ ቁልፍ ቃሉ መዝክርነቱ ነው ።

አቢይ የአንድ መዘክር ሊለው ይችላል። የቦታ ስራ ግን መናፈሻ ጋርደን አይደለም ፣ የቅርስ ስብስብ ማሳያ ጋለሪ እንበለው መዘክር ጽንሱ ያለው እዚያ ስለሆነ መስክ ማለት ይሁሉም ነገር መታያ ቦታ ማለት ነው እንበል

መቼም ዛሬ አቢይ ምኒልክ መስክ ሆነ ምኒልክ መዘክር ወይም ምኒልክ ቤተ ቅርስ አይለውም፣ እነ ጃዋር ስለሚነሱበት። ኢትዮጵያዊያን ግ ን በምኒልክ ይሰይሙታል።

እንዲያውም ዝም ተብሎ ምኒልክ ቤተ መንግስት መባል ነው የነበረበት ።

Horus
Senior Member+
Posts: 39924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by Horus » 12 Oct 2019, 01:29


EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by EPRDF » 12 Oct 2019, 17:09

Horus wrote:
11 Oct 2019, 22:04
እኔ መስክ። መናፈሻ ወይም ሌላ የተሻለ ኢትዮፒክ ቃል ግድ የለኝም ። ግ ን ይህን የዘመናዊ ኢትዮጵያ ማእከል ፓርክ ብሎ በፈረንጅ ተውሶ መሰየም ነውር ነው ።

ቦታው ግን መናፈሻ ብቻ አይደለም ። በመሰረቱ ወመዘክር (ቤተ መዘክር) ነው፣ ከሁሉም ነገር በላይ ማለት ነው። ሌላ ይዘቱ የሕዝብ መናሀሪያ ወይም መናፈሻ ወይ መሰባሰቢያ መስክ መሆኑ ነው ። ለምሳሌ ብሄር ብሂረ ሰቦች ተይንት ስብስብ ወዘተ ።

እንግዲህ ሁሉንም ታሳቢ ብናደርግ ቤተ ዝክር ወይም ቤተ መዘክር ዋነኛ ሃሳቡ መሰለኝ ። ስለምን ቢሉ ያሉት ነገሮች ታሪኮች ቅርሶች ሁሉ በአንድነት ማሳያ ቦታ ስለሆነ ፣ እጽዋቶቹም ቢሆን እንደ ቦታኒካል ሙዚየም ነው ሚታዩት ። ብቻ ቁልፍ ቃሉ መዝክርነቱ ነው ።

አቢይ የአንድ መዘክር ሊለው ይችላል። የቦታ ስራ ግን መናፈሻ ጋርደን አይደለም ፣ የቅርስ ስብስብ ማሳያ ጋለሪ እንበለው መዘክር ጽንሱ ያለው እዚያ ስለሆነ መስክ ማለት ይሁሉም ነገር መታያ ቦታ ማለት ነው እንበል

መቼም ዛሬ አቢይ ምኒልክ መስክ ሆነ ምኒልክ መዘክር ወይም ምኒልክ ቤተ ቅርስ አይለውም፣ እነ ጃዋር ስለሚነሱበት። ኢትዮጵያዊያን ግ ን በምኒልክ ይሰይሙታል።

እንዲያውም ዝም ተብሎ ምኒልክ ቤተ መንግስት መባል ነው የነበረበት ።
I don’t like this wajo Horus guy, and I never liked to agree with him. However, I have to confess my agreement on this particular issue for the sake of the perspective I have on our history.

ታሪክ ስንል ያለፈ፣ የሞተ፣ ያከተመ ፣ ያለቀና የደቀቀ ማንም ኃይል ሊቀይረው የማይችለው ክስተት ነው፣ ስለዚህ ታሪክን ሳንደላልዝ፣ ሳናስውብ፣ ጥላሸትም ሳንቀባ ታሪክን እንደታሪክነቱ እንዳለ እንደወረደ መጠበቅ፣ መንከባክብና ለቀጣዩ ትውልድ ማሳለፍ ቅዱስ ተግባር ይመስለኛል። የዚህ ትዉልድ አሁን የሰመጠበት መከራና አባዜም ዋነኛው ምክንያት ከቀደምት ታሪካችን እንደተለመደው፣ የመንገዶችን፣ የሰፈሮችን፣ የመንደሮችንና የከተሞችን ስም መቀየርና በሌላ የመተካት እኩይ ተግባር ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው። ይህንን ስንል አሁንም በመጪው ጉዞዋችን፣ካለፈው ተምረን ዳግም እንዳንሳሳት መጠንቀቅ ይሻል።

ስለዚህ አሁን ለማለት የፈልግኩት፣ አዲስ አበባ ፊንፊኔ የሚለውን የዘመኑ የፖለቲካ መድረክ ተዋንያን ክርክር ወደ ጎን ትተን፣ አሁንም ትኩረታችንን ታሪክና ክስተቱ ላይ እናሳርፍ።
እንግዲህ አሁን በታሪክ ይህ ስፍራ የምንይልክ ቤተ መንግስት ተብሎ ነው የሚታወቀው። መጀመሪያ የቆረቆረውም፣ የሰፈረበትና የኖረበትም ይሀው ምንይልክ ነበር። ስለዚህ ይህ ምንይልክ፣ በዘመኑ አጠፋም አለማም፣ ይህ ስፍራ ወደድንም ጠላንም የእርሱ የታሪክ ቅርስ ነው፣ ስለዚህ ይህንን አንድነት ፓርክ ሚል ስያሜ የተሰጠው ቦታ፣ በታሪካዊው መጠሪያ ስሙ የምንይልክ ቤተ መንግስት መናፈሻ፣ የባህልና ቅርስ መዘክረ ማዕከል ተብሎ ቢሰየም አማራጭ አልነበረውም።

በተጎዋዳኝ በእንግሊዝኛም ተጎኑ:
Palace Menilik
Recreation and center for Ethiopian cultural and historical legacy. something like that.

Naga Tuma
Member+
Posts: 6786
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by Naga Tuma » 14 Oct 2019, 15:39

ሆረስ፤

ባነሳሀዉ የሃገር እና የተዉሶ ቃላት ሀሳብ ላይ ኣስተያየቴ ተጨማሪ ከሆነ የሃገር ቃል መጠቀም ኣስፈላጊ ነዉ። እስማማሉሁ። እንዲሁም የቃላትን ጥልቅ ትርጉሞች ኣብሮ ማስተዋልም መልካም ነዉ። በዚህም እስማማለሁ።

እዚህ በርካታ ቃላት ተጠቅሰዋል፤ መስክ፣ ወመዘክር፣ ቤተ መንግስት፣ ማእከል፣ መናፈሻ። እኔ ያሰብኩት ሌላ ቃል ግቢ ነዉ። የምንይልክ ኣዳራሽ ስፍራ የምንይልክ ግቢ ውስጥ ነዉ። ሜዳ፣ ግቢ፣ እና ኣዳራሽ ደረጃ ኣላቸዉ።

ቦታዉን በጥልቀት የሚገልጸዉ ቃልም ወመዘክር ነዉ ባልከዉም እስማማለሁ። ግቢ የሚለዉም ቃል ያንን ሃሳብ በቀላሉ መግለጽ የሚችል ይምስለኛል። እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ቤተሰም በቀላሉ የሚረዳዉ ቃል ነዉ።

ለወደፊትም ለታሪካዊ ቦታ ስም ከማዉጣት በፊት የቃላትን ጥልቅ ትርጉሞች ማስተዋል ኣስፈላጊነት ይህ ምሳሌ ጥሩ ትምህርት ነዉ።

ሜዳ (field)፣ ለምሳሌ ጃንሜዳ፣ መጫወቻ ቦታ ነዉ።
መስክ (stage?) የጊዜያዊ (temporary) መገናኛ ቦታ የመስላኛል።
ግቢ (garden) ወመዘክርን በቀላሉ መግልጽ የሚችል ይመስለኛል።
መናፍሻ (leisure) መዝናኛ ቦታ ነው።
ማእክል (center) የስራ (official business) ቦታ ይመስላል።
ጋለሪ የአማርኛ ትርጉሙን ባላስታዉስም የተዉሰኑ ቁሳ ቁሶች ማሳያ ቦታ የመስላል።

ስለዚህ የቦታዉ ዓላማ ከታወቀ ለዛ ቦታ ተገቢ የሆነ ቃል መምረጥ ይቀላል።

የኣጼን ትክክለኛ ስም ኣጠራር ትግራይ ዉስጥ ምንይልክ ፩ኛዉ እንዴት ይጠሩ እንደነበረ በማወቅ ያንኑ ስም ለኣጼ ምንይልክ ፪ኘዉ መጠቀም ያምያስፈልግ ይመስላኛል።

ኬር።

Horus
Senior Member+
Posts: 39924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by Horus » 14 Oct 2019, 22:00

Naga Tuma

እንዴት ሰነበትክ?
እኔ በፓርኩ ስም ላይ ያለኝ ሁለት ነገር ብቻ ነው ። አንዱ የዚህ ሁሉ ነገር ወላጅ የሆነው ምኒልክ ስለሆነ የሱ ስም መኖሩ ፍጹም የታሪክም የሞራልም ግዴታ ነው ። ሁለተኛ ፓርክ የሚለው የተውሶ ባእድ ቃልን መተው ። ከተፈለገኮ ከመቶ ማያንሱ ኢትዮፒክ ስሞች ይኖሩናል። ስለሆነውም እንዳለክው ከቦታ አላማ ጋር ተስማሚ የኛ የሆነ ስም መስጠት ነው።

የምኒልክ ስም ግ ን በተመለከተ ከራሱ እና በቤተ ሰቡ በላይ እኛ ስለሱ ስም ማወቅ አንችልም።

የራሱ ልጅ ንግስተ ነገስታት ዘውዲቱ ያሳተመችው የራሱ የንጉሱ ታሪክ [ ታሪከ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በጸሃፊ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ፣]

ትክክለኛ ስም ያመጣሁት ከዚያ ነው ።

ይህ መጽሃፍ ዘውዲቱ እንዲጻፍ ያዘዘችው 1910 ነበር ። ግ ን ከህትመቱ በፊት እሷም አረፈችና ኋላ ታተመ ። ምንም የማይነካው ትክክልኝ ስም ምኒልክ ነው።

Masud
Member+
Posts: 8502
Joined: 18 Jun 2013, 09:06

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by Masud » 15 Oct 2019, 01:29

That place must be called "Holocust Memorial Place" to remember the persons killed and tortured at that place by Menelik, Hailesellassie, Mengistu and Meles. It is the place where the bloods of many individuals were split.

Naga Tuma
Member+
Posts: 6786
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by Naga Tuma » 15 Oct 2019, 17:29

ሆረስ፤

ደህና። ወሂም ነሪ?

ቤተሰቡ ስለ ፩ኛዉ ወይም ቀዳማዊ ሰምቶ ኣይዴለም ፪ኛዉ ወይም ዳግማዊ ያለዉ? ከሆነ ፩ኛዉ ምኒልክ ከተባለ ፪ኛዉም ምኒልክ መባል ተገቢ ነዉ። ፩ኛዉ ምንይልክ ከተባለ ፪ኛዉም ምንይልክ መባል ተገቢ ነዉ። ንግስተ ነገስታት ዘዉዲቱ እና ጸሃፈ ትዕዛዝ ገብረ ስላሴ ዳግማዊ ብለዉ የቀዳማዊዉ እና ዳግማዊዉ ኣጼዎች ስም አጻጻፍ ይለያዩ የሚሉ ኣይመስለኝም። የቀዳማዊዉ ትክክለኛ አጻጻፍ ኣንተ እንደምትለዉ ምኒልክ ከሆነ ሁሉም ተስማማ ማለት ነዉ። የ፩ኛዉን ትክክለኛ ስም አጻጻፍ ሎዉላንደሩ ህይማይንድ ኤደን ሊነግረን ይችላል።

Horus
Senior Member+
Posts: 39924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by Horus » 15 Oct 2019, 22:24

ኛጋ ቱማ

እኔ ቀዳማዊ ምኒልክ ስሙን እንዴት እንደ ጻፈ አላቅም ። ዳግማዊ ምኒልክ ግን ይህ ነው የናት አባቱ የንግስ ስሙ ፣ ያንን መለጥ አንችልም ።

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ
አጼ ምኒልክ 2ተኛው
እምዬ ምኒልክ
አጤ ምኒልክ
ምኒልክ

EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by EPRDF » 16 Oct 2019, 00:28

Horus wrote:
15 Oct 2019, 22:24
ኛጋ ቱማ

እኔ ቀዳማዊ ምኒልክ ስሙን እንዴት እንደ ጻፈ አላቅም ። ዳግማዊ ምኒልክ ግን ይህ ነው የናት አባቱ የንግስ ስሙ ፣ ያንን መለጥ አንችልም ።

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ
አጼ ምኒልክ 2ተኛው
እምዬ ምኒልክ
አጤ ምኒልክ
ምኒልክ
ዋጆ Horus,

ምኒልክ ብሎ የኣማርኛ ቃል የለም። ምንይልክ ደግሞ የኣንኮበር አማራ ነበር እና ስም ከወጣለት በአማርኛ ትርጉም ያለው ስም ነው የሚወጣለት፣ ያም ምንይልክ ነው።

ሌላው መላምት ያለው እንግዲህ ያው የአማራ/ትግሬ ነገሥታት አፈ ታሪክ ነው ያም፣ ምንይልክ ዳግማዊ ከሆነ፣ ሌላ እርሱን የቀደመ ምንይልክ አለ ማለት ነው፣ እርሱም በንግሥተ ሳባ ና ጠቢቡ ሰለሞን የተወለደው ቀዳማዊ ምንይልክ ነው። ስለ እርሱም ስም ከምን እንደመነጨ በአንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ አፈታሪክ ተንታኞች ሲተነተን እንደሚከተለው ያስቀምጡታል

በኒ= ዘር... መሊክ= ንጉስ....በኒመሊክ= የንጉስ ዘር። ወይንም ቢን=ልጅ... መሊክ=ንጉስ..ቢንመሊክ= የንጉስ ልጅ ለማለት ነው በእብራይስጥ ወይም በአረብኛ።

የአማርኛውን ቃል ምንይልክ፣ ወይንም የምድረ ፍልስጤምን ቃል ቢንመሊክ፣ ለመውሰድ እንግዲህ ዋጆ Horus ትገደዳለህ።

ከዚህ ውጭ ግን ምኒልክ ብሎ ቃል የለም ፣ ብታጠብቀውም ብታላላውም አራት ነጥብ.

Naga Tuma
Member+
Posts: 6786
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by Naga Tuma » 16 Oct 2019, 13:48

Horus wrote:
15 Oct 2019, 22:24
ኛጋ ቱማ

እኔ ቀዳማዊ ምኒልክ ስሙን እንዴት እንደ ጻፈ አላቅም ። ዳግማዊ ምኒልክ ግን ይህ ነው የናት አባቱ የንግስ ስሙ ፣ ያንን መለጥ አንችልም ።

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ
አጼ ምኒልክ 2ተኛው
እምዬ ምኒልክ
አጤ ምኒልክ
ምኒልክ
ሆረስ፥

ይህ ቀላል ሃሳብ እንዲህ ያስኮርፋል እንዴ? የእናሸንፋለን እና እናቸንፋለን ትክክለኛነት ክርክር ኣልሰለቸህም እንዴ ጃል (ጃሌ?)

የእኔ በጣም ቀላል ሃሳብ የእናሸንፋለን ወይም የእናቸንፋለን ቃል ትክክለኛነት ሳይሆን መጀመርያ እናሸንፋለን ካልክ ሁለተኛ ጊዜም እናቸንፋለን ሳይሆን እናሸንፋለን ማለት ያስፈልጋል ነዉ። በእንግሊዘኛ consistency የሚባለዉ ማለት ነዉ።

የኣጼዉ ቤተሰብ ስም ስያወጡ ኣጠገባቸዉ የነበርክ ኣይመስለኝም። ስለዚህ የኣንተ መረጃ ዋና ወይም ቀዳሚ ምንጭ (primary source) ሊሆን ኣይችልም። የኣማርኛ ቋንቋ ኣስተማሪዬ ኣጼዉን እግዝኣብሄር የላከዉን እግዝኣብሄር ምን ይልክ ብለዉ ስለኣሰቡ ነዉ ምንይልክ የሚለወ ስም የወጣዉ ብሎ ስያስተምር ሰምቻለሁ፣ በወጣትነት ዕድሟዬ። ያ ማለት ሙሉ ስማቸዉ እግዝኣብሄር ምንይልክ ነዉ። (EPRDFም ይህን ልብ በል።) ኣስተማሪዉም ዋና ወይም ቀዳሚ ምንጭ ኣይዴለም።

ስለዚህ ቀዳማዊዉ ስሙን እንዴት እንደጻፈ ኣለዉቅም የምትል ከሆነ የዳግማዊዉን ስም አጻጻፍ ትክክለኛንት እንዴት ትከራከራለህ?

Horus
Senior Member+
Posts: 39924
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by Horus » 16 Oct 2019, 14:11

ናጋ ቱማ

ኩርፊያኮ አይደለም። አንድ ነገር ፋክት ነው አይደለም ነው ። የቃሉ ስር ያንተ አስተማሪ በስመ ነጋ ያለው አይደለም ። እንግዲያው ይሀውልህ፤ ምኒልክ ፊሎሎጂውና እና ኤቲሞሎጂው ለሚያውቁ ሰለሞን ከሚለው ቃል ጋር አንድ ሲሆን ትርጉሙም አዋቂ መሪ (ዋይዝ ሩለር)፣ ብልህ መሪ ማለት ነው ። ይህን ሂስቶሪካል ሊንጉስቲክስ ጋ ወስደህ አሸንፈኝ። ሌላው ዝም ብለው በድምጽ መመሳሰል ትርጉም የሚፈጥሩ ቄሶች ሺ ናቸው ። ሰላም !

Naga Tuma
Member+
Posts: 6786
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ምኒልክ መስክ ተከፈተ !!

Post by Naga Tuma » 16 Oct 2019, 15:17

ሆረስ፥

እኔ ኣንተን ኣሸነፍኩ ከማለት በኣንተ ተሸነፍኩ ማለት ያስደስተኛል። ፋክት ስያሸንፍ ደግሞ የበለጠ ያስደስታል። ኬር!

Post Reply