ርዕሰ-አንቀፅ ፡ ኢሬቻ እና የጤና ጥቅሙ ! በክቡር ቶማስ ሐጎስ የቀረበ
Posted: 06 Oct 2019, 16:46
በዚህ ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ ኢሬቻን ለማክበር ተብሎ ቅቤ ያልተቀባ ዛፍ የለም:: እንዲያውም ጎጃሜዋ እጮኛዬ ወደ አገር ቤት ዓርብ ነበር የሸኘኋት እና አይሮፕላኑ ልክ የሱዳንን ድንበር አቋርጦ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ሲገባ ነው ቅቤ የሸተተኝ አለችኝ:: እንግዲህ በዚህ ሁሉ 35000 ሺ ጫማ ከፍታ የሚበር አይሮፕላን ውስጥ ሆኖ ቅቤን ማሽተት ከታቻለ ድምዳሜው አገሪቱ ውስጥ ምንም የቀረ ቅቤ እንደሌለ ነው:: ዓብይ አሕመድ የተከላቸው ችግኞች ሳይቀሩ ቅቤ ተቀብተዋል::በአጭሩ አዲስ አባባ በቅቤ ታጥናለች:: እና ቅቤ ጠፋ ማለት ክትፎ እና ቅባት ያላቸው ምግቦች ቀሩ ማለት ነው :: ይሄ ማለት ደግሞ የደም ግፊት፣የልብ ድካም እና stroke ታማሚ ቁጥር ይቀንሳል ማለት ነው::
