Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

ኢሕአዴግ ስሙን ከመቀየሩ በፊት ከስሕተቱ ይማር !!!

Post by MINILIK SALSAWI » 29 Sep 2019, 14:46

ኢሕአዴግ ስሙን ከመቀየሩ በፊት ከስሕተቱ ይማር !!! ( ምንሊክ ሳልሳዊ)

ከስም ለውጥ በፊት ስር ነቀል የመዋቅርና የፖሊሲ ለውጥ ሊጀመር ይገባል።ካሁን ቀደም እንዳልነው ኮማ ውስጥ ያለው አሮጌው ኢሕአዴግ ተቀብሮ አዲስ ኢሕአዴግ መወለድ አለበት። በየክልሉ የምናያቸው ችግሮች አባታቸው ኢሕአዴግ ነው ፤ ከየቦታው እየፈለቁ በሕዝብ መሓል ግጭት የሚፈጥሩት አባታቸው ኢሕአዴግ ነው ፣ በየሚዲያው የፖለቲካ ተላላፊ ወረርሽኝ የሚያሰራጩት አባታቸው ኢሕአዴግ ነው ፣ ሐገራችንን ለእርስ በርስ ጦርነት ለሃይማኖትና ለጎሳ ግጭት የሚዳርጉ ከባባድ አደጋዎችን እየፈጠሩ ያሉት በመንግስት ጉያ የተወሸቁት ሁከት ፈጣሪዎች፣ መዋቅሮችና ፖሊሲዎች አባታቸው ኢሕአዴግ ነው። ወዘተ .......

ያደፈው በሕዝብ ደምና ለቅሶ የጨቀየው ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ባለፉት አመታቶች በርካታ መንግስታዊ ወንጀሎችን ሰርቷል፤ አሁንም በተዝረከረከው መዋቅር የከፋ ሽብር በሕዝብ ላይ እያካሔደ ነው።ኢሕአዴግም ተዋኻደም አልተዋኻደም ፤ ኢሕአዴግ ኢሕአዴግ ነው። የስም ውሕደት ብቻውን ዋጋም የለውም ፤ በነብስም በስጋም ካልተቀየረ ለውጥም አያመጣም። ኦሕዴድም ብአዴንም ስማቸውን ቀይረዋል ግብራቸውን ግን አልቀየሩም።ሕወሓት ስሟንም ግብሯንም አልቀየረችም።ጥቂት አመራሮች ካልሆኑ በስተቀር ኢሕአዴግ እንደ ድርጅት ካለፉት ስሕተቶቹ ተምሮ አዲስ ነገር ለመፍጠር እየሰራ አይደለም።ባለህበት እርገጥ ሆኗል።

ኢሕአዴግ በተከፋፈሉ ኃይሎች ተከቧል።ለስልጣን ከቋመጡ ኋይሎች ጀምሮ እስከ ለውጥ ፈላጊ ኃይሎች ድረስ እየተራወጡ ድርጅቱን ኮማ ውስጥ አስገብተውታል። አጋር ድርጅቶችም ቢሆኑ ወደ አሸናፊው ኃይል ለመቀላቀል እንደፔንዱለም እየተወዛወዙ ነው።እነዚህን ኃይሎች ለመለየት ከፍተኛ ፍጭት ቢኖርም የደፈረሰው እንዲጠራ ያበጠው መፈንዳት አለበት ።

ኢሕአዴግን ለማመን ቢከብድም የመንግስት መራሹ አካል ገኖ በወጣበት መንገድ አዲስ ድርጅታዊ ኃይሉን አምቆ የያዘው አካል ወደፊት መግፋቱ የማይቀር ሀቅ ነው። ኢሕአዴግ ራሱን የብልጽግና ፓርቲ ቢለውም ባይለውም ስር ነቀል የርእዮተዐለም ፖሊሲና የመዋቅር ለውጥ እስካላደረገ ድረስ መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ ከማለት ውጪ ምንም ለውጥ የለውም።

ኢሕአዴግ ስሙን ከመቀየሩ በፊት ከስሕተቱ ይማር በዋነኛነት ከኢሕአዴግ የሚጠበቀው የሚከተለውን የጸረ ሕዝብ የዘረኝነት ፖሊሲውን በመቀየር ከላይ እስከታች ያለውን መዋቅሩን በአዲስ አሰራር ሲለውጥ ብቻ ነው። ካሁን ቀደም እንዳልነው አሮጌው ኢሕአዴግ ተቀብሮ አዲስ ኢሕአዴግ መወለድ አለበት። የስም መለወጥ ለወሬ ካልሆነ በቀር ፋይዳ ቢስ ነው። ከስሕተቱ የማይማር አንድም የሐገር ጠላት ሲልም ድንጋይ ብቻ ነው።( ምንሊክ ሳልሳዊ)

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: ኢሕአዴግ ስሙን ከመቀየሩ በፊት ከስሕተቱ ይማር !!!

Post by TGAA » 29 Sep 2019, 16:38

ሚንይልክ ሳልሳዊ ያስቀመጠው ላይ ምንም መጨመር የሚያስፈልገው ነገር የለም ፡፡ኢህአድግ ከፊቱ ያለው ምርጫ ሁለት፤ ነው እነዚህም ምርጫዎች አይናቸውን አፍጥጠው ከፊት ለፊት ቀርበዋል ፤ የነዚህ ጥያቄዎች መልስ የሚሹት ከሁለት የፖለቲካ አመለከከት ካላቸው ቡድኖች ነው ፡፡ በአንድ በኩል ያለፈውን 27 አምት ትርምስና አሁንም በየቀኑ ለእርስ በእርስ ጦርነት እየጋበዘን ያለው የወያኔ ስርአትና የወያኔን ስራ አብረው ካዋለዱት ጠባብ ብሄርተኛ የኦሮሞ ቡድኖች በአሁኑ ሰአት ተሰባስበው እየገፉ የሚገኝት የወያኔውን ስርአት እንዲቀጥል የሞት ሽረት ትግል የሚያካሄዱት ወገኖች ናቸው ፡፡ በሌላው በኩል የሀያ ሰባቱን አመት የበሰበስ የጥፋት ስርአት ዲሞክራሲና ፍትህ ላይ የተመሰረተ የሁሉንም ኢትዮጵያዊናን መብትና ስብእናን ያከበረ ዜግነት መብቶችን በህግ ያስከበረ ስርአት ለመመስረት የሚታገሉ ወገኖች ስብስብ ወገን ነው፡፡ በአሁኑ ሰአት በወያኔና በአያቶላ ጀዋር የሚመራው ወገን ያንን የዘረኛ ስርአት በኋይል ህዝቡ ላይ ለማስፈር የተቀነባበረ ሴራና እርምጃ እየወሰዱ ይገኛል ፤ እስካሁን ጠንከር ያለ የአቋም መግለጫ እንኳን መውሰድ ያቃተው ወገን የራሱን አቋም እንኳን ወስዶ ለመከለከል የሚወስዳቸው እርምጃዎች በቅጡ አይደለም ፤ የጸረ ኢትዮጵያዊያን ቡድን ከግብጽ እንዲሁም ከተለያየ አቅጣጫ የገንዘብና የሞራል እርዳታ እየተደረገለት የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው ፡፡ የዲሞክራሲና የፍትህ ቡድኑ የአብይ እንዲጠናከር አስፈላጊውን ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ አለበት ፤ የሀገሪቱን አንድነትም በሚመለከት አቋም መውሰድ አለበት ፤ መግለጫም ማውጣት አለበት ያ እርምጃ ነው የዲሞክራሲና የፍትህ ካምፑን ሊያጠናከር የሚችለው፡፡ ልክ እንደማንኛውም የረጅም እሩጫ በሁለት ሯጮች መሃከል እርቀቱ በጣም እየረዘመ ሲመጣ ያንን ማካካስና እሩጫውን ማሸነፍ የማይቻልበት ደረጃ ይደረሳል ፡፡ ይህንን እውነታ ተገንዝቦ ተመጣጣኝ የሆኑ ህዝቡን የሚያረጋጉና ሁሉም ነገር በቁጥጥር ስር መሆኑን የሚያሳይ ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊና ወቅታዊ ነው፡፡

Post Reply