የአማራ ክልል በጥባጮችን አስጠነቀቀ! የትኛውንም ለመመከት አቅሙ አለን ብሏል! ምናልባትም ወያኔን የሚመለከት ይመስለኛል:::
የአማራ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር : በአማራ ክልል ሰሞኑን በጎንደር በጭልጋ የተፈጠረው ቀውስ : በጥባጮች የፈጠሩት በመሆኑ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በማሳሰብ : አማራ የትኛውንም ለመመከት አቅሙ እንዳለው ገልዋል::
“የአማራ ክልል የጦር አውድማ ለማድረግ የሚጥሩ አካላት አይሳካላቸውም: ይህን ለማድረግ የመጡ ካሉም ለመከላከል ብቃቱ አለን::” ብሏል::
እንዲሁም “ ችግር እያደረሱ ባሉ አካላት ላይ ከማህበረሰቡ በመነጠል የማያዳግም ርምጃ እንይወሰዳል::” ብለዋል::
ምንጭ : amara mass media agency