Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Horus
Senior Member+
Posts: 39844
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ደመራ ማለት መደመር ማለት ነው

Post by Horus » 27 Sep 2019, 20:18

temawi,

መጀመሪያ ምነው ጠያቂዋ ልጅ ትንሽ አግሮችዋን ብትሸፍን ከአንድ ሊቀ ጳጳስ ጋር ፊት ለፊት ተቀምጣ? !!

ደመራ እና መደመር ብዙ አይራራቁም። ደመራ (ምጅር፣ ምጅራ) ቀጥታ ትርጉሙ ጅመራ፣ መጀመሪያ፣ ስር፣ መነሻ ፣ዘር ወዘተ ማለት ነው ። እሱን ከብርሃን መውጣት፣ ከጸሃይ መውጣት ጋር ተያይዞ ነው። ግን አንድ የተጀመረ፣ የተወለደ ነገር ስለሚያድግ፣ ማደግ ደግሞ መደመር ፣ መበልጸግ ስለሆነ ካህኑ ያለው በመሰረቱ ትክክል ነው ። ከደመራ ይልቅ ከመደመር ጋር ቀጥታ ትርጉም ያላቸው መስከረም ፣ መስቀል፣ ክረምት፣ ክርማን፣ አክራሚ፣ ወዘተ የሚሉት ቃላት ናቸው ። ሁሉም ከፍጠት፣ መልማት፣ ማደግ፣ ማበብ ጋር የተያያዙ ስለሆነ ያ ሁሉ የሚሆነው በመደመር፣ በመከመር፣ በመጨመር ነውና !!

Post Reply