Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

ቢዘገይም የአማራ ብሄርተኝነትም የማታ ማታ መከሰቱ አልቀረም፡

Post by Za-Ilmaknun » 27 Sep 2019, 14:23

በአማራ ክልል ያለው (በመረጃ እጥረት ምክንያት ከክልሉ ውጭ ባሉ ወገኖቹ ላይ የሚደርሰውን በደል ከተባራሪ ወሬ በቀር በተገቢው ሁኔታ ሳያውቅ የኖረው) የአማራ ህዝብ ከሆነበት በደል የተነሳ አዲሱ ወደሆነው የአማራ ማንነት ህብረት መሄዱ አይቀርም፡፡ ንዴት የሚቀናው የዘውግ ህብረት ደግሞ ከአማራ ህዝብ ብረት የማንገት ባህል ጋር ተዳምሮ አማራን ከረዥም ዝምታው ሊያነቃው ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ የአማራውን ነፍስ እንዳለው አካል መንቀሳቀስ የማይወደወን “ገድየ ቀበርኩ” ባዩን ህወሃትን ማስበርገጉ አይቀርም፡፡ስለዚህ ህወሃት የአማራውን መደራጀት በተለየ ትዕግስት ማጣት እንዲያየውና እየተከተለ እንዲያጠፋው አድርጓል፡፡ የፕሮፌሰር አስራትን ነፍስ በመብላት ያልተመለሰው የመአድ እና የህወሃት ግብግብ ለዚህ ሁነኛ ምስክር ነው፡፡ መአድ የተደረገበትን ያህል ኦብኮ/ኦፌኮ ያሉ ሌሎች የዘውግ ፓርቲዎች ገና ዳዴ ከማለታቸው የህወሃትን መራራ በቀል አለመቅመሳቸው መአድ በልዩ ሁኔታ ይታይበት የነበረውን የህወሃት ክፉ አይን ለማወቅ ይረዳል፡፡

ንዴት የሚቀናው የዘውግ ህብረት ደግሞ ከአማራ ህዝብ ብረት የማንገት ባህል ጋር ተዳምሮ አማራን ከረዥም ዝምታው ሊያነቃው ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ የአማራውን ነፍስ እንዳለው አካል መንቀሳቀስ የማይወደወን “ገድየ ቀበርኩ” ባዩን ህወሃትን ማስበርገጉ አይቀርም፡፡ስለዚህ ህወሃት የአማራውን መደራጀት በተለየ ትዕግስት ማጣት እንዲያየውና እየተከተለ እንዲያጠፋው አድርጓል፡፡ የፕሮፌሰር አስራትን ነፍስ በመብላት ያልተመለሰው የመአድ እና የህወሃት ግብግብ ለዚህ ሁነኛ ምስክር ነው፡፡ መአድ የተደረገበትን ያህል ኦብኮ/ኦፌኮ ያሉ ሌሎች የዘውግ ፓርቲዎች ገና ዳዴ ከማለታቸው የህወሃትን መራራ በቀል አለመቅመሳቸው መአድ በልዩ ሁኔታ ይታይበት የነበረውን የህወሃት ክፉ አይን ለማወቅ ይረዳል፡፡

መአድ በህወሃት ክርን ተደቁሶ ወደ መኢአድ ከተቀየረበት ዘመን ጀምሮ እስከ ህወሃት ለመውደቅ ዘመም ዘመም ማለት ድረስ ባለው ረዥም ዘመን ከየአቅጣጫው እንደ እንጀራ ልጅ ለሚዋከበው የአማራ ህዝብ ጥብቅና የሚቆም ፓርቲም ሆነ ሌላ አይነት ድርጅት በሃገር ውስጥ አልነበረም፡፡ በዚህ ምክንያት አማራው ከአርባጉጉ በደኖ በኋላ ለተከሰተ መንግስት መራሽ ሁለተኛ ዙር ሞት እና መፈናቀል ተዳረገ፡፡ ይህ መንግስት መራሽ መፈናቀል በህወሃት መራሹ የአዲስ አበባው መንግስት ቀጭን ትዕዛዝ እንደ ሽፈራው ሽጉጤ እና ያረጋል አይሸሹም ባሉ ተላላኪ አሽከሮቻቸው አጋፋሪነት በጉራ ፈርዳ እና በቤኒሻንጉል የተከወነ ነበር፡፡ ህወሃት በአፉ በአልጠላውም የሚለውን የአማራ አርሶ አደር ከገጠር ሲያፈናቅል፣ እንደማይወደው በግልፅ የሚናገረውን የአማራ ምሁር እና የከተማ ልሂቅ ደግሞ ወደ እስርቤት እያጋዘ አስሮ ይገርፍ ነበር፡፡