Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39917
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጉራጌ ለምንድን ነው መስቀልን ለማክበር ይህን ሁሉ ጥረት የሚያደርገው? መስቀል የኬር በዓል ነው

Post by Horus » 27 Sep 2019, 03:02

መስቀል የኬር በዓል ነው

ኬር ምን ማለት ነው? ኬር እምነትም፣ ፍልስፍናም፣ ባህልም ነው። ለጉራጌ እግዚአብሄር ከሚለው ክቡር ቃል ቀጥሎ ያለው ክቡር ቃል ኬር ነው። ኬርነት የህይወት ፍልስፍና ብቻ ሳይሆን የመጨረሻው የሞራል እና የስነ ምግባር መሰረት ነው። መልካም ነገር ሁሉ፣ ሙሉ ነገር ሁሉ፣ ስኬታማ ተግባር ሁሉ መሰረቱ ኬርነት ነው።

መስቀል የኬር ክብረ በአል ነው። ሁሉም ነገር ሙሉ መሆኑን፣ ትክክል መሆኑን፣ ሰላም መሆኑን፣ ጤነኛ መሆኑን፣ ስኬታማ መሆኑን፣ ሰውም እንሰሳም እጽዋትም፣ አፈርም፣ አየርም፣ ዉሃም ፣ አለምም አለመጉደሉ፣ አለመበላሸቱ እና በደስታ፣ በእርካታ በደህንነት ላይ መሆኑ የሚገለጸው ኬር በሚባለው ነገርን ሁሉ መመልከቻ በሆነው ፍልስፍናና የባህርይ ስነ ምግባር መሰረት በሆነው በዚህ ጽንስ ነው።

ኬር ለጉራጌ ብቸኛው የካልቸሩ መሰረት ነው። ኬር ለጉራጌ አንድ ብቸኛ የኮስሞልጂው መጥሪያ ቃል ነው። ኬር ማለት ሁሉም መልካም ነገር ማለት ነው።

ባንድ ቃል፣ የጉራጌ መስቀል የኬር ክብረ በዓል ነው። ከዋና ዋና ይዘቶችሁ መካከል ከግማደ መስቀሉ መገኛ እስከ የመልካምነት በጎ ተግባር ያሉት የኬርነት አካላት ናቸው ። መስቀሉን ማሰብ፣ ምርቃት፣ ምስጋና፣ ያዲስ አመት ፌስታ (ጌሳት)፣ እርቅ፣ ፍቅር፣ እና ቸርነት ጥቂቱ የኬር መገለጫዎች ናቸ።

በመስቀል እለታት ፈጣሪ ይቀደሳል፣ ልጅ ይመረቃል፣ ወላጅ ይመሰገናል፣ አዲስ አመት ይባረካል፣ ቤት ንብረት ፍጥረት ሁሉ ይባረካል፣ ላለፈው አመት ስኬት ምስጋና ይሰጣል፣ የወደፊቱ አላማ እንዲሟላ አሚን ዬሁን ይባላል፣ ጠብ እርቅ ይሆናል፣ ወጣት ፍቅረኛውን/ዋን ታገኛል፣ የተቸገረ ይረዳል፣ ቤተሰብ አንድ ይሆናል፣ ማህበረሰብ ይተሳሰራል።

ይህ ረእስ ሙሉ መጽሃፍ የሚሻ ቢሆንም ባንድ ቃል ጉራጌ መስቀልን ሲያከብር ምንን አስቦ ነው ለሚለው አጭር መስሉ ይህ ነው ፤ ለጉራጌ መስቀል የኬር በዓሉ ነው ።

መስቀል እምነት ነው ። መስቀል ባህል ነው። ባህል ያንድ ማህበር አኗኗር ዘዴ ነው። ባህል ብልሃት ነው። ሰውም ሆነ ድርጅት ፣ አገርም ሆነ ጎሳ መድረሻ፣ አላማ፣ አጀንዳ፣ ፋዪዳ፣ ራእይ ወይም መሪ ብርሃን ከሌለው ሺ ግዜ ቢባክን፣ ቢንጫጫ ምንም ማለት አይደለም ።

ሺ ግዜ ቡድን ቢሰለፍ፣ ሺ ግዜ መንግስት ሰዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሊቆጣጠር ቢሞክር ሕዝብ ያሰበውን ያረጋል ወይም ያምጻል ። ግለሰብም እንደዚያ ነው። ሺ ግዜ ቡድቦች ግለሰቡን በዘር በጎሳ ምናምን ሊቆጣጠሩት ቢሞክሩ አይችሉም ።

አንድ ሰው የሚሰራውና የሚሳካው በባህሪው ልክ ነው። ባህሪ ያንድ ሰው ብልህነት ወይም ብህላታዊነት ማሳያው መለኪያው ነው። ባህል ያንድ ማህበር ብልህነት ማሳያው እና መለኪያው ነው። አንድ ህዝብ የሚሰራውና የሚለካው በባህሉ ልክ ነው ። ይህ ህግ ነው።

አዋቂ፣ የሚያድጉ፣ የሰከኑ፣ ተራማጅ፣ ምክን ያታዊ ፣ ግምታዊ ፣ ብልህ ፣ ሚዛናዊ ሕዝብ ራሱን የሚያገኘው በብርሃን እና በእውቀት ሳቢያ ነው። መስቀል ጥልቅ ነው ። መስቀል እምነት ብቻ ሳይሆን ፍልስፍና ነው። መስቀል እንደ ብርሃን መመሪያ ነው። መሪ ነው ።

ግን አላማ የሌለው ሰው፣ መድረሻው ምን እንደ ሆነ የማያቅ ሰው ፣ ወይም አጀንዳው ምን እንደ ሆነ የማያቅ ድርጅት የመስቀልን ትርጉም ሊያገኝ አይችልም። መስቀል አንድ ብሩህ አላማ ይዘው ያን አላማ ግብ ለማድረስ ሰው ለመርዳት፣ አገር ለማቆም በስራ ክቡርነት ላይ ቆመው ለሚተጉ እንደ ፋና እንደ ኮከብ የሚመራ ብርሃን የሚወጣበት ክቡር ቅዱስ ቀን ነው ።

ያ ደሞ ከክርስቶስ ቤዛነት ጋር አንድ ነው። ብርሃንና ብልሃት የሌለው ሰው መንጋ ነው ። ለምን እንደ ሚኖር፣ ለምን እንደ ሚሞት ማያቅ እንሰሳ ነው !!

ይህ ነው የመስቀል ትርጉም እንጂ ዝም ብሎ ጩሀትና ጭፈራ፣ ዝላይ አይደለም ። የኬር ዘመን ለኢትዮጵያ !!
Last edited by Horus on 28 Sep 2019, 01:25, edited 5 times in total.





Horus
Senior Member+
Posts: 39917
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ለምንድን ነው መስቀልን ለማክበር፣ መስቀልን ለማግነን ይህን ያክል ርቀት የሚጓዘው?!!

Post by Horus » 27 Sep 2019, 13:33

መስቀልን በማይዳሰስ ያለም ቅርጽነት በተመድ ቢመዘገብም በኢትይዮጵያዊያን ዘንድ ከእምነቱ ያለፈ ፍልስፍናዊ፣ ባህላዊ እና ማህበራዊ ምርምር አልተደረገበትም ። ይህ አሁን የሚለወጥ ይመስለኛል። የዚህን በአል ማህበራዊ ፋዪዳ በተመለከተ ከጉራጌ በላይ አግንኖ የሚያከብረው ስለሌለ በዚህ መስክ ሃላፊነት ያለባቸው እነሱ ናቸው ።

መስቀል ምንም እንኳ የተለያዩ ጎሳውዎች በተለያየ ስም ቢጠሩትም የብዙሃን (ማጆሪቲ) ኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልም እምነትም ነው ። ያከባበር አይነቱ እና ክብደቱ ከጎሳ ጎሳ ይለያያል እንጂ ። ዋና ዋና በመስቀል ውስጥ ያሉት ጽንሶች ለግዜ በስም እንጥቀሳቸው ።

አንድ ፣ የክርስቶስ ግማደ መስቀል መገኛ በዓል

ሁለት ፣ የዘመን ወይም የወቅት መለወጫ በዓል

ሶስት ፣ የምርቃት በዓል

አራት፣ የምስጋና በዓል

አምስት፡ የእርቅ በዓል

ስድስት፣ የፍቅር በዓል

ሰባት፣ የመልካምነት በዓል

ከሁለት እስከ ሰባት ካሉት እሴቶች ውስጥ ምርቃት እጅግ ከፍተኛው ነው። እርክ ወይም እክር የሚባለው የግብጽ ቃል ፍጥረት፣ ማደግ፣ መልማት፣ መብዛት ማለት ሲሆን ዛሬ መባረክ፣ ምርቃት፣ መጨመር፣ መበርከት እና ለሌሎች እጅግ ብዙ መንፈሳዊና ማህበራዊ ጽንሶች ስር ነው ። ለምሳሌ መደመር ማለት መመረቅ ማለት ነው። መርቅ ሲባል አክል፣ ጨምር ማለት ነው። ይህ ጽንሰ ሃሳብ ወደ ፊት ስለልማት፣ ስለእድገት፣ ስለብልጽኛ የሚፈላሰፉና የሚመራመሩ ምሁራን እንደ ሚያነሱት አምናለሁ ።

ይቀጥላል


Horus
Senior Member+
Posts: 39917
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ለምንድን ነው መስቀልን ለማክበር ይህን ሁሉ ጥረት የሚያደርገው? መስቀል የኬር በዓል ነው

Post by Horus » 28 Sep 2019, 00:29

ብዙ ግዜ የተንቢ ሲባል ትሰማላችሁ ። ቀጥታ ትርጉሙ እንኳን ደህና መጣህ፣ መጡ ማለት ሲሆን የተንቢ በሰባት ቤት፣ ዪምጣቢ በክስታኔ እያለ በሁሉም ጉራጌ ማህበረሰብ አንድ ትርጉም አለው ። የተንቢ፣ ዪምጣቢ በጥሬው በእኔ ላይ ይምጣ ማለት ሲሆን ጥልቅ ትርጉሙ እንደዚህ ያለ መልካም ዜና፣ አጋጣሚ በኔም ላይ ይምጣ ማለት መምትህ ትልቅ ደስታ ነው ማለት ነው ። በክስታኔ በላለዲ ዪምጣ ሲሉ በጥሪው በላዬ ላይ ይምጣ ማለታቸው ነው።

ጂበ ወይም ጅባ ምንጣፍ ማለት ነው
አንቀፎ ከቀንድ የሚሰራ ማንኪያ ነው። በትክክል ጉራጌ ክትፎ በእጁ አይበላም፤ በከንድ ማንኪያ ነው ሚበላ ።


Horus
Senior Member+
Posts: 39917
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ለምንድን ነው መስቀልን ለማክበር ይህን ሁሉ ጥረት የሚያደርገው? መስቀል የኬር በዓል ነው

Post by Horus » 28 Sep 2019, 00:57

በመሰረቱ ጉራጌ የሚፈጥረው እንጂ የሚቃወመው አንጃ ግራንጃ ብዙም የለውም ። የሱ ጥድፊያ ስራ፣ ፈጠራ፣ መሻሻል ፣ ነገሮችን መለወጥ ላይ ነው። ዛሬ በሁሉም መስክ ያለው ሩጫ ፈጠራና ብልጽ ግና ላይ ነው። ይህ ባህል ሽክታ፣ ሽከታ፣ ሽካ ፣ ነገሮችን ኣባልቶ ማሳመር መፍጠር መሸከት ይባላል ፣ ሽካ ችሎታ፣ ጥበብ፣ ሙያ፣ የስራ እውቀት ማለት ነው ። ይህ አንዱ ትልቁ የጉራጌ ካልቸር ነው ፤



Horus
Senior Member+
Posts: 39917
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ለምንድን ነው መስቀልን ለማክበር ይህን ሁሉ ጥረት የሚያደርገው? መስቀል የኬር በዓል ነው

Post by Horus » 28 Sep 2019, 02:28

አንድ ካልቸር መልካም ባህል ነው ከሚያሰኙት ነገሮች አንዱ በዚያ ካልቸር ውስጥ ያሉትን ሕዝቦች ማስደሰት መቻሉ ነው። ለያዙት ሕዝቦች ደስታ ሊፈጥር የማይችል ባህል መተው ያለበት እንጂ ከድሮ ስለ መጣ ብቻ መቀጠል የለበትም ። ኻልቸር አላማ አለው፣ አንዱ አልማ ሕዝቡን ተደሳች ማድረግ ነው !!!


Horus
Senior Member+
Posts: 39917
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ለምንድን ነው መስቀልን ለማክበር ይህን ሁሉ ጥረት የሚያደርገው? መስቀል የኬር በዓል ነው

Post by Horus » 28 Sep 2019, 02:51

ባዎረሩም መካም፣
ባላውረሩም መካም።
ተሰባቲ ሙካ አቲ ኢቲ ፈካም፣
የመካ ጉራኘ በኮነብከው ነገር፣
በክስታኔ አውርር፣
ባማርኛ ዘብር።

ይህ አባባል በሰባት ቤት መኖሩን አላቅም ነበር፤ ይገርማል !



Selam/
Senior Member
Posts: 16929
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ጉራጌ ለምንድን ነው መስቀልን ለማክበር ይህን ሁሉ ጥረት የሚያደርገው? መስቀል የኬር በዓል ነው

Post by Selam/ » 28 Sep 2019, 08:49

Translate please
Horus wrote:
28 Sep 2019, 02:51
ባዎረሩም መካም፣
ባላውረሩም መካም።
ተሰባቲ ሙካ አቲ ኢቲ ፈካም፣
የመካ ጉራኘ በኮነብከው ነገር፣
በክስታኔ አውርር፣
ባማርኛ ዘብር።

ይህ አባባል በሰባት ቤት መኖሩን አላቅም ነበር፤ ይገርማል !


Horus
Senior Member+
Posts: 39917
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ለምንድን ነው መስቀልን ለማክበር ይህን ሁሉ ጥረት የሚያደርገው? መስቀል የኬር በዓል ነው

Post by Horus » 28 Sep 2019, 13:13

Selam/ wrote:
28 Sep 2019, 08:49
Translate please
Horus wrote:
28 Sep 2019, 02:51
ባዎረሩም መካም፣
ባላውረሩም መካም።
ተሰባቲ ሙካ አቲ ኢቲ ፈካም፣
የመካ ጉራኘ በኮነብከው ነገር፣
በክስታኔ አውርር፣
ባማርኛ ዘብር።

ይህ አባባል በሰባት ቤት መኖሩን አላቅም ነበር፤ ይገርማል !

ሰላም መልካም መስቀል !
ዝም ብሎ ትርጉሙ እንዲህ ነው ።
ቢናገሩ ችግር፣
ዝም ቢሉ ችግር
ክሰባቱ ሙካ አንድ የት ደረሰ?
ነገር እንዲህ ሲሆንብህ
በጉርጌ ነግረህ
ባማርኛ መልስ

ሙካ እንደ ድንች ተቀቅሎ ምክክ ያለ የእስንሰት ስር ነው። የእሰት ስር አዉታ ይባላል ። ባልየው 7 ጉማጆች ቆራርጦ እንድታዘጋጅ ለሚስቱ ሰጥቶአታል። ግን ምግብ ሲቀርብ ያሉት 6 ሙካዎች ብቻ ናቸው ። አሁን ባል ይህን ነገር ልጠይቃት ወይስ ይቅር እያለ ከራሱ ጋር በሃሳቡ ሲያብላላ የተናገረው አባባል ነው ። እንዲህ ያለ አስቸጋሪ ነገር ሲያጋጥም በቋንቋ ጉራማይሌ ባግብዎ በቅኔ አለባብሶ እንደማለፍ ማለት ነው ።


Horus
Senior Member+
Posts: 39917
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ለምንድን ነው መስቀልን ለማክበር ይህን ሁሉ ጥረት የሚያደርገው? መስቀል የኬር በዓል ነው

Post by Horus » 28 Sep 2019, 20:25

ኬር ዪሁን የሚለውን የምርቃት መዝጊያ ረሱት እንጂ ቆንጆ ነው ባህላችህን ሕዝባችህን በሄደበት ሁሉ መቀጠሉ ድንቅ ነው !!


Horus
Senior Member+
Posts: 39917
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ለምንድን ነው መስቀልን ለማክበር ይህን ሁሉ ጥረት የሚያደርገው? መስቀል የኬር በዓል ነው

Post by Horus » 28 Sep 2019, 21:18

ይህን ለምምቴ የተሰኘ አስደናቂ እና ጥልቅ ፍልስፍና ተከታተሉ ። እጅግ ረቂቅ ጽንሰ ሃሳብ !!!


Horus
Senior Member+
Posts: 39917
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ለምንድን ነው መስቀልን ለማክበር ይህን ሁሉ ጥረት የሚያደርገው? መስቀል የኬር በዓል ነው

Post by Horus » 29 Sep 2019, 03:07

ትኩል ወይም ቅቅል ክትፎ እጅግ የማይጠገበው የክትፎ እና የስልስ ዘር ለመጀመሪያ ግዜ ለህዝብ በሚዲያ ሲነገር ሰማሁ !!


Horus
Senior Member+
Posts: 39917
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ ለምንድን ነው መስቀልን ለማክበር ይህን ሁሉ ጥረት የሚያደርገው? መስቀል የኬር በዓል ነው

Post by Horus » 29 Sep 2019, 03:52

በኢትዮጵያ መስቀል ሁለት ነገር ነው፣ አንዱ የግማደ መስቀሉ መታሰቢያ የመላ ኦርቶዶክስ በአል ነው። ሁለተኛው የምስቀል ካልቸር ነው ፣ይህ ደሞ በዋናነት ተወክሎ ያለው በጉራጌ ነው !! እጅግ ገናናዎቹ የጉራጌ ሸለቆችና ግዙፍ ተራራዎች እነ ዘቢደር እጹብ ድንቅ የእግዚአብሄር ምድር !!!!

Post Reply