Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

የወያኔን የሞተ ስርአትና እርዝራዦቹ ደንቃራዎችን ከኢትዮጵያ ትከሻ ላይ ማራገፍ

Post by TGAA » 24 Sep 2019, 19:48

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ብዙ ብሄረሰቦች ባሉበት ሀገር ፍትህን ዲሞክራሲን ለማምጣት ምንድነን የጋራ የሆነ ብሄራዊ ጥቅማችን ብሎ በማሰብ ሁሉንም እኩል የሆነ ተጣጥሮ የሚያድግበትን፤ እኩል የሆነ መስክ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ፡ ማንኛውም ብሄራዊ ንድፍ መስጠትና መቀበልን በውስጡ ያካተተ መሆን አለበት፤ ቁጥራቸው ብዙሃን የሆኑ ብሄረሰቦች ደግሞ ከነርሱ አነስ ላሉት ብሄረሰቦች ወንድማዊና እህታዊ የሆነ ቀና ልቦና በሚታይበት መልኩ በየመስኩና በየአስተዳደሩ በትምህርትና በልምዳቸው መጠን ሁሉ በተመጣጣኝ መልኩ በእኩል እርከን ተቀምጠው ሀገሪቷን እንዲመሩ ማድረግ የግድ ያስፈልጋል፤ ወያኔ እራሱን የሚያየው ልክ እንድ ትርፍ አንጀት ስለነበረ ውጥኑም ፤አካሄዱም ፤አግላይለቱም ኢትዮጵያን በጊዚያዊ ኮንትራት እንድያዘው ቤቱ ነበር ያስተዳደረው ፤ ሲዘርፍም ፤ ሲገልም ከኢትዮጵያ ጋር ምንም ውስጥዊ ትሥሥር እንደሌለው መንግስት ነበር ተግባሮቹ ሁሉ የሚያሳዩት ነው፡ መለስ፤ ስብሀት ነጋ፤ አቦይ ፤ መስፍን የሌሎቹንም ወያኔዎች የኢትዮጵያ ትፍርሳልች መስፍራርያ ጣታቸውን ሲወዘዉዙ የነበሩበት ምክንያት የመሰሪ ስራቸውን ሲጀምሩ ትግራይን እንገነጥላለን ብለው ስለተነሱ በኋላም ባላሰቡት መንገድ የኢትዮጵያ መሪዎች ሆነው ፤ በመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ቆራጭ ፍላጭ ሲሆኑና በኢትዮጵያ ህዝብን ሀብትና ንብረት ህይወት ወሳኝ ሲሆኑ የበለጠ የተነሱበት የመሰሪ እቅድ ጥቅሙን እንጂ ጉዳቱ ማየት አልቻሉም ፤ ፎቅ በፎቅ ፤ የመቶ የሁለት መቶ የጭነት መኪና ባለቤት በአመት ተተኩሶው ስማይ ያወጣቸን ይህ የጎሰኛ ስርአት እንዴት ጉዳቱን ይዩት? አሁን እንኳን ከስልጣን ወርደው ዘርፈው ጓዳቸው የከመሩትን ገንዘብ እየበተኑ እኛ የስርአቱ ተጠቂ የሆነውን ኢትዮጵያን _ ወርቅማው የኢትዮጵያ ጊዜ የወያኔ ግዜ ነው ብለው ሊያሳምኑን ሲሞክሩ ደግሞም በሆነ ሴራ መንግስት ገልብጠው ሊመለሱ ከሚያደርጉት መግተርተር በላይ የሚያሳዝንና የሚያስቅ ትርኢት የለም ፡፡ እስካሁንም ጠበቅ ያለ የዘረፉትን ዝርፍያ የሚከታተልም ስራ እየተሰራ አይደለም በሁለት ምክንያት፤ አንደኝ በዚህ ጊዜ ወደዚያ መሄዱ ካለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት አንጻር አስፈላጊ አይደለም ወይም ደግሞ አንዳንዶች እንደሚያስቡት ያለፈውን ትተን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመመስራት አስተዳደራዊ ፍትሀዊነት እንመስርት ሌላው የገበያ ስርአቱ ከተስተካከልነው ፤ በዘረፋና በወያኔ ድጋፍ የተቋቋሙ ድርጅቶች የመንግስት ድጋፍ ሲያጡ ይወድቃሉ የሚል አስተሳሰብ ነው ፡፡ ሁለቱም ሀሳቦች የየራሳቸው አሳማኝ ነጥቦች አሏቸው ፡፡ ወደፊት እያንዳንዱ ላይ ጥንካሬውንና ድክምቱን እናያዋለን ፡፡