Page 1 of 1
በህሊና ደሳለኝ ግጥም ሳቢያ ጠ/ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን እንዲለቁ እነበቀለ ገርባ ጠየቁ
Posted: 16 Sep 2019, 04:46
by Mereja.TV
Subscribe to Mereja Youtube Channel:
https://bit.ly/2WbsDeL
Re: በህሊና ደሳለኝ ግጥም ሳቢያ ጠ/ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን እንዲለቁ እነበቀለ ገርባ ጠየቁ
Posted: 16 Sep 2019, 11:09
by Assegid S.
ትላንት ያልተዘጋን መንገድ "ተዘግቷል" ብለው አንድን ማህበረሰብ ከሌላው ማህበረሰብ ለማቃቃር በሐሰት ሲመሰክሩ የሰማናቸው አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ደግሞ ሆነ ብለው ትርጉም አዛብተው ያልተሰደበን ማህበረሰብ ተሰድቧል በማለት ርካሽና የዘቀጠ ፖለቲካ ሲጫወቱ ማየት በጣም ያሳፍራል - ያሳዝናል።
ቀን አልፎ ቀን በመጣ ቁጥር እኚህ ትልቅ ሰው ናቸው ብዬ አስብ የነበረው ግለሰብ ሊወርዱ ይችላሉ ብዬ ከማስበው በታች እጅግ ወርደው ባገኛቸው ምናልባት ማሰቢያና ማገናዘቢያ አእምሮአቸውን እዛው እስር ቤት ትተውት ነው እንዴ የወጡት ብዬ አሰብኩ። ይልቅ የለቅሶአቸው ዜማ "ለምን በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊ እንግዶች አልሆንም" የሚል ለዛ ያላት ከመምሰልም አልፎ የአእምሮአቸውን መካንነት፣ አዲስ ሃሳብና የተቃውሞ ምክንያት ለማፍለቅ መንጠፉን በግልፅ ያሳያል። አዎ ... ቂማቸው ከዝግጅቱ አስተባባሪዎች እንጂ ከገጣሚዋ ግጥም አለመሆኑ በደንብ ይገባናል። በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊ እንግዶች ቢሆኑ ኑሮ እንኳን "መንጋ" በሚል ቃል ... በሰከረ ባለስልጣን መንጋጋቸው በቡጢ ቢነድልም እንዲህ አያለቅሱም ነበር። አልገባቸውም እንጂ ይህን መሳይ ዝቃጭ የፖለቲካ አተላ ናላችንን አዙሮ ገጣሚ ህሊና እንዳለችው እንደ መንጋ ተነድተን በወጥመዳቸው ለመውደቅ ትናንሾች አይደለንም። ባይሆን በአዘጋጁ ኮሚቴ ላይ ያላቸውን የቂም ድምር ለማወራረድ "የህዝብ ሀብት፣ የቀረጥ ግብር"፣ ምናምን ባሉበት ጩኽት ያላዝኑ ... በሚቀጥለው "ገብታ" እንዳይረሱ።
ግን ይኼ ነገር ትንሽ አልበዛም? ግለሰቦችንና ምሁራኖችን ለማሽማቀቅ መሞከር? ወይዘሮ የትነበርሽ፣ ገጣሚ ህሊና፣ አቶ ታድዎስ ታንቱ ...