የአገራችን አመት በዓል ገበያ ምን ይመስላል በወፍ በረር
ብቻ ምን ልበል ዓመት በዓሉ ደስ ይላል:: ከተማው ለአመት በዓሉ ሽር ጉድ እያለች ነው:: በየቦታው ዶሮ በግ ... የማይታይ ነገር የለም::
የገበያው ሁኔታ የዶሮን ካየን የፈረንጅና የአበሻ ዶሮዎች አሉ;; ህዝቡ የሚፈልገው የአበሻን ዶሮ ነው:: ምክንያቱ ደሞ የፈረንጅ ዶሮ ጣአም የለውም:: በዋጋም የአበሻ ዶሮ ውድ ነው:: እንቁላልንም በተመለከተ የአበሻ እንቁላል በጣም ተመራጭ ነው:: ዋጋውም ከፈረንጁ ጋር ሲወዳደር ውድ ነው::
የፈረንጅ ዶሮዎች በጣም ግዙፍ ቢሆኑም ሞኛ ሞኝ ናቸው :: ህዝቡ ሞኝነታቸውን የወደደላቸው አይመስልም::
አንድ እንቁላል 5.5 ብር ይሸጣል(ይህ የፈረንጅ እንቁላል ነው::) የአበሻው መገኘቱ አጠራጣሪ ነው::
ዶሮ ....... መካከለኛ ዶሮ 500 እየተሸጠ ነው::
በግ መካከለኛ 2500 ጀምሮ ይገኛል:: ግዙፍ የሆነ በግ ከ7000 ጀምሮ ይገኛል::
በትግራይ ደሞ: (አሰግደ ገብረስላሴ እንደገለፁት )
ዶሮ ---- -- ከ 250 - 450 ብር
በግ ----------ከ 2500 – 10,000 ብር እንደሆነ ተገልፆል::