"የኦሮሞ ብሄርተኞች በህወሃት ላይ አንጀታቸው አይጠናም.."
Posted: 09 Sep 2019, 13:51
"የለማ ቡድን የሚባለው ስብስብ በኦህዴድ/ኦዴፓ በኩል ሃገሬን አስመልሳለሁ ያለውን ሰፊውን የኢትዮጵያ ህዝብ እምነትም ሳያገኝ፤ ኦዴፓ/ኦህዴድ እንደ ኦነግ ካልሆነ ደስ የማይላቸውን የኦሮሞ ብሄርተኞችንም ሳያስደስት ከሁለት ያጣ ሆኖ ይቀራል፡፡ በዚህ መሃል ያለው ትልቁ አደጋ ሃገራችን ወደማትወጣበት የእርስበርስ እልቂት እና መፈራረስ የማምራት እድሏ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ተበጥብጣ እና ፈርሳ ኦሮሚያ እንደ ገነት በሆነ ሰላም መኖር የምትችል የሚመስላቸው የኦሮሞ ብሄርተኞች ደግሞ ይህ የሚያሳስባቸው ነገር አይደለም፡፡ የራሳቸው ጎሳ ሰዎች የፈደራል "ስልጣን ላይ ወጥተው የሚያደርጉትን ነገር ትቂት ጊዜ ወስዶ ለማየት ትዕግስት የሌላቸው የኦሮሞ ብሄርተኞች ኦሮሞ ስልጣን በያዘ ዘመን ሃገር ፈረሰ የመባሉ የታሪክ ተወቃሽት አማርኛ በኦሮሚያ ክልል ከሶስተኛ ክፍል ጀምሮ በትምህርትቤቶች ይሰጥ መባሉ የሚያሳስባቸውን ያህል እንኳን ከቁብ የሚያስገቡት ቁምነገር አይመስልም፡፡ እንዲህ ባለው አድሮ ቃሪያ የፖለቲካ አካሄድ ተዋናዮች የገመድ ጉተታ ውስጥ የተሰነቀረው የሃገራችን እጣ ፋንታ ከመቸውም ጊዜ በላይ አሁን አሳሳቢ ነው
በሃገራችን የጎሳ ፖለቲካን በማስኬድ በኩል እድሜ ጠገቡ የኦሮሞ ብሄርተኝነት ሲሆን ስኬታማው ደግሞ ህወሃት መራሹ የትግሬ ብሄርተኝነት ነው፡፡ማንኛውም የዘውግ ብሄርተኝነት ትግሉን የሚጀምረው አስቀያሚ የጠላት ምስል በመሳል ነው፡፡ የትግሬ እና የኦሮሞ ብሄርተኞች ደግሞ በያሉበት ሆነው የፖለቲካ ሸራቸውን ወጥረው የጠላት ስዕል ስለው ሲጨርሱ የሚመጣው ምስል ተመሳሳይ ነው:- ሰባት ቀንድ ያለው፣ ጨካኝ እና ጨቋኝ የአማራ ምስል! በዚህ የተነሳ ሁለቱም የአማራ የሆነ ነገርን ሁሉ እኩል ይጠላሉም; ይፈራሉም፡፡ ይህ የኦሮሞ እና የትግሬ የጎሳ ፖለቲከኞች ዞረው ዞረው የሚገጥሙበት ሁነኛ መገናኛቸው ነው፡፡ ለዚህ ነው የኦሮሞ ብሄርተኞች የዛሬ ሳምንት ዘቅዝቆ ገርፎ ጥፍራቸውን ከነቀለው ህወሃት ይልቅ ከዛሬ አንድ መቶ አመት በፊት በኦሮሞ የጦር ጀነራሎች ጭምር ታጅቦ ግዛት ለማስፋፋት የዘመተው ምኒሊክ የበለጠ ክፉ መስሎ የሚታያቸው፡፡
የኦሮሞ ብሄርተኞች በህወሃት ላይ አንጀታቸው አይጠናም፡፡ ተገላቢጦሹ ግን ለህወሃት አይሰራም፡፡ህወሃት ከስልጣን አምሮቱ በተቃራኒ ቆሞ፣ የማይፈልገውን ሲሰራ ላገኘው ኦሮሞ ቀርቶ ትግሬም የሚራራ አንጀት፣ ይቅር የሚል ልብ የለውም፡፡ተገልብጦ መገረፍ ያለበት የበላው በአፉ እስኪመጣ ተዘቅዝቆ ይገረፋል፣ ጥፍሩ መነቀል ያለበት ይነቀላል፣ ጀርባው መተልተል ያለበት ይተለተላል-ህወሃት እንዲህ ነው! ለኦሮሞ ብሄርተኞች ግን ዋናቸው አማራን በመጥላት መተባበሩ ላይ ነው፡፡ ከዛ በመለስ ላለው ነገር ቂም የለም!በማዕከላዊ፣ በዝዋይ፣ በሸዋሮቢ፣ በቂሊንጦ እስርቤት የተደረገባቸውን ክፉ ነገር ሁሉ አማራን ለማሸመድመድ በሚደረገው ትብብር ያካክሱና የበደል እዳ ይሰርዛሉ፡፡ ከእነሱ ጋር የማይሰረዝ የበደል ዕዳ ያለበት “ባለ ሰባት ቀንዱ አማራ” ብቻ ነው፡፡ ይህ ነገር ለትግራይ መራሹ ባልንጀራቸው ህወሃት አይሰራም"
https://ethiothinkthank.com/2019/09/06/ ... -it-poses/