Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

የኦሮሞ ጽንፈኞችና የወያኔዎች የፍቅር ፊሸታ (a marrage made in hell)

Post by TGAA » 03 Sep 2019, 23:39

የወያኔና የጽንፈኛ ኦሮሞዎች ታንጎ ዳንስ በሚያስቅ ሁኔታ እየተካሄደ ነው ፡፡ እነኝህ ጸረ ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮጵያ ያላቸው ጥላቻ እግራቸውን ፤ብልታቸውን፤ አይምራቸውን ሲያሽመደምደው የነበሩበትን ያምናውን ግፍ ረስተው ጽንፈኞቹ ኦሮሞውች አብረ አንድ አልጋ መተኛት ከጀመሩ ሰንብተዋል፡፡ ኢትዮጵያን ለማፍረስ አማራ ላይ መዝመት ብለውም ተስማምተው በተቀናበረ መልኩ እየስሩ ነው፡፡ የሚገርመው ግን ብዙው የአማራን ጥቅም በአሁኑ ዘር ተኮር አድርጎ አማራን የሚያጠቃውን ስርአት ለመቋቋምና የአማራን ጥቅም ለማስከበር በአማራነት መደራጀት አለብን በሚሉና ነገር ግን ለኢትዮጵያ አንድነት ለመሞት ለአንድ ስከንድ እንኳን በማያመነቱና፤ በኢትዮጵያ ዜግነት በተደራጁ መሀከል ያለውን አለመናበብ ሲታይ በጣም ግራ የሚያጋባ ነው ፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም የማይቃረኑ አብረው የሚሄዱ ለአንዱ ጥሩ የሚሆነው ለሌላውም ጥሩ የሚሆን ፤ መጥፎም ከሆነ ለሌላውም መጥፎ የሚሆን እንደሆነ ግልጽ ስለሆነ፤ እንግዲህ መማር ካለባችሁ ክስር ካስቀመጥኩት የወያኔና የጽንፈኞቹ የነጀዋርን ፤ኢዝቄኤልን ፤ የአራርሳን ፤ የበቀለ ገርባን ፤ ኦነግን እንዲሁም የኦሮሞ ኮንግረስን የተስተካከለ የታንጎ ዳንስ በማየት መማር ይገባቸዋል ፡፡
በመጀመርያ ጽንፈኞቹን የሚያስፈራቸው ግራ የሚያጋባቸው ነገር ቢኖር የኢትዮጵያዊነት እየገነነ መምጣት ነው ፡፡ ወያኔንም ቢሆን ውይም በእርሱ ተኮትኩተው ላደጉት ጽንፈኞች በሞላ፡፡ የኢትዮጵያዊነቱ በህዝብ ብዛቱም ይሁን ከሌላው ህዝብ ጋር ተመሳጥሮ በመኖሩ በማያወላዳ መልኩ ትልቁን ድርሻ የተሸከመው አማራው ነው፡፡ ስለዚህ አማራውን ካጠቃን ከሌላው ብሄረሰብ ኢትዮጵያውነትን ያነገቡትን በሙሉ እንደፍጥጣቸዋለን በሚል ሂሳብ ነው የሚሰሩት፡፡ አማራን በሚወክሉ ፓርቲዎችና ህብረ ብሄራዊ የሆኑት የኢትዮጵያ ዜጎችን አንድነት የሚሰብኩ ፓርቲዎች መጠንከር ወዴት እንደምያመራ ስለገባቸው ወያኔም ሆነ ጽንፈኛ ኦሮሞዎቹም አብረን ይህንን እናቁመው ብለው እየተራወጡ ነው ፡፡
1* ከበቀለ ገርባ ጀምሮ ሁሉም ጽንፈኞች መቀሌ ሄደው እንደ መካ ሲሰግዱ ከርመዋል ፤ ዘርፋ፤ ገድላ ተደብቃ የነበረችውም ወያኔም አበባ በትና ተቀብላቸዋለች፡፡ ለወያኔ ከሞተችበት የማንሰራርያ የምትልሰው አፈር ስላገኝችበት ፡፡ እነዚህ ጽንፈኞች እነርሱን ስብስቦ አዲስ አበባ ያስገባቸውን አብይን ልታስገድለው እንደነበረ አያውቁም? ፤ በደንብ ያውቃሉ ፡፡ ከአምስት ሺህ እየኦሮሞን ወጣቶች ወያኔ ገደለብን ሲሉ የሚሰሙት ለኬኛ ዲስኩራቸው ብቻ ሲሆን ነው ፤ያለዚያማ እንኮን መቀሌ የአምስት ሺህ ኬሮ ገዳዮች ዋሻ ጋር ሊሄዱ ቀርቶ ስሙን የሚያነሱት ቦታ አልነበረም ፡፤ ግን ኢትዮጵያን የሚገድል መርዝ ከተገኝ ከማንም ጋር ለመሸርሞጥ እነዚህ ጽንፈኞች አያቅማሙም፡፡ እነዚህ ጽንፈኞች አዴፓን በደንብ ተቆጣጠረውታል ስለዚህ የወያኔ መልክት ኦዴፓ በደንብ ደርሶታል ፡ እዚያ ሄደው ሲለፈልፉ የነበረውን መድገም አያስፈልግም፤
2* ከዚያ በጀዋርና በጸጋዬ አራርሳ የሚመራው ጉሌሌ ፖስት ምን የሚል አያወጣል በአብይና በለማ ማሀል ቀዳዳ ካለ ለማስፈት ለማ ላይ አብይ መፈንቅለ መንግስት ፈጽሞበታል የሚል ትልቅ ወሬ መናፈስ ጀመረ፡ ምንም ያህል የአብይን ፖለቲካዊ አካሄዶችን ባንወዳቸውም ፤ ለጽንፈኞቹ ግን አብይ እንደፈልጉት ያህል አልተመቻቸውም ፤ ስለዚህ እርሱን የአማራ አገልጋይ ነው እያሉ ስሙን ማጥፋት ከጀመሩ ከርመዎል ፡፡ በለማና በአብይ መሀከልም ክፍተት መፍጠርንም ችለዋል ፡

3* ከዚያ የኢሀድግ ስብሰባ ላይ ለማ በአልጋ ፎረም የወያኔ ጋዜጣ እንደዘገበው አስደሳች አቋም እንደያዘ ነው ፡ የወያኔው ጋዜጣም አርእስት “ ፈጣሪ በአቦ ለማ አድሮ ሊታረቀን ነው እንዴ?”
አቶ ለማ ምንድ ነው ያሉት፥-
ንግግራቸውን የጀመሩት በሊቀምበር ዶክተር አብይ የተዘጋጀው የመወያያ ፅሑፍ አርእስትን በመቃወም ነበር። “ሁለተኛ ጥፋት ቆሞ ማንቀላፋት” የሚለው አርእስት ተቀይሮ ሁኔታችን የሚገልፀው ‘አገር አጥፍተን እኛም እየጠፋን ነው’ ቢሆን ነው የሚሻል አሉ። ኢህአዴግ ፈርሷል። የለም። ከአሁኑ የፈራረሰው ኢህአዴግና አገር ከለውጡ በፊት የነበረው ኢህአዴግና አገር ከነችግሮቹ ይሻላል አሉ። ከለውጡ በኃላ እየታዩ ያሉ ችግሮች በአገራችን ታሪክ ተከስተውና ታይተው የማያውቁ ናቸው። አገር የሚያጠፉ ናቸው። ዋናው ችግራችን ኢህአዴግ ኣለመኖሩ ነው። ለውጡ ስለተጠለፈ (hijacked ስለ ተደረገ) ነው ችግር ላይ የወደቅ ነው። መዳን ከፈለግን ኢህአዴግ ወደ ነበረበት ቁመና እንመልሰው። ወይም በሰላማዊ መንገድ እንለያይ አሉ። ለዉጡ ተጠልፋል እያሉ እነ ጸጋዬ አራርሳ ሲለፈልፉ እንደንበር ግልጽ ነው ፡ኦቦ ለማም ያንን ባንዲራ አንስቶ ለውጡ ተጠልፋል እያለ ነው ፡፡ እነጀዋር አይደሉም የጠለፉት ፤ እነኢዜቄል አይደሉ ፤ ስለኢትዮጵያ አንድነት የሚታገሉት ናቸው ለውጡን የጠለፉት ፡፡
http://www.aigaforum.com/amharic-articl ... eeting.htm
4* የመለሰ ወያኔ አማርኛን ከሶስተኛ ክፍል ጀምሮ እንዲማሩ 27 አመት ፖሊሲው ቢሆንም ፡ እነጀዋር የአማርኛ ትምህርት መሰጠትን እንደ ጦርነት እንደማወጅ ነው ሲሉና ኦቦ ሽመልስም ደግሞ አንደራደርም ሲሉ፡ ወያኔም ከተል ብላ ድጋፋን ከፍ አድርጋ ተናገረች ፡ ከሁለቱ ጸረ ኢትዮጵያዊያን በስተቀረ ሌላው ህብረተሰብ ተቃውሞ አላሰማም የሱማሌው አስተዳደር በሙሉ ደግፍታል ፡፡
5* ባለፈው 150 በላይ የሆኑ የኢትዮጵያዊያን ሀገሪቱ ላይ የሚታየው የማፈናቀል ዘር ላይ ያተኮረ ጥቃት እንዲቆም በጻፉት ትክክለኛውን የኢትዮጵያን ሁኔታ የሚገልጽውን ይፋ ደብዳቤ ታትሞ ሲወጣ ፡ የኦሮሞ እንወክላለን የሚሉ 50 የሚሆኑ ደግሞ ደብዳቤው ጥቅማቸው የተነካባቸው የነፍጠኞች ድብዳቤ ነው ፤ ኢትዮጵያዊያንን አይወክልም ፡የመልስ ደብዳቤ ጽፈው ነበር ፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ ኦሮሞን እንወክላለን የሚሉ ህሊና የሌላቸው ሰዎች 2 ሚሊዮን በላይ ጊዶዎች በኦሮሞ ጽንፈኞች ጭፍጨፋ ሲፈናቀሉ ምንም ትንፍሽ ሳይሉ ፤ ካለዚያም ሲሸፋፍኑ ቢቆዩም ፡፡ ወያኔ ግን ጸረ ኢትዮጵያ ባለበት ቦታ ሁሌ ቀድማ ስለምትገኝ ድጋፋን በትግራይ ኦንላይ ላይ እንዲህ ሲሉ ድጋፍቸውን አስቀምጠውታል “Concerned Diaspora Tigraians support the communique delivered by our Oromo Ethiopian brothers and sisters
Concerned Diaspora Tigraians
http://www.tigraionline.com/articles/ti ... -each.html
ይህንን በጣም የተቀነባበረ ሴራ እያዩ እንደመናበብና ጠንክሮ አብሮ እንደመቅረብ ለኢትዮጵያ አንድነት እንታገላለን የሚሉት ግን እርስ በራሳቸው አላማቸውን ትተው ሲተናናቁ ማየት በጣም ነው የሚገርመው፡ አብይን ማውገዝ ፤ ከዚያ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ልክ እንደጠላት መፈረጅ ; ደካማ መሆን ብቻ ሳይሆን እጃችን ላይ ያለን እድል በእንዝህላልነት አሳልፎ እንደመስጠት ነው፡፡ ለምሳሌ የነበቀለ ገርባ ፌደራሊስ አባሎቼ ታሰሩብኝ ብሎ (ምንም እንኳን ስማቸውን በአሁኑ ሰአት ማቅረብ አያስፈልግም ቢልም) ለሰብአዊ መብት አቀረበ ይላል ) ይህንን የሚያደርጉት እንደኔ አስተያየት አውቀው ነው ፡፡ ለአዴፓ ሽፋን ለመስጠት ፡ ያም በአሁኑ ሰአት የሚታሰሩት የባላንደራስ አባሎች ብቻ ሳይሆኑ ፤ የአማራው ድርጅት ብቻ ሳይሆን እኛም ነን ብሎ ፖለቲካ ለመስራት ነው የታሰረባቸው የአባሎች ቁጥር 6000 (በወያኔ ጊዜም እንደዚህ የበዛ ሰው ታሰረብን ብለው አያውቁም) ኢትዮጵያን አንድነት ፤ ለህቦች እኩልነት፤ ለዲሞክራሲ ፤ ለፍትህ እንታገላለን የሚሉ ኢትዮጵያን ከዚህ በተሻለ መናበብ መቻል አለባቸው ግዴታቸው ነው