Page 1 of 1
በጉራጌዎች ዘንድ የገዳ ስርአት ስለመኖሩ አላውቅም - ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ
Posted: 03 Sep 2019, 12:36
by Mereja.TV
Subscribe to Mereja Youtube Channel:
https://bit.ly/2WbsDeL
Re: በጉራጌዎች ዘንድ የገዳ ስርአት ስለመኖሩ አላውቅም - ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ
Posted: 03 Sep 2019, 12:49
by mitmitaye
Most southern ethnics of Ethiopia had gada system. Actually, oromos learned the gada system from the sidamas and added their warring culture to it.
Gada is not oromo culture.
Re: በጉራጌዎች ዘንድ የገዳ ስርአት ስለመኖሩ አላውቅም - ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ
Posted: 03 Sep 2019, 13:28
by Horus
ፍቅሬ ቶሎሳ እንደ ወትሮው በውል ባላጠናው ነገር ላይ ሃሳብ ወረወረ ። ሲማ፣ ጋሪ የሚባል ስም ሶዶ አካባቢ ያሉት ክስታኔዎች ስለ ሚጠቀሙ ገዳ ሊኖር ይችላል አለ።
አንደኛ ፍቅሬ ሲማ እና ጋሪ የሚሉት ቃላት የሴም ቃላት እንደ ሆኑ ኤቲሞሎጂውን አያቅም ። ክስታኔውዎች ሲማ ይላሉ፣ ስሜ፣ ሲሜ ይላሉ ። ስም የሚለው የሴም ቃል ነው። ትርጉሙ መሰሌ፣ መሳዬ፣ ማለት ነው ።
ጋሪ የሚለው ከግብጽ ተነስቶ እስከ ግሪክ፣ እስከ ላቲን እስከ ሴም ድረስ ያለው ጉራጌ ኬር የሚለውና የጉራጌ ኮስሞሎጂ መሰረት የሆነው ቃል ነው። ኬር ማለት በኦሪት ዘመን የነበረውን ትርጉም እንኳ ብንተው ዛሬ በጉራጌ ዘንድ ሰላም፣ ሙሉ፣ ለም፣ ደህና፣ ጤና፣ የተባረከ፣ ሌላም ሌላም የሚል እጅግ ከፍተኛ ጽንስ ነው። ጉራጌ እዝጌር ይላል። እዝኬር ማለት ነው። ለጉራጌ እግዚአብሄር ከሚለው ቅዱስ ቃል ቀጥሎ ያለው ክቡር ቃል ኬር ነው። በእግዚአብሄር ስም ወስጥ ሄር የሚለው ኬር ነው። ያ ነው የጋሪ ግንድ። ኦሮሞ ነው ኬርን ከጉራጌ ተውሶ ጋሪ ያለው። ዛሬ ጂዳ ተብለው ስለ ገዳ ሚቀባጥሩት ግማሽ ክስታኔ ግማሽ ኦሮሞች በክስታኔውች ዘንድ ላሊጌ ወይም ሰሜንጌ ይሏቸዋል። ድሮ ራሳቸውን ክስታኔ ብለው ቋንቋውን ሲናገሩ ነበር። ኦነግ አዲሳባ ሲገባ ስልጣን ፍለጋ ኦሮሞ ነኝ አሉ ። አሁን ግራ ስለተጋቡ ገዳን ከጉራጌ ጋር አያይዘው የቀባጥራሉ።
የክስታኔ ግንድ እና ጥንታዊ ስሙ አይመለል ነው ። አይመለል ማለት አማኝ ማለት ነው። በዚያም ሳቢያ ነው ክስታኔ (ክርስቲያን) የሚለውን ስም የያዙት ።
የክስታኔ ማህበራዊ፣ ህጋዊና እና አስተዳደር ስርአት ጎርደና ወይም የጎርደና ሴራ ይባላል። ሴራ ማለት ስርአት ለሚለው ግዕዝ ነጠላ ቃል ነው። (ሴራ፣ ስርአት) ። ድርድሮ በአማርኛ ጎርደማም ይባል ነበር ። ጎርደና እጅግ ጥንታዊ ሰር አለው። ከኦሪታዊ እምነትና የቃል ኪዳን ሰራት ጋር ይያያዛል። ዛሬ የቃሉ ትርጉም ያገር ጉባኤ፣ ያገር ፓርላማ ማለትና ያገሩ ከፍተኛ ስልጣን ነው። ክስታኔ ሆነ ሌሎቹ የጉራጌ ወገኖች በገዳ የተወረሩ እንጂ በገዳ ራሳቸውን ያደራጁ አይደሉም ። ሰባት ቤት የራሱ የጆካ እና ቅጫ (መቀጫ) አለው። መስቃን ሂዱ ያው ነው ። ወዘተ
ኦሮሞ በጉራጌ ላይ የሚቃዥውን አዲስ የወረራ ህልም ያቁም !!!
Re: በጉራጌዎች ዘንድ የገዳ ስርአት ስለመኖሩ አላውቅም - ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ
Posted: 03 Sep 2019, 14:10
by Horus
ፍቅሬ ቶሎሳ ተምሮ ተምሮ ወደ ኋላ ተምልሶ በተረት ሚትዝ ቆሞ ትውልድ እያደናገረ ያለ ሰው ነው። እሱ ግዚውን ወስዶ ያንድ ቃል ስርና ስነት (ፊሎሎጂ እና ኤቲሚሎጂ) የማያተጠና በመሰለው ሃሳብ እየወረወረ ምሁራዊ ዝቅጠት ወርዷል። አንድ ሰው አንድ ቃል ስላለ ወይ ያ ስም አርጎ ስለያዘ በዚያ ብቻ ቆሞ መደምደም እንኳን ከፒኤች ዲ ካልተማረ አይጠበቅም ።
Re: በጉራጌዎች ዘንድ የገዳ ስርአት ስለመኖሩ አላውቅም - ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ
Posted: 03 Sep 2019, 14:25
by Horus
በነገራችህን ላይ ዛሬ ከግዜ ብዛት ክስታኔዎች ጎርደና የሚለውን ቃል ትርጉም እንደ ሜታፎር የቤት ግድግዳ እንጨት ማለት ነው ይላሉ። ትክክለኛ ትርጉሙ ግ ን ያገር ዳኛ፣ ያገር መዳኛ፣ ያገር ጉባኤ ማለት ነው። በ17ኛው ዘመን ጉራጌው ራስ ዘስላሴ ያጉራ ጠነ ይሉት የነበረው ነው። ጠነ ማለት ሃይል፣ ስልጣን ማለት ነው። ራሱ ስልጣን የሊለው ቃል ውዚያ አለ ። አጉራ፣ ጎራ፣ ጎር ማለት አገር ማለት ነው። ስለዚህ ጎርደና ማለት ያገር ባለስልጣን ያገር አስተዳደር ማለት ነው።
የስር አቱ ዝርዝር እዚህ በዘብዘብ አይሻም ። ይህ ነው በዘልማድ የሶዶ ጉራጌ የሚባሉት የክስታኔ ህዝብ ስርአት ።