ከ3 ቀን በፊት በአዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 10 የቤት ቁጥር 466 ፤ የቤቱ ባለቤቶች በማያውቁት ሁኔታ ከነዋሪዎቹ ፍቃድ ውጪ ከጅማ ለመጡ ግለሰቦች መታወቂያ እንዲወስዱ መደረጉና ፤ ይህ ህገወጥ ድርጊት በስፋት መገለጹን ተከትሎ የሚመለከተው አካል ድርጊቱን መፈጸሙን አምኖ ፣ የቴክኒክ ችግር መሆኑን መግለጹ የሚታወስ ነው።
ይህ መታወቂያ የማደል ተግባር በተመሳሳይ ሁኔታ የቀጠለ ሲሆን ፤ በኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 03 ለ78 ሰዎች በአንድ ቤት ቁጥር መታወቂያ ለማደል ዝግጅቱ ተጠናቆ ፤ የ5 ሰዎች መታወቂያ ፕሪንት ተደርጎ ከተሰጠ በኋላ በወረዳ ወሳኝ ኩነት ሰራተኞችና በሌሎች ሰዎች ጥቆማ ህገወጥ ድርጊቱን ማስቆም ተችሏል ። ጉዳዩም በህግ መያዙ ተገልጿል ።
ይህ ድርጊት ሊፈጸም የቻለው ፦ በወረዳው ነዋሪ የሆኑ ግለሰብ በፍቃደኝነት ለአንድ ግለሰብ ጥገኝነት በመስጠት በቤት ቁጥራቸው ወይም በግል ማህደራ እንዲመዘገብ በማድረግ ፤ ግለሰብ መታወቂያ እንዲሰጠው ያደርጋሉ ፤ ይሁን እንጂ ይህ መታወቂያ የተሰጠው ግለሰብ ከዋናው ባለቤት እውቅና እንዲሁም ፍቃድ ውጪ ሌሎች 78 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል መሸኛ ይዘው እንዲመጡ አድርጎ እሱ በጥገኝነት በተመዘገበበት የቤት ቁጥር እና ወረዳ ለ78 ሰዎች መታወቂያ ለማሰጠት ነው።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የግል ማህደራችሁን ፈትሹ !
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 34573
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 34573
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 34573
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Re: መታወቂያ እደላ በኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 3 ! " ለ78 ሰዎች በአንድ ቤት ቁጥር መታወቂያ ለማደል.."
Please wait, video is loading...
