Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39816
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በኢትዮጵያ የጎሳ ፌዴሬሽን መፍጠር አይቻልም፤ ለምን? No Trust No Federation !

Post by Horus » 01 Sep 2019, 00:34

በኢትዮጵያ የጎሳ ፌዴሬሽን መፍጠር አይቻልም
በአ/Horus


በጎሳ ፌዴሬሽን ወስጥ መተማመን በፍጹም ሊኖር አይችልም። በኢትዮጵያ ውስጥ ፌዴሬሽን የሚለው ቃልና ጽንሰ ሃሳብ ምናልባት ከ60 አመታት በላይ እድሜ አለው፤ ከኤርትራ ፌዴሬሽን እንኳ ብንጀርምር። በአሁን ሰአት በየቀኑ ይህን ቃል ሳንሰማ አንውልም። ነገር ግን አንድም ቦታ ስለዚህ ቃል ሆነ ስንጸ ሃሳብ እውነተኛ ትርጉም ሲጠቀስ ስምቼ አላውቅም ።

ፌዴሬሽን ምን ማለት ነው? የቃሉ ስረ ምንጭስ ምንድን ነው? ለመሆኑ የጎሳ ፌዴሬሽን በእውን በተግባር ሊኖር ይችላልን?
ፈደረ ማለት አመነ ማለት ነው፤ ማለትም ፈደርነት እምነት፣ ኪዳን፣ ማመን፣ አንድን ነገር እንደ እውነት መቀበል፣ አንድን ነገር ማተለቅ፣ ማግነን፣ ማክበር ማለት ነው። ሰው ከአምላኩ ጋር ያለው አንድነት በኪዳን፣ በፈደር፣ በእምነት ላይ የተመሰረተ ነው። ማህበርተኞች እቁብ የሚጠጡት በፈደር፣ በእምነት ላይ ተመስርተው ነው። ስለዚህ ያለ እምነት፣ ያለ መተማመን ፌዴሬሽን የሚባል ጽንስ፣ ልምድም ሆነ ንድፈ ሃሳብ በአለም የለም።

ስለሆነም በአላማ፣ በቁጥር፣ በባህል፣ በራእይ ሆነ በፍላጎት የተለያዩ ብቻ ሳይሆን የሚጠርጠሩ፣የሚፎካከሩ፣ የሚጣሉ ጎሳዎች በእምነት፣ በኪዳን በመተማመን ቃል ኪዳን ላይ የተመሰረተ ህብረትም ሆነ መንግስት ሊያቆሙ አይችሉም። ራሱ የፌዴራላዊ ህብረትም ሆነ የጋራ መንግስት ሊያቆሙ የሚችሉት በፈጣሪም ሆነ በሕግ ፊት እኩል የሆኑት የኢትዮጵያ ግለሰቦች ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈለገው አይነት ፌዴራሊዝም ሊቆም ሊጽና የሚችለው በኢትዮጵያ ዜጋዎችና በዜጋ ፍልስፍና፣ በዜጋ ፖለቲካ ንድፈ ሃሳብ እና በዜኘት ካልቸር ላይ ነው።
Last edited by Horus on 01 Sep 2019, 02:12, edited 2 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 39816
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢትዮጵያ የጎሳ ፌዴሬሽን መፍጠር አይቻልም

Post by Horus » 01 Sep 2019, 01:10

ዉሸት ዉሸት በጎሳ ፌዴሬሽን ቅዠት ስር ይህ የሚባለው የኢኮኖሚ እድገት ሁሉ በፍጹም አይሆንም


Horus
Senior Member+
Posts: 39816
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢትዮጵያ የጎሳ ፌዴሬሽን መፍጠር አይቻልም፤ ለምን?

Post by Horus » 01 Sep 2019, 02:06

ያበሎ

ሳታነብ መልስ መስጠትህ ይሚነግረኝ ተስፋ መቁረጥህ ነው። ሳይንሱ ያሸንፍሃል። በጎሳ ዘመንህ አልፎ የነገው ትውልድ ይረሳሃል። ጎሳ የፖለቲካ ሰራት አያቆምም።

Horus
Senior Member+
Posts: 39816
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢትዮጵያ የጎሳ ፌዴሬሽን መፍጠር አይቻልም፤ ለምን? No Trust No Federation !

Post by Horus » 02 Sep 2019, 00:59

የጎሳ ፌዴሬሽን የለም፣ አይሰራም ስንል እነመሃይም ጃዋር አይስማሙም ። በቃ ያላችሁ ምርጫ ተገንጥላችሁ የኦሮም ፈተና መስጠት ወይም የጎሳ ፌዴርንን ማፍረስ !!

Post Reply