Page 1 of 1

Re: SLOGAN OF THE DAY. ALSO: OPINION: "ታሪክ ራሱን ሲደግም".

Posted: 31 Aug 2019, 23:24
by fasil1235
yaballo wrote:
31 Aug 2019, 22:59
SLOGAN OF THE DAY. ALSO: OPINION: "ታሪክ ራሱን ሲደግም" + NEW & NICE ORTHODOX MEZMUR: "Kaleessa Naceesifte".



photo: ቄሲስ በላይ መኮንን - የኦሮሞ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መስራች።





ALSO: OPINION: ታሪክ ራሱን ሲደግም.

<<ታሪክ ራሱን ሲደግም - - -
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ "ዘመነ መሳፍንት" የሚባል ነገር ነበረ። ወቅቱ ሃረጋችን ከሰለሞናዊያን ይመዘዛል የሚሉት ሰሜነኞች ከአቢሲኒያ የፖለቲካ ስልጣን ተወግደው የወሎ ኦሮሞዎች የጎንደርን ቤተመንግስት የተቆጣጠሩበት ዘመን ነበር። ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ኣጋማሽ እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ኣጋማሽ የቆየው ይህ የወሎ ኦሮሞ በተለይም የኤጁ ስርወ መንግስት ተብሎ የሚታወቀው አገዛዝ በአቢሲኒያውያኑ ዘንድ በሃፍረትና በጥላቻ ይታወሳል። የኦሮሞ ኣንድ ጎሳ የሆነው የወሎው ኤጁ ብቻውን ሆኖ ለኣንድ ክፍለዘመን ለሚገመት ጊዜ አቢሲኒያውያንን ማስገበር በመቻሉ ይህንን ኣገዛዝ ከመንግስታዊ ታሪካቸው ቆርጠው ለመጣል ሲሉ የተለየ ስም ኣበጅተውለት "ዘመነ መሳፍንት" ኣሉት። የጎንደር ማእከላዊ መንግስትን የተቆጣጠሩትን የወሎ ኦሮሞዎች እውቅና ለመንፈግና ስልጣናቸውን ላለመቀበል ተብሎ የተበጀ ስም ነው።

ምንም እንኳ ኤጁ ኦሮሞዎች በወቅቱ ለመሳፍንቱ ለቀቅ ያለ መብት ቢሰጡም መሳፍንቱ ከኦሮሞዎቹ ኣመራር ኣቅም ውጭ መሄድ የቻሉ ኣልነበሩም። መሳፍንቱ ላይ ማለትም በነ ራስ ሃይሉ፣ ደጃች ውቤና በሸዋው ንጉስ ሳይለስላሴ ላይ ግልጽ ስልጣን ነበራቸው። ግብርም ያስገብሯቸው ነበር። የኦሮሞው ኣገዛዝ ተቀባይነት የተነፈገው በሁለት ዋና ዋና ምክኛት ብቻ ነበር። ኦሮሞ በመሆኑና በሃይማኖቱም ክርስቲያን ባለመሆኑ ነው። እንዲህም ሆኖ ኤጁዎች ስማቸውንና ሃይማኖታቸውን ጭምር ከኣማሮቹና ትግሬዎቹ ጋር ለማቀራረብ ሲሉ ብዙ ርቀት ተጉዘው ነበር። ነገር ግን ኦሮሞነታቸው የደም ጉዳይ ነውና በፍጹም ሊፋቅ ስላልቻለ "ሰለሞናዊ" መባል ኣልቻሉም። ካሳ ሃይሉ በቴዎድሮስነት ከነገሰ በሁዋላ የተሰጠው እውቅና ለኦሮሞዎቹ ኤጁዎች ተነፍጎ "ቴዎድሮስ ዘመነ መሳፍንት እንዲያከትም ያደረገ ጀግና" ተብሎ የተወደሰው በወቅቱ ኣማራ ነኝ ብሎ በመነሳቱና የኦሮሞን ኣገዝዝ ኣምርሮ በመጥላቱ ብቻ ነው።

ወደ ዛሬው ጉዳይ እንመለስ። ዛሬ ፍንፍኔ ከሚገኘው ቤተመንግስት ኦሮሞ እግሩን በማስገባቱ የዘመነ መሳፍንቱ ኣይነት እሮሮ በዘመናዊ ቅኝት ከች ብሏል። "ባለተራነት" የሚል ስምም ተሰጥቶታል። ኢትዮጵያ የተዋረደችበት ዘመን ላይ ነን በማለት ዳግማዊ ዘመነ መሳፍንት ለማለት ምንም ያልቀራቸውንም እየታዘብን ነው። ኣዎን! ብሉም ኣይገርመንም። እርግጥ ነው ኣራት ኪሎው ቤተመንግስት በኦሮሞ ርስት ላይ ከተገነባ ጊዜ ጀምሮ ቤተመንግስቱ ላይ የነገሰ ኦሮሞ ኣልነበረም። ዶር ኣብይ ቤተመንግስቱ የገባ የመጀመሪያው ኦሮሞ መሆኑ ኣይካድም። ለቤተመንግስት ያበቃው ትግል ባለቤት ለሆነው የኦሮሞ ህዝብ ግን ያመጣው የተለየ ጥቅም የለም። ከዘመነ መሳፍንቱ የኦሮሞ ኣስተዳደር በተሻለ የሁሉም መብት ተከብሮ በእኩልነት የጋራ ኣገራችንን እናስቀጥል ቢልም ከውግዘትና በሴራ ፖለቲካ ከመተብተብ ኣልዳነም። የኣመራር ብቃቱ ከኣገር ውጭ ኣድናቆት ቢያተርፍለትም ኦሮሞ ነውና ለዘመናት ስልጣን ባጣጣሙት ወገኖች ዘንድ ኣገር መምራት የማይችል "ኣቅመ ቢስ" ነው። ኣብይ ላይ የሚጎነጎነው የሴራ ፖለቲካ ኣላማው ኣንድና ኣንድ ብቻ ነው። ኣገሪቷን የመምራት በቃት የተካኑ ሰሜነኞቹ ብቻ መሆናቸውንና ኦሮሞ ለስልጣን የማይመጥን መመራት እንጂ መምራት የማይመለከተው መሆኑን ማሳመን ነው።

ነገር ግን በጥላቻ፣ በንቀትና በምኞት ለሚጋልቡት የሰሜን ፖለቲከኞች ኣንድ ሃቅ ኣስታውሼ ላብቃ። ትላንት በዘመነ መሳፍንቱ ወቅት ወሎ ብቻውን ሆኖ ያንን ሁሉ ግዜ ጎንደርን ብሎም ኣቢሲኒያን ተቆጣጥሯል። እናንተ እውቅና ብትነፍጉትም በዛ ጨለማ ዘመን ኤጁ ብቻውን ሆኖ ለክፍለ ዘመን ለሚጠጋ ጊዜ መላውን ኣቢሲኒያ ማስገበር ከቻለ መላው ኦሮሞ ደግሞ ዛሬ የኢትዮጵያን እድል ምን ሊያደርግ እንደሚችል ገና ኣልተገለጠላችሁም። ትላንት "ዘመነ መሳፍንት" ብሎ የኦሮሞን የወቅቱ ፖለቲካዊ ኣመራር ኣቅም ኣኮስሶና ጥላሸት ቀብቶ የተጣመመ ታሪክ በመጻፍ ትውልድን ማታለል ተችሎ ይሆናል። ዛሬ ግን ዘመኑ ያን ኣይፈቅድላችሁም። ኢትዮጵያን ማዳን የሚጀመረው ኦሮሞን በማወቅ ነው። ኢትዮጵያን ማዳን የሚጀመረው ኦሮሞ የኢትዮጵያን ህልውና በመወሰን ሚና ውስጥ የአንበሳ ድርሻ እንዳለው አምኖ ከመቀበልና በበከተ ጥላቻ ከገለማው የድንቁርና ኣመለካከት በመጽዳት ይሆናል። BY: Yaya Beshir>>


spiritual song: New Ethiopian Orthodox Afaan Oromoo Mezmur+++Kaleessa Naceesifte.



spiritual song: GALATAN DHIIYEESSA (AFAAN OROMO ORTHODOX).

I enjoy the music cause it’s based of Amharic 😆

The song isn’t Oromo Enough it has some Amharic words I can understand.