Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum


Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [VIDEO] ቀኑን ቀይሮ ፣ አወናብዶ ፣ ሹልክ ብሎ ቢገባም ሆቴሉ ተከቧል

Post by Revelations » 31 Aug 2019, 17:33

ያልተዘገበው ጉዞ !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድን ይፋዊ የስራ ጉብኝት በእስራኤል ሽፋን ሳይሰጠው ቀርቷል ።

ምንም እንኳን ጠ/ሚ ዶ/ር እብይ አህመድ እለተ እሁድ ወደ እስራኤል ይገባሉ ተብሎ ቢጠበቀና በሀገሪቱ መገናኛ እውታሮች ቢዘገብም ጠ/ሚ አብይ እለተ ቅዳሜ ወደ እስራኤል ገብተው ከኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ረታ አለሙ ጋር እንዲሁም ከቅርብ ሰዎቻቸው ጋር በእየሩሳሌም ኪንግ ዳቪድ ሆቴል ለመወያየት የታቀደው ፕሮግራም በቤተ እስራኤሎችና በትውልደ ኢትዮጵያውያን የጋለ ተቃውሞ ከጠዋት አንስቶ ተረብሾ ውሏል።

ተቃዋሚዎች ይዘዋቸው ከወጡት መፈክሮች መካከል “የማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እመራሮች ባስቸኳይ ይፈቱ፣ በመፈንቅለ ሰበብ የታሰሩ የአማራ ክልል የጦር መኮንንኖች ይፈቱ፣ የአስራት ጋዜጠኞች ይፈቱ፣ እና በአማራው ህዝብ ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል መንግስታዊ ሽብር ባስቸኳይ ይቁም!...” የሚሉት ዋናዎቹ ነበሩ ።

ጠ/ሚ ዶ/ር እብይ አህመድ በነገው እለት “ያድ ቨሼም” የተሰኘውን በናዚ ጭፍጨፋ ህይወታቸውን ላጡ አይሁዳውያኖች ብሔራዊ ሙዚየምን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#ኢትዮጵያንዲጄ

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: [VIDEO] ቀኑን ቀይሮ ፣ አወናብዶ ፣ ሹልክ ብሎ ቢገባም ሆቴሉ ተከቧል

Post by Assegid S. » 31 Aug 2019, 18:01

በእኚህ ሰውና በኣማራ መካከል ሰላምና ዕርቅ እንደ ኩነኔና ፅድቅ ከሞት ወዲያ ማዶ እንጂ በህይወት ዘመን የሚታሰብ አይሆንም። ኣማራ ጀግናውን በግፍ ገድለውና አስገድለውበት አይደለም ረስተውበት ሲመለከት እንኳ ይከፋዋል። ለጊዜው ቅኔውን እንተወውና ... በሰሙ ብቻ እንኳ ስንተረጉመው ... ለዛ ነበር እጅጋየሁ ሽባባው፦
"ምነው ቢነሳ መይሳው ካሳ
አልወድም ጎበዝ ጀግና ሲረሳ
"
ያለችው። This is just the beginning.




Post Reply