ዐቢይ አሕመድ መቀሌ ከተመሰረተው የሕወሓት የባላደራ መንግሥት ጋር «ግልጽ ጦርነት» ውስጥ ይገባ ይሆን?
Posted: 29 Aug 2019, 01:42
ሕወሓት «የፌዴራል መንግሥት ኃላፊነቱን አልተወጣም» በማለት «ሕገ መንግሥትና የፌዴራል ሥርዓት» ያለውን ለማዳን «የፌዴራሊስት ኃይሎች» ያላቸውን ሰብስቦ የሁለት ቀናት ጉባኤ አጠናቅቆ ቀጣይ እንቅስቃሴዎችን የሚያስተባብር ኮምቴ አቋቁሟል፤ የአቋም መግለጫም አውጥቷል። ሁሉም የጉባኤው ተሳታፊዎች ተስማሙበት በተባለው የአቋም መግለጫ «ሕገ መንግሥትና የፌዴራል ሥርዓቱን» ለመታደግ አለማቀፍ ጥሪ ቀርቧል። ይህ ጉባኤ በመንግሥትነት የተሰየመውን የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ የመንግሥትነት ሥልጣን በግልጽ ውድቅ ያደረገ ስብስብ ነው።
በመንግሥትነት የተሰየመውን የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ «ኃላፊነቱን አልተወጣም» በማለት የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ ዋና ሥራው የሆነውን «ሕገ መንግሥትና የፌዴራል ሥርዓቱን» የማዳን አላማ ይዞ የሚቋቋም ማናቸውም ስብስብ የባላደራ መንግሥት ነው። ይህ ግልጽ የሆነ በመንግሥት ላይ የተመሰረተ ሌላ መንግሥት ነው።
ባጭሩ በመንግሥት ላይ መንግሥት የመሰረተው፣ «የፌዴራል መንግሥት ኃላፊነቱን አልተወጣም» በማለት «ሕገ መንግሥትና የፌዴራል ሥርዓቱን» ለማዳን ጉባኤ የተቀመጠውና ቀጣይ መንግሥታዊ ስራዎች የሆኑትን ሕገመንግሥትና የፌዴራል ሥርዓቱን ለመታደግ አለማቀፍ ጥሪ ያቀረበው የመቀሌው ስብስብ አካል የባላደራ መንግሥት ነው።
ዐቢይ አሕመድ ከዚህ በፊት የፖለቲካ ድርጅት ባልሆነውና ሥልጣን የመያዝ አላማ ከሌለው በእስክንድር ነጋ ከሚመራው የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ጋር «ግልጽ ጦርነት» ውስጥ እንደሚገባ ነግሮን ነበር። ዐቢይ አሕመድ ከአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ጋር ጦርነት ውስጥ እገባለሁ ያለው «ምክር ቤቱ ምርጫ ሳያሸንፍ ባላደራ፣ ባደራ የሚል ጫዎታ ውስጥ ገብቷል» ብሎ ነው። ምክር ቤቱ ግን የሲቪክ ተቋም እንጂ ምርጫ የመሳተፍና የፖለቲካ ሥልጣን የመያዝ አላማ እንደሌላው ግልጽ አድርጓል።
የዐቢይ አሕመድን መንግሥት ተቀብሎ የፖለቲካ ሥልጣን የመያዝ አላማም ፍላጎቱም ከሌለው ከአዲስ አበባ ምክር ቤት ጋር «ግልጽ ጦርነት» ውስጥ እገባለሁ ያለን ዐቢይ አሕመድ አሁን በግልጽ የሚፈተንበት ወቅት መጥቶለታል። ሕወሓት «የዐቢይ አሕመድን አገዛዝ ኃላፊነቱን አልተወጣም» በማለት የመንግሥት ዋና ተግባር የሆነውን «ሕገ መንግሥትና የፌዴራል ሥርዓቱን» የመታደግ ሥልጣን ነጥቆ «ሕገ መንግሥትና የፌዴራል ሥርዓቱን» ለማዳን የሚል መንግሥታዊ አላማ ይዞ በመቀሌ ከተማ የባላደራ መንግሥት መስርቷል።
ዐቢይ አሕመድ ከዚህ መቀሌ ላይ ከተፈጠረው የሕወሓት የባላደራ መንግሥት ጋር ግልጽ ጦርነት ውስጥ ይገባ ይሆን? ነው ዐቢይ አሕመድ ጦርነት ውስጥ የሚገባው የመንግሥት ዋና ተግባር የሆነውን «ሕገ መንግሥትና የፌዴራል ሥርዓቱን» የመታደግ ሥልጣን ከዐቢይ በመንጠቅ «ሕገ መንግሥትና የፌዴራል ሥርዓቱን» ለማዳን የሚል መንግሥታዊ አላማ ይዞ የተቋቋመውን የመቀሌ የባላደራ መንግሥት እሹሩሩ እያለ የባላደራ መንግሥት የማቋቋም እቅድም አላማም ከሌለው ከአዲስ አበባው ምክር ቤት ጋር ብቻ ነው?
አቻምየለህ ታምሩ