Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

የወያኔን የ27 አመት የወንጀል ክምችት ከምንጣፍ ስር ደብቆ ሰላም ለማውረድ መሯሯጥ ሀገሪቷን ትልቅ ማጥ ውስጥ ይከታታል

Post by TGAA » 28 Aug 2019, 20:25

የኢትዮጵያን ህዝብ እየደጋገመ የጥቃት ሰለባ የሚያደርገው ነገር ቢኖር እውነታዎችን ከምንጣፍ ስር መደበቅን እንደ አርቆ አሰትዋይነት መመልከት ፤ ከግጭት ወጥተን ወደሰላም የመመለስ ዘይቤ አድርጎ መመልከትን፤ ፤ የህዝቦችን አንድነት መጠበቅ የሚቻለው ያለፈውን አለባብሶ በመተው ሰለወዲፊቱ ብቻ በመመልከት በሚል የተሳሳተ እሳቤ ነው፤ይህ የመሳሰሉ ከፊት ለፊት ሲታዮ መልካም የሚመስሉ ነገር ግን እየደጋገሙ እንደገና ህዝቡን ወደችግር የሚወስዱ የአስተሳሰብ ልምዶች ናቸው፡፡ ታሪክን ሳይማሩበት አለባብሶ መሄድ የሚረዳው ነገር ቢኖር ኢትዮጵያ ተመሳሳይ ችግሮች በተመሳሳይ ጠላቶቿ ሲገጥሟት ልክ መከላከያ እንዳልተከተበ ህጻን በቀላሉ በበሸታው እንድትጠቃ ማድረግ ነው ፡፡ ስለዚህ ታሪክን ግልጽ በሆነ ሆኔታ ማስቀመጥ ከዚህ በፊት የማያስፈልጉ መስዋእትነት ያስከፈሉንን ፤ የማያስፈልግ ሰቆቃን ያተረፍንባቸውን ክስተቶች ለማሰወገድ ይረዱናል ፡፡ ለምሳሌ የኤርትራን ታሪክ ለብቻው አውጥተን ስናየው ከኤርትራዊና በኩልና በኛ መሃከል ያለው ግንዛቢ በጣም የተለያየ ነው፡፡ በኤርትራ ሙስሊሙ ማህበርሰብ ዘንድ ስለኢትዮጵያ ያለው አስተያየትና በክርስቲያኑ ኤርትራዊያን ያለው ግንዛቤ። በትግሉ ወቅት ፡ስለኢትዮጵያ ይተረኩ የነበሩ ትርክቶች ፤ እውነትም እውሸትም ፡፡ በኢትዮጵያ በኩል ይነገር የነበረው ትርክ ግን የተሸፋፈነ፤ እውነቱን ምንም ግንዛቤ ውስጥ ያልከተተ ትርከት ነበር፡፡ መስከረም ላይ በሬድዮ ኢርትራ ከእናት ሀገሯ ጋር የተቀላቀለችበት ተብሎ ይከበራል ፡ የአረብ አገሮች ናቸው ኤርትራን አረብ ባህር ለማድረግ የሚለ ጭፍን ፕሮፓጋንዳ ይለፈፍ ነበር ፡ ያ ሁሉ ኢትዮጵያዊ የተሰዋው ግን እንደሚነገረውና እንደሚተረከው ኤርትራን ኮሎኒ ለማድረግ ብሎ መቼም አልነበረም ፡፡ ስለኤርትራ ታሪክ በደንብ ብናውቅ ኖሮ ብዙ ጥፋቶችን ማሰውገድ እንችል ነበር ኤርትራም ኢትዮጵያም የተሻለ ውጤት ያለው የተለያየ ወይንም ተመሳሳይ ጉዞ ማድረግ ይችሉ ነበር ፤ ይህ የኢትዮጵያ ታሪክን የማደባበስና የማለፍ ስራ ብዙ ጉዳት ለሁለቱም ህዝቦች አድርሷል፡፡ የእውነት ታሪካችንን ብናውቅ ኖሮ ኤርትራዊያን ከ60 አመት በላይ በጣሊያን ኮለኒ ሲደረጉ በልምደም ሆነ በጣሊያን ፍላጎት የተለይ ሳይኮሎጂ የተቀናጁ ህዝቦች ናቸው ፡ እንጀራ መብላታቸው፤ ትግርኛ መናገራቸው ፤ አንድ ህዝብ ሊያደርገን የሚችልበት መንገድ የለም ፡ ሁለት ትውልድ በሌላ በኮሎኒያል ስርአት የታነጸ ሰው ተመሳሳይ አመለካከት ከኢትዮጵያዊያን ጋር አንድ አይነት ስነልቦና ሊኖረው አይችልም ( ሁለት ትውልድ ያልኩበት በግዜው አማካዩ እድሜ 30 አመት ስለነበረ ነው) ኢትዮጵያ ከሸፋፈናቸውና ካለፈቻቸው ታሪኮች በኋላ ላይ ግን የጎዶት ብዙ ታሪኮች አሉ እንደምሳሌ ለጣልያል ያ30ለገሉ ባንዳዎች ሀይለሰላሴ ሲገቡ ታሪካቸው ሳይነገር ተሽፍኖላቸው ስልጣን ተስጥቷቸው ልክ እንድ አርበኞቹ ተጠቃሚ ሆነዎል ፡ ህዝቡ ባንዶች ነበሩ ብሎ ሰፈር ውስጥ ከኋላቸው ከሚያወራው በስተቀር ምንም ተጠያቄ ያደረጋቸው ነገር የለም “ ለሰላም “ ሲባል፡፡ ይህ ሲባል በቀል ይወሰድባቸው ለማለት እንዳልሆነ በግልጽ ማውቅ ያስፈልጋል ፡፡ ግን የሰሩት ስራ ግን በግልጽ ተቀምጦ ምን አይነት ግለሰቦች ምን እንዳደረጉ ፤ በግልጽ ለህዝቡ እንዲያውቅ ማድረግ ያስፈልጋል ፡፡ አሁንም ወያኔዎች የሰሩትን ስራ ቶሎ ሀገሪቷን ለማረጋጋት በሚል ስባብ የማለባበሱ ስራ ኢህአድግ በመንግስት ሚዲያ በሰፊው ይዞታል ፡ ይህ ደግሞ በለውጡ ላይ ለሚያሰሩ ያለፈውን ወንጀላቸውን ከህዝቡ በመደበቅ ከፍርድ እንዳይቀርቡ በማድረግ የልብ ልብ እንዲያገኝ ብቻ ሳይሆን ጊዚያቸውን ወስደው አሲረው የጭቆና መዳፋቸውን እንዲመልሱ መሬቱን አደላድሎ እንደመጠበቅ ነው የሚቆጠርው ፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ በብድር ካመጣቸው 51 ቢሊየን ብር 30 ቢሊየን ያሸሹ ሰዎች ፤ ከሱማሊያ አስተዳደር በተለያዩ አካባቢዎች ሰዎች እንዲገደሉ ገንዘብ ያፈሰሱ ፤ እራሱ አብይን በአደባባይ ሊገሉ በይፋ ያሴሩ ሰዎችን በፖለቲካ አቋም ልፍስፍስነትና፤ ግልጽ አቋም ወስዶ የተደረጉትን የወያኔ ወንጀሎች ሸፋፍኖ መሄድ ከፍተኛ አደጋ የሚዳርግ መሆኑን መረዳት ያለባቸው የአብይ መንግስትና ብሄራዊ ሀላፊነት ያለባቸው የፖለቲ ፓርቲዎች ሀላፊነት ነው፡፡ ይቅርታ ቢደረግ እንኳን ኢትዮጵያ ላይ የተደረጉ ወንጀሎች ይፋ ማድረግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እነኝህ የማይተኙ የኢትዮጵያ ጠላቶች መቀሌ ላይ ጭፈራ ጀምረዋል _ እንደሚባለው አያያዙን አይተው ጭብጦውን ቀሙት፡፡ አብይ ልብህ እንደ እርግብ ጥንቃቄህ እንደ እባብ የሚለውን የመጻሃፍ ቅዱስ ጥቅስ ከልቡ ሊገነዘብ ይገባል ፡፡