Page 1 of 1

በወሎ ወልድያ የፍተሻ ኬላ የኦነግ ሳይሆን እንዳልቀረ የተገመተ ዩኒፎርም የጫነ አውሱዙ መኪና በቁጥጥር ስር ዋለ።

Posted: 26 Aug 2019, 23:07
by Revelations
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ነሃሴ 20 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

ትናንት ነሃሴ 19 ቀን 2011 ዓ.ም መነሻውን ትግራይ ክልል አድዋ አል ሜዳ ጨርቃጨርቅ ያደረገና 50 ማዳበሪያ የኦነግ ዩኒፎርም ነው የተባለ ልብስ የጫነ ኮድ አ.አ 3 ቁጥር 11059 መዳረሻው አዲስ አበባ የሆነ አውሱዙ ሙኪና ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።

ከሾፌሩ ጋር 3 ሰዎች አብረው የነበሩ ሲሆን ላኪም ተቀባይም ግለሰብ መሆኑ፣ ሚሊተሪ/ዩኒፎርም በግለሰብ መዘዋወርና መመረት አለመቻሉ፣ ከዚህ ቀደምም 5 ዓይነት ቀለም ያለው ቲሸርት ኬላ ከተያዘ በኃላ በጉምሩክ በኩል መለቀቁ ለጥርጣሬ እንደዳረጋቸው የኬላ ተቆጣጣሪዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል ገልጸዋል።

አሁን ላይ መኪናው ተይዞ ሰዎቹ የህጋዊነት ወረቀት እናመጣለን ብለው እየተጠበቁ መሆኑንም ጨምረው ነግረውናል።

በወልድያ ከተማ በቁጥጥር ስራው ያገኘናቸው ጓድ መሪ ምክትል ሳጅን መሃመድ አወል እንደነገሩን በቁጥጥሩ ሂደት እክል እየገጠማቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ፈትሸው ንብረቱን ለጉምሩክ ሲያስተላልፉ ጉምሩክ ማህተም እየመታ እንደሚያሳልፋቸው ገልጸዋል። ለዚህም የልዩ ሃይሉ ጋር በዘላቂነቱና ውሳኔ አሰጣጡ ላይ እንደሚመክር ነግረውናል።

ዘጋቢያችን አራጋው ሲሳይ ከወልድያ በስፍራው ተገኝቶ እንደዘገበው







Re: በወሎ ወልድያ የፍተሻ ኬላ የኦነግ ሳይሆን እንዳልቀረ የተገመተ ዩኒፎርም የጫነ አውሱዙ መኪና በቁጥጥር ስር ዋለ።

Posted: 26 Aug 2019, 23:25
by ethiopian
Rev Drama Queen is at it again ..... keep crying about nothing and you will live an illusion ..... Federalist Ethiopia is a way to go whether you are happy, sad or a drama faaaaag

Re: በወሎ ወልድያ የፍተሻ ኬላ የኦነግ ሳይሆን እንዳልቀረ የተገመተ ዩኒፎርም የጫነ አውሱዙ መኪና በቁጥጥር ስር ዋለ።

Posted: 26 Aug 2019, 23:58
by Revelations
ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የተሸጋገረው ወታደራዊ ትጥቅ በሱዳን የጸጥታ አካልት ቁጥጥር ስር ዋለ
***************************************


መነሻው ኦሮሚያ ክልል አምቦ ከተማ እንደሆነ የሚነገርለት እና በአምስት ከባድ የጭነት መኪናዎች የተጫነው ግዙፍ ወታደራዊ ትጥቅ በሚስጥር በመተማ በኩል ወደ ሱዳን ለማሸጋገር ሲታሰብ የመተማ ዩሃንስ ከተማ ህዝብ ባደረገው ጥርጣሬና ክትትል ጉዳይ ተጋልጦ ህዝብና የኢህአዴግ መንግስትን አወዛጋቢ ሆኖ መሰንበቱ ይታወቅል።

በወቅቱ የሚደርሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በመተማ በኩል ወደ ሱዳን ተሸጋግሮ የገባው ወታደራዊ ትጥቅ ገዳሪፍ ከተባለችው የሱዳን ከተማ በጸጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ወዋሉን ከዚሁ ከተማ የሚገኙ መረጃዎች ያመለክታል ። ይህ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የተሸጋገረው ወታደራዊ ትጥቅ በሱዳን የጸጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር እንዲውል የቻለበት ምክንያት ሱዳን በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የጦር መሳሪያ እቀባ የተጣለባት አገር በመሆኗ የተባበሩት መንግስታት የጦር መሳሪያ ተቆጣጣሪ አካላት ባደረጉት ክትትል እንደሆነ ተገልጿል።