ነሃሴ 20 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ
ትናንት ነሃሴ 19 ቀን 2011 ዓ.ም መነሻውን ትግራይ ክልል አድዋ አል ሜዳ ጨርቃጨርቅ ያደረገና 50 ማዳበሪያ የኦነግ ዩኒፎርም ነው የተባለ ልብስ የጫነ ኮድ አ.አ 3 ቁጥር 11059 መዳረሻው አዲስ አበባ የሆነ አውሱዙ ሙኪና ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።
ከሾፌሩ ጋር 3 ሰዎች አብረው የነበሩ ሲሆን ላኪም ተቀባይም ግለሰብ መሆኑ፣ ሚሊተሪ/ዩኒፎርም በግለሰብ መዘዋወርና መመረት አለመቻሉ፣ ከዚህ ቀደምም 5 ዓይነት ቀለም ያለው ቲሸርት ኬላ ከተያዘ በኃላ በጉምሩክ በኩል መለቀቁ ለጥርጣሬ እንደዳረጋቸው የኬላ ተቆጣጣሪዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል ገልጸዋል።
አሁን ላይ መኪናው ተይዞ ሰዎቹ የህጋዊነት ወረቀት እናመጣለን ብለው እየተጠበቁ መሆኑንም ጨምረው ነግረውናል።
በወልድያ ከተማ በቁጥጥር ስራው ያገኘናቸው ጓድ መሪ ምክትል ሳጅን መሃመድ አወል እንደነገሩን በቁጥጥሩ ሂደት እክል እየገጠማቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ፈትሸው ንብረቱን ለጉምሩክ ሲያስተላልፉ ጉምሩክ ማህተም እየመታ እንደሚያሳልፋቸው ገልጸዋል። ለዚህም የልዩ ሃይሉ ጋር በዘላቂነቱና ውሳኔ አሰጣጡ ላይ እንደሚመክር ነግረውናል።
ዘጋቢያችን አራጋው ሲሳይ ከወልድያ በስፍራው ተገኝቶ እንደዘገበው



