[DW] የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ምርጫው እንዲራዘም ጠየቀ
Posted: 21 Aug 2019, 13:37
ምርጫው እንዲካሄድ ግፊት ማድረግ በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም- ኢዴፓ
(ኢ.ፕ.ድ)
በ2012 ዓ.ም ሊካሄድ የታሰበውን ሀገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ግፊት ማድረግ በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለውና ሀላፊነት ከሚሰማው አካል የማይጠበቅ መሆኑን ኢዴፓ አስታወቀ።
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የፓርቲው 7ኛ ጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ዛሬ መግለጫ በሰጠበት ወቅት እንደተገለጸው ቀጣዩን ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ አገሪቱ ውስጥ አስተማማኝ ሰላም ካለመኖሩም ባሻገር መንግስት በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ህግና ስርዐትን ማስከበር አቅቶታል።
ኢዴፓ ከምርጫው በፊት ሊከናወኑ የሚገባቸው ተግባራት ባለመከናወናቸው እና ምርጫ ቦርድም ነፃና ፍትሀዊ ምርጫ ለማካሄድ በሚያስችል ዝግጁነት ላይ ባለመሆኑ እንዲሁም ሌሎች ስራዎችን ለመስራት ለሚያስችል ጊዜ መራዘም አለበት ብሎ እንደሚያምን በመግለጫው ተጠቅሷል።
''ይሁን እንጂ ምርጫው እንዲካሄድ ግፊት እያደረጉ ያሉ ጥቂት የፖለቲካ ሀይሎች ይህንን ለማድረግ ያስገደዳቸው የህግ መከበር ተቆርቋሪነት ሳይሆን የአንድነት ሀይሉ በተዳከመበት በዚህ ወቅት አዲስ የትብብር ግምባር በመፍጠር ምርጫን አሸንፈው ለስልጣን የሚበቁት የተሻለ እድል እንደሚኖር ስለገመቱ ነው'' ብሏል ፓርቲው።
ኢዴፓ ምርጫው እንዲራዘም የፈለገው ህግ እንዳይከበር ፈልጎ ሳይሆን ቢካሄድ በሀገር ላይ ሊያደርስ የሚችለው ከፍተኛ ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ተብሏል።
በድልነሳ ምንውየለት