በታከለ ኡማ ፈቃድ ከባድ የደን ጭፍጨፋ በመሀል አዲስ አበባ እየተካሄደ ነው!
Posted: 15 Aug 2019, 13:06
ዛሬ ቦሌ ወረዳ 3፣ ፒኮክ መናፈሻ አካባቢ ከባድ የደን ጭፍጨፋ እየተካሄደ እንደሆነ መረጃ ደረሰኝና ከደቂቃዎች በፊት ወደ ስፍራው ሄድኩ። እንደተመለከትኩት ከአውሮፓ ህብረት ጀርባ ያለው ይህ ጥቅጥቅ ደን ሙሉ ለሙሉ እየተቆረጠ ነው። እርግጥ ቆረጣው የተጀመረው ከሶስት ቀን በፊት እንደነበርና ይህ የባህር ዛፍ ደን እድሜው ከ40- 50 አመት እንደሚገመት የአካባቢው ሰዎች ነግረውኛል።
ቆረጣውን ሲያስተባብር የነበረውን ግለሰብም አግኝቼ ስለጉዳዩ ጠይቄው ነበር። የፍቃድ ደብዳቤ አሳይቶኝ እንዲህ ሲልም መለሰልኝ:
"እነዚህን ለመቆረጥ የደረሱ ዛፎችን እንድንቆርጥ እና ወደ 8,000 ካሬ የሚጠጋው መሬት ላይ መዝናኛ ፓርክ፣ የመኪና ማቆሚያ፣ ሲኒማ፣ የመዋኛ ገንዳ፣ ላይብረሪ፣ ካፌዎች እና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎችን እንድንሰራ የፈቀዱልን ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ ናቸው። ዛፎቹን ቆርጠን እና ሸጠን ገቢውን ለአ/አበባ አካባቢ ጥበቃ እናስገባለን፣ ቦታውን ደሞ እኛ የአካባቢው ሰዎች እንጠቀምበታለን። ስለዚህ ህገ-ወጥ ቆረጣ እያካሄድን አይደለም። ዛፎቹም በእርጅና ምክንያት እራሳቸው እየወደቁ ነው።"