Page 1 of 1

[VOA UPDATE VIDEO] በወለጋ ህፃናት በምግብ እጥረት እየሞቱ ነው

Posted: 15 Aug 2019, 11:19
by Revelations
ቪኦኤም ትክክለኛውን ቃል መጠቀም የፈራ ይመስላል:: "በወለጋ ህፃናት በረሃብ እየሞቱ ነው" ማለት ቀጥተኛ አነጋገር ነበር:: ግን ምን እንደፈሩ ባናውቅም ፈርተው ትተውታል:: ቀለብ ከ አዲስ አበባ ይሰፈርላቸዋል እንዴ?!

Please wait, video is loading...

Re: [VOA] በወለጋ ህፃናት በምግብ እጥረት እየሞቱ ነው

Posted: 15 Aug 2019, 12:25
by Revelations


በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀሙሩ ጉዪ ቴቦ ቀበሌ የሰፈሩ ተፈናቃዮች "ላለፉት ሶስት ወራት የእህል ድጋፍ በመቋረጡ ከ10 በላይ ሕፃናት በምግብ እጥረት ሞቱ" ሲሉ ገለፁ፡፡
ነቀምት —

የወረዳውና ዞኑ አደጋ ሥጋት አመራር ፅህፈት ቤት ኃላፊዎች ድጋፉ የተቋረጠው ለሦስት ወር ሳይሆን ለሁለት ወር ነው ካሉ በኋላ ለበላይ ባለሥልጣን አመልክተው መልስ እየተጠባበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል፤ ስለ ህፃናት መሞት የሰሙት እንደሌለም ገልፀዋል::

የክልሉ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር በበኩሉ፣ ድጋፉ የዘገየው እህል ለማድርስ በዝናብ ምክንያት መንገድ ስለማያስገባ ዕርዳታው በፍጥነት በገንዘብ መልክ ይሰጣቸዋል ሲሉ አስታውቀዋል::

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

https://amharic.voanews.com/a/displaced ... 41816.html

Re: [VOA] በወለጋ ህፃናት በምግብ እጥረት እየሞቱ ነው

Posted: 16 Aug 2019, 02:35
by Revelations

Re: [VOA] በወለጋ ህፃናት በምግብ እጥረት እየሞቱ ነው

Posted: 20 Aug 2019, 16:53
by Revelations
Please wait, video is loading...