‘ኳሲቱ’ና ብልሀተኛው ታጋይ - የዚያኛው ዘመን ወግ
Posted: 14 Aug 2019, 12:04
እንዲህ እንዲህ ላፍታም ቢሆን እስቲ የትጥቅ ትግል ወቅት ወጎችን እናጣጥም! ያኔ በዚያኛው ዘመን፡ እንደ አሸን የፈላው የደርግ ሰራዊት ኤርትራ ውስጥ ይርመሰመስ የነበረበት ግዜ፣ ያኔ ኤርትራ ውስጥ ነጭ ለባሾችና ሰላዮች የከተማ የውስጥ አርበኝነትን ትግል ለመደፍጠጥና ለመደምሰስ “ጀሮ ጠቢዎቻቸውን” በየአንዳንዱ ኤርትራዊ ቤተሰብ ደጃፍ ላይ ያሳድሩ በነበረበት ወቅት። ያኔ መሬት ቀውጢ ስትሆን ግዜ ባልባሌ ምክንያት “ውሃ ቀጠነ” እያሉ ለደርጉ እጃቸውን የሚሰጡ ወዶገቦች በተበራከቱበት ዘመን። ሻዕብያ፡ ኤርትራ ውስጥ በአንድ ስፍራ፡ የህዝብ አደረጃጀት ክፍል አባላቶቿንና ከተለያዩ ስፍራ የተሰባሰቡ የአካባቢያዊ(ዞባዊ) ሰራዊት ክፍሎች የተውጣጡ ታጋዮችዋንና አባላቶቿን በመሰብሰብ፡ ወደፊት ላሰበችው ረቂቅ ውጥን ትግባሬ፡ መላ ለመዘየድ አንድ ግዙፍ ስብሰባ ጠራች።
ከዚያስ . . .
ከዚያማ የናቅፋው ‘ግልገል አንበሳ’፣ በአስመራ አውሮፕላን ማረፊያ የደርጉን 33 ጀቶችንና ሄሊኮፕተሮችን በ18 ደቂቃ ኦፕሬሽን ዶግ አመድ በማድረግ ያደባዮት የኤርትራዉያን ጥቂት ኮማንዶዎች የሚሊተሪ ኦፕሬሽን ስትራቴጂ ነዳፊና አስተግባሪዉ፣ የህዝብ አደረጃጀትና የዞባዊ ሰራዊት ክፍል ሃላፊዉ ታጋይ ስብሃት ኤፍሬም “ወዲ ኤፍሬም” ስብሰባዉን ከሚመሩት ታጋዮች መካከል፣አንዱ ነበር።
ስብሰባዉ እንደታሰበው በተወጠነለት ሰዓትና ቦታ ተጀመረ። ግሩም የሃሳብ ፍጭትም ተካሄደ። በስብሰባው መካከል ወዲ ኤፍሬም ለሁለቱ የስብሰባው ግዙፍ ክፍሎች ማለትም ለህዝብ አደረጃጀት(ድርጅት) ክፍልና ለሰራዊቱ ወኪሎች እስቲ የሚከነክናችሁና ሊብራራላችሁ የምትሹት ጥያቄ ካላችሁ ዕድሉን ለናንተ ሰጥቻለሁ ጥያቄዎቻችሁን አቅርቡ አላቸው።
የህዝብ አደረጃጀት ክፍል አባላት፣ በደርጉ ጥንግንግ የስለላና የነጭ ለባሽና በተለይም በ “ወዶ-ገባ” ሴራ ብዙ የስራ እንቅፋት ይፈጥርባቸው ስለነበር፣ በወኪላቸው አማካኝነት እንዲህ በማለት የሚቆጠቁጣቸውን ጥያቄ አቀረቡ፦
“እነዚህ ወዶ ገቦች ከኛ ጋር እንዳልታገሉና ብዙ ምስጢራችንን እንዳልተጋሩ ይሀው ወደ ደርጉ እየገቡ በዕለታዊ ስራችን ውስጥ ብዙ እንቅፋት እየፈጠሩብን ስለሆነ፣ ድርጅታችን አፋጣኝ ፈውስ ይፈልግላቸው፣ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም የማያዳግም እርምጃ ለምን አይወስድባቸው? አስቸገሩን እኮ! መፈናፈኛ ሊያሳጡን እኮ እየተወራጩ ነው!” በቁጭት ስሜት ወኪላቸው ጥያቄውን አቀረበ። አብዛኛው የ”ክፍሊ-ህዝቢ” ታጋይም በልቡ “እውነቱን ነው፡ እነዚህን ወዶገቦች ባንዴ ድምጥማጣቸውን በማጥፋት የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ነው ፈውሳቸው” እያለ አሰላሰለ።
ወዲ ኤፍሬምም ለቀረበለት እውነተኛ ጥያቄ መለሰ፡ እንዲህ ሲል፦
“አዪ ይህ አይነት መሰናክል ካልታከለበትማ ትግል መች ትግል ይባልና! እነዚህ ወዶ ገቦች እንደሆኑ ከአለቆቻቸው ጋር በተለያዩ ኢምንት ምክንያቶች እየተኳረፉ የሄዱ(የከዱ) እንጂ የፖለቲካ ብስለት ኖሯቸው ወደ ደርግ የገቡ አይደሉም። ሶቭየት ህብረትና ሌሎች አሉ የሚባሉ የአለም ሃያላን የሚያግዙት ግዙፉ ጠላታችን ደርግ ሊደፈጥጠን እያቆበቆበና ሳያሰልስ እየሰራ በሚገኝበት ቅጽበት፡ ለነዚህ በስሜት ለሚጋልቡ አንዳንድ ትርኪምርኪዎች ግዜና ጥይት አናጠፋም። ሲሆን ሲሆን በስራችን ላይ ይበልጥ ረቀቅ ያለ ዘዴና ብልሀትን አክለን፣ እነዚህን ወንድሞቻችንን በጥበብና በመላ አስተምረን ለዓላማችን ማስፈጸሚያ መሳሪያዎች ወይም ድልድዮች አድርገን እንጠቀምባቸዋለን፣ ስለሆነም ይልቅስ እንዴት አድርገን የኛን አላማ አስፈጻሚዎች እንደምናደርጋቸው ዘይዱ። ወዘተ” የሚል የቤት ስራን ለትጉዎቹ አባላቶቹ ሰጠ።
ቀጥሎም የተለያዩ ዞባዊ ሰራዊት ክፍሎች ወኪል ደግሞ ጥያቄያቸውን በወኔና በቆራጥነት፡ የአይበገሬነት ስሜት እየተናነቀው እንዲህ ሲል አቀረበ፦
“እኛን የሚገርመን ከደርግ ሰራዊት ጋር እስከመቸ ነው የምንፋጠጥ፣ በአሁኑ ወቅት ከመቸውም ግዜ በላይ ሞራላችን ሆነ ብቃታችን እጅግ አስተማማኝ ነው፣ ታድያ በፊታችን ተገትሮ ያለውን የጠላት ሰራዊት አብጠልጥለን አውቀነዋል፡ ስለሆነም ድምጥማጡን እንድናጠፋው ለምን አይፈቀድልንም፣ ሆ ብለን አንዴ ከተነሳን ሃያል ክንዳችንንና ብርቱ በትራችንን ሊቋቋም የሚችል ምንም ዓይነት ኃይል ሊገታን አይችልም፣ ስለዚህ በአፋጣኝ አንድ በሉን፡ ገስግሰን ይህን የደርግ ሰራዊት እንገርስሰው።” ይህ በወኔ የተሞላ የታጋዮች ወኪል ጥያቄውን አቅርቦ በተሰብሳቢዎችም ተጨብጥቦለት ተቀመጠ። ‘ወዲ ኤፍሬም’ ምን ብሎ ይመልስ ይሆን እያለ አሰፍስፎ ይጠብቅ የነበረው ተሰብሳቢም በጉጉት መልስ መጠበቅ ጀመረ።
ወዲ ኤፍሬም ቀጠለ
“ኣዪ ስታስቡት በጠበንጃ አፈሙዝ ይህን ሁሉ ሰራዊት ገለንና ማርከን የምንጨርስ ይመስላችኋልን? ስንት ሚሊዮን ብለን ገለን ልንጨርስ? እኛ እንደሆንን ከቁጥራችን አንጻር ወታደር መግደል ላይ ብቻ አተኩረን መስራት አያዋጣንም ይልቅስ ኳሷን ኢትዮጵያ ውስጥ ማስገባት ነው የሚያዋጣን? ኳሷ እዛ ከሄደች በኋላ የኛ ስራ ከበቂ በላይ ተከናውኗል ማለት ይቻላል፣ ከዚያ በኋላ ይህን ግዙፍ ሰራዊት እንዴት እንደምናደርገው ባይናችሁ ታያላችሁ፣ ‘ወዲ ኤፍሬም’ ምን ብሎ ነበር ትላላችሁ።”
ተሰብሳቢው ሁሉ “ፀጥ ረጭ” ሲል እያንዳንዱ ተሰብሳቢ ግን “እውነቱን ነው” እያለ በልቡ ያወጋ እንደነበር ሳይታለም የተፈታ ሓቅ ነበር።
እናማ ምን ለማለት ነው፡ ጀኔራሉ የዋዛ አይደሉም፣ ሁሉንም እንደየ አመጣጡ የመመለስ፡ አፈሙዝ ይዞ የመጣንም እንዴት መመለስ እንዳለባቸው ጠንቅቀው የሚያውቁ ባፍላው ዘመናቸው የፋርማሲ ተማሪ የነበሩ የኋላኋላ የአስተዳደርና የወታደራዊ ስትራቴጂ ፋርማሲስት ለመሆን የበቁ በሳል ሰው ናቸው ለማለት ነው። እንዲያው የዘመነ ትጥቅ ትግል ውሏቸውን ለግዜው ብናቆየው፣ ወያኔን እንኳ ስንት ግዜ አይደል ጀነራሉ በረቂቅ ጥበባቸው ‘መድኃኒቷን’ የሰጧት - የአስተዳደርና ወታደራዊ ስትራቴጂ ‘ፋርማሲስቱ’ ጄኔራላችን! ወዲ ኤፍሬም!!!
ከዚያኛው ዘመን ወግ!