Re: OPINION: 'put lipstick on a pig, but it's still a pig .. አሳማ ያው አሳማ ነው..እንደ ታዬ ቦጋለ ያሉ የተሸናፊ አፅናኞች፣ ማስታገሻ እንጂ መፍትሄ አይ
Posted: 09 Aug 2019, 04:30
ጋላ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከገባ 500 አመት አልሞላዉም፡፡ እንግዳ ስለሆነ ጃዝ ብቻ ካሉት ባንዲ ማዳጋስካር ይገባል፡፡yaballo wrote: ↑09 Aug 2019, 04:11"You can put lipstick on a pig, but it's still a pig. .. አሳማ ያው አሳማ ነው--እንደ ታዬ ቦጋለ ያሉ የተሸናፊ አፅናኞች፣ ማስታገሻ እንጂ መፍትሄ አይሆኑም!"
=============
"የኢትዮጵያ (የአማራ) የፖለቲካ ልሂቅ፣ ይህች የግፍ ክምር የሆነች፣ የጠቅላይ-ተስፋፊዎች የምናብ ውላጅ የሆነች ኢትዮጵያ፣ ዓይኑ ላይ እንደ ፈንዲሻ እየፈነዳዳች እያየ፣ የታሪክ ሁነቶችን መካድን ሙያው አድርጎ የተነሳ ይመስላል።
ሰሞኑን፣ እንደ ታሪክ ሊቅና እንደ ሥነ-ጥበብ ሰው ሆኖ፣ ታዬ ቦጋለ የሚባል የሰው ጭንጋፍ (ጭንጋፍ ነኝ ያለው እራሱ ነው!) ይሄን በድፍረት ሲያደርግ ይታያል።
ሰሞነኛ የተሸናፊዎች አፅናኝ (comforter of the losers) መሆኑ ነው። አንድ ሰሞን፣ ኃይሌ ላሬቦ፣ አሰፋ ጨቦ፣ ታድዮስ ታንቱ፣ ወዘተ ባለተራ ሆነው፣ ይሄን ሚና ሲጫወቱ ነበር። ይሄ ታዬ፣ በጥራዝ ነጠቅ የታሪክ ንባብ አደባባይ ወጥቶ፣ ዘመነኛ-ልሂቅ ደንበኞቹን እያፅናና፣ 'ያልተማሩ ምሁራን' ያላቸውን ደናቁርት ጀግኖቹን እያወደሰ፣ ሌሎችን 'ያልተማሩ መሃይማን' ብሎ ሲያንኳስስ፣ በእያንዳንዱ ዓረፍተነገር፣ እራሱ አለመማሩን እና መሃይምነቱን (ያልተማረም፣ መሃይምም መሆኑን) ሲገልፅ አመሸ። ማነብነብ የሚችል መሃይም!
በክህደት እና ጭፍጨፋን በማስጌጥ፣ ወይም ውብ አስመስሎ በማቅረብ (by aestheticizing barbarity)፣ አገርን መገንባት ይቻል መስሎአቸው፣ በጃዝ አጀብ ታድመው፣ ለውሸትና ለክህደት ሲገለፍጡና ሲያጨበጭቡ የሚያመሹ፣ የደላቸው (privileged) የግፍ አትራፊዎችስ ምን ይባላሉ?
ይኼንኑ የታሪክ ክህደትና ሕዝቦችን በጅምላ የመሳደብ ተግባር፣ በግብር ከፋይ ሕዝብ በሚታገዝ ብዙሃን ሚዲያ የሚያቀርብ መንግሥትስ ምን ይባላል?
'የፈለገ ያህል ብታሽሞነሙነው አሳማ እንደው ያው አሳማ ነው፣' ይላሉ ፈረንጆቹ። የፈለገውን ያክል 'በማስዋብ' (aestheticize በማድረግ) ክርፋቱን ለመቀነስ ብትሞክርም (deodorize and sanitize ብታደርገውም)፣ የተፈጸመውን ግፍ፣ ግፍነቱን አይሽረውም።
የመንግሥታቱንም ሆነ የመሪዎቹን ስህተትም አይሰርዘውም። የአገሪቱን የጋራ የበደል (የ collective guilt) ክርፋት አያርቀውም።
ከሁሉም በላይ፣ መሠረታዊውን የፖለቲካ ተቃርኖ አያጠፋውም። አገረ-መንግሥቱንም ከመፈራረስ አድኖ፣ ታሪኩን ለመዋጀት አይረዳም።
አንዴ በመፈክር ('ኢትዮጵያ ትቅደም'፣ 'ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር'፣ ወዘተ በማለት)፣ አንዴ በተረትና በድግምት ('የ3000 ዓመት ያልተቋረጠ የመንግስትነት ታሪክ' እያሉ በመደጋገም፣ 'ዳግማዊ ጽዮን የሆንን አገረ-እግዚአብሔር ነን' በማለት፣ 'ባንዲራችን ከሰማይ የተሰጠች የቃልኪዳን ምልክትና ሥላሴያዊ ቀስተደመና ነች'፣ ወዘተ በማለት)፣ ወይም በተራ 'ሥነጥበባዊ' ፕሮፓጋንዳ ('ነጭ ነኝ' ብሎ የሚኩራራን ከንቱ ፀረ-ጥቁርና ፀረ-አፍሪካ ንጉሥ፣ 'ጥቁር ሰው' እያሉ በማሞካሸት፣ ወዘተ) አገረ-መንግሥት መፍጠርም፣ መገንባትና ማቆየትም አይቻልም።
መፈክሮችን ('እንደ ባጃጅ ጥቅስ') በማብዛት፣ የታሪክ ሁነቶችን በመካድ፣ ወይም ተረትን በመደጋገም የግፍ ወራሽ የሆኑ ተሸናፊዎችን ለማፅናናት (to comfort losers and to assuage the guilt of the hegemonic habesha political class) ይጠቅም ይሆናል እንጂ፣ መሠረታዊውን የፖለቲካ ተቃርኖ መፍታት፣ የሕዝብን ጥያቄዎች መመለስ፣ ወይም ፍትህ፥ እርቅ፥ እና ሰላም በማውረድ፣ አገርን ማደላደል አይችልም።
መፈክር መደርደር ('መደመር')፣ ተረት መደጋገም ('ወደ ቀድሞው ክብር እንመለሳለን'፣ 'ኢትዮጵያ የዘላለም እውነት ነች')፣ እና የሃሰት ፕሮፓጋንዳን በመንዛት አገር የሚቀና ቢሆን ኖሮ፣ በዚህ ባለፈው ዓመት ብቻ የተፈጠሩትን ፈታኝ ችግሮች ባላየን ነበር።
በዚህ ባለፈው ዓመት፣ እነዚህን መፈክሮች፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይና ደብተራ አማካሪዎቹ፣ በጉልበት በሕዝብ ላይ ለመጫን በሞከሩ መጠን፣ ተቃርኖዎቹ ጦዘው፣ አገሪቱ አይታ ወደማታውቀው ቀውስ ውስጥ ገብታለች።
የኢምፓየሩ ማዕከል የሆነው የአማራ ክልል እራሱ፣ እነዚህ መፈክሮች በወለዱት እብሪት አብጦ በመፈንዳት፣ እራሱን እያጠፋ ይገኛል፤ አገሪቷንም የለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት አፋፍ ላይ አዳርሷታል።
ስለዚህ፣ የሃበሻ ምሁራን፥ ፖለቲከኞች፥ የኪነትና የፕሮፓጋንዳ ሊቃውንት፣ ይሄን አጽናኝ ውሸቶችን የመፈብረክ ሥራ ትተው፣ (ቀላሉንና) ቅድሚያ የሚሻውን ተቃርኖን የመፍታት ሥራ፣ የሕዝብን ጥያቄዎች የመመለስ ሥራ፣ እና ፍትህ የማስፈን ሥራ፣ ቢሰሩ ይሻላቸዋል። ምናልባትም ይሄን በማድረግ እራሳቸውን በዚህ ዘመን ለመዋጀት ይችሉ ይሆናልና።
ተቃርኖውን ለመፍታት፣ ከታሪካቸው ጋር መታረቅ አለባቸው።
አገረ-መንግሥቱ፣ በጅምር የቀረ የኢምፓየር ፍርስራሽ መሆኑን መቀበል ያስፈልጋቸዋል።
በዚህ ፍርስራሽ ውስጥ፣ በሕዝቦች መካከል የተዛነፈ የሕዝቦች/ብሔሮች ግንኙነት መኖሩንና ይሄን ማስተካከል እንደሚገባ መቀበል አለባቸው።
ይሄ የተዛነፈ ግንኙነት፣ የዘመናችንን የፖለቲካ ጥያቄዎች እንዳወረሰን መረዳት ይገባቸዋል።
በአሁኑ ወቅት፣ የአማራ ልሂቃን የሚጠይቁት፣ በሌሎች ሕዝቦች ላይ የበላይነትን የመጎናፀፍ፣ ሌሎችን የመግዛት፣ እና አገሪቷን የግል እርስታቸው አድርገው የማስቀጠልና የማቆየት ጥያቄ ነው። (ይሄንን፣ የአማራነት ፖለቲካ ይበሉት፣ የአንድነት ፖለቲካ ይበሉት፣ የዜግነት ፖለቲካ ይበሉት፣ የግለሰብ መብት (የ liberalism) ፖለቲካ ይበሉት፣ ምንም ይበሉት፣ በመሠረቱ የሚፈልጉት፣ አገሪቷን በሙሉ እነርሱ ብቻ አዛዥ የሚሆኑባት፣ የእነሱ ቡድን ራዕይና ማንነት የሚናኝባት፣ የነሱ የቋንቋና የባህል የበላይነት ሕጋዊ መሠረት የሚይዝባት፣ የግል እርስታቸው ማድረግ ነው።)
የአማራ ልሂቃን እና 'Ethiopianist ነኝ' የሚለው የሃበሻ የፖለቲካ መደብ (political class) በሙሉ፣ ይሄንን የባለርስትነትና የበላይነት ጥያቄ ማዕከሉ ያደረገ ፖለቲካ፣ በግልፅ ካልተወ በቀር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ መቼም ሰላም አይወርድም።
ምክንያቱም በዛሬ ጊዜ፣ ይሄንን ተቀብሎ፣ ዝም ብሎ ተገዝቶ የሚኖር አንዳችም ሕዝብ የለምና።
ይሄ ዓይነት አስተሳሰብ፣ በፖለቲካ የማያስኬድ (politically unsustainable) ብቻ ሳይሆን ምግባራዊ ትክክለኝነትም የለውም። ይሄ አስተሳሰብ የማያስኬድበት ምክንያቱ፣ አገሪቱ ውስጥ ለዘመናት ታፍኖ የቆየ እና አሁንም እየታፈነ ያለ፣ የፍትህ እና የእኩልነት ጥያቄ መኖሩ ነው።
የእኩልነትና የፍትህ እጦት በቁጭት እያንተከተከው ያለ ሕዝብ ላይ፣ የአማራ (ወይም የማንም ሌላ ወገን) የበላይነትን (በአማራነት ሥም፣ በአንድነት ሥም፣ በግለሰቦች መብት ሥም፣ ወይም በኢትዮጵያዊነት ሥም ተደራጅተህ) ለመጫን መሞከር፣ የለየለት የፖለቲካ ስሜት መገንፈልን (an overflow of resentful political passion) ያስከትላል።
ሰሞኑን በተለያዩ የደቡብ ክልል ከተሞች የምናየው ይሄንን የፍትህና እኩልነት ናፍቆት የወለደውን የተቃውሞ ስሜት መገንፈል ነው።
የእነዚህ ሕዝቦች የፍትህ ጥያቄ፣ በአስቸኳይ መመለስ አለበት።
ቢያንስ ቢያንስ፣ ለመመለስ የሚያስችል ቅን ልቦናና በጎ ፈቃድ መኖሩን (good faith and commitment) ማሳየት ይጠበቃል።
ፍትህን ማስፈን፣ የሰላምና መረጋጋት ዋስትና ነው።
ሰላምና ፍትህ ካለ፣ እውነትና ሃቅን በጋራ በመመሥረት፣ ዘላቂ እርቅ (reconciliation) ለመፍጠር መንገዱ ተመቻቸ ማለት ነው።
በመሆኑም፣
መሠረታዊ የፖለቲካ ተቃርኖን በመፍታት፣ የፍትህና የእኩልነት ጥያቄን በመመለስ፣ ሰላም፥ እውነትና፥ ዘላቂ እርቅ ላይ የተመሠረተ አገረ-መንግሥት ግንባታ ላይ ለመሰማራት እንዲቻል፣ ከግፍ ታሪካችን ጋር መታረቅ ይበጃል እንጂ፣ እኒህ (እንደ ታዬ ቦጋለ ያሉ) የክሹፍ ኢምፓየር አጽናኝ የሆኑ ሰሞነኛ 'ኮሚኮችን' እየጋበዝን በክህደት መዝናናት፣ በሕዝብ የፍትህ ጥያቄ ላይ መዘባበት፣ እና የቆሸሸ የግፍ ታሪክን ለማስዋብ (deodorize or aestheticize ለማድረግ) መሞከር አይጠቅምም።
ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ተሞክሮ አልሰራም።
አሁንም፣ ወደፊትም፣ አይሰራም።
እላይ እንዳልኩት፣ ምንም ብታሽሞነሙነው አሳማ ያው አሳማ ነው።"
By: Tsegaye Ararssa ... https://www.facebook.com/tsegaye.ararss ... 5762872428



