Page 1 of 1

ኦነግ በምእራብ ሃረርጌ ጥቃት አደረሰ ፣ ኦህዴድ/ኦዲፒ አጥቂን በስሙ መጥራት ፈርቷል

Posted: 08 Aug 2019, 14:21
by Revelations

Re: ኦነግ በምእራብ ሃረርጌ ጥቃት አደረሰ ፣ ኦህዴድ/ኦዲፒ አጥቂን በስሙ መጥራት ፈርቷል

Posted: 08 Aug 2019, 14:43
by Revelations

Re: ኦነግ በምእራብ ሃረርጌ ጥቃት አደረሰ ፣ ኦህዴድ/ኦዲፒ አጥቂን በስሙ መጥራት ፈርቷል

Posted: 08 Aug 2019, 14:57
by Revelations
1. በምዕራብ ሐረርጌ በርደዴ በተባለ ቦታ፣ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 10 ሰዎች መሞታቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘግቧል፡፡ 3 ሰዎችም ቆስለዋል፡፡ በግጭቱ ሳቢያ መኪና መንገዶች በመዘጋታቸው፣ ከሐረር-አዳማ-አዲስ አበባ የሚጓዙ መንገደኞች በረሃ ላይ እንደቆሙ ናቸው፡፡ አዲስ ስታንዳርድ በበኩሉ የኦሮሚያ ኮምኒኬሽን ቢሮን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ግድያውን የፈጸሙት ታጣቂዎች ናቸው፡፡ ጥቃቱን ተከትሎም የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ፖሊሶች ወዳካባቢው ገብተዋል ተብሏል፡፡ የጥቃቱ አድራሾች ማንነት አልተገለጸም፡፡

Re: ኦነግ በምእራብ ሃረርጌ ጥቃት አደረሰ ፣ ኦህዴድ/ኦዲፒ አጥቂን በስሙ መጥራት ፈርቷል

Posted: 08 Aug 2019, 15:16
by Revelations
ከሀረር ወደ ኢዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ ልዩ ስሙ ቦርደዴ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።

አማራ ሚድያ ማዕከል/አሚማ
ነሃሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

የአካባቢው ነዋሪዎች ግጭት መፈጠሩን አሩጋግጠውልናል ብሎ ኢትዮ ኤፍ ኤም እንደዘገበው በግጭቱ 7 ሰዎች ሞተዋል፤ 3 ሰዎች ደግሞ በህይወት እና በሞት መካከል ናቸው፡፡

የሚመለከተው አካል ጉዳዩን አጣርቶ መፍትሄ እንዲሰጣቸውና የተፈጠረውን ችግር እንዲያስረዳቸውም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡

በአካባቢው በተፈጠረው ግጭት መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት ምንም ዓይነት መኪና እንዳያልፍ ተዘግቷል፡፡
ከሀረር ወደ አዲስ አበባ፣ ናዝሬት እንዲሁም ሌሎች አካቢዎች ለመሄድ የተሳፈሩ ተጓዦች ከማለዳው 2 ሰዓት ጀምሮ መንገዱ መዘጋቱን እና በረሀ ላይ መሆናቸውንና መንቀሳቀስም እንዳልቻሉ ታውቋል፡፡

ከቦርደዴ - አዋሽ መግቢያ ድረስ መኪኖች መንቀሳቀስ ባለመቻለቸው ተሰልፈው መቆማቸውን እና ይህ ነው ብሎ የተፈጠረውን ችግር ያስረዳቸውም ሆነ መፍትሄ የነገራቸው አካል እንደሌለ ተናግረወዋል፡፡

መንገዱ የተዘጋውም በግጭት ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ወደ አሰብ አስክሬን ጭኖ የሚያልፍ መኪና ማየታቸውንም አክለዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዩን ፖሊስ ገና እያጣራው ነዉ ተብሏል።

Re: ኦነግ በምእራብ ሃረርጌ ጥቃት አደረሰ ፣ ኦህዴድ/ኦዲፒ አጥቂን በስሙ መጥራት ፈርቷል

Posted: 08 Aug 2019, 18:58
by Revelations

Re: ኦነግ በምእራብ ሃረርጌ ጥቃት አደረሰ ፣ ኦህዴድ/ኦዲፒ አጥቂን በስሙ መጥራት ፈርቷል

Posted: 08 Aug 2019, 20:18
by Medo
Really?😂😂😂😂 It was skirmish between pastoralists around Awash. Big lier. Kkkk