የማይገባቸውን ሽልማትና ውዳሴ እየዞሩ የሚለቃቅሙት ወሴት(ወንድም ሴትም) መአዛ አሸናፊ ተከሰሱ!!
Posted: 05 Aug 2019, 03:14
የማይገባቸውን ሽልማትና ውዳሴ እየዞሩ የሚለቃቅሙት ወሴት(ወንድም ሴትም) መአዛ አሸናፊ ተከሰሱ!!
===
የቀድሞ ረዳት ጠቅላይ አቃቤህግ እና የፍታብሄር መምሪያ ሀላፊ የኢህአዴግን መንግስት በመቃወም አሁን በስደት ላይ የሚገኙት አቶ አለማየሁ ዘመድኩን ( Alemayehu Mengesha) ስለ ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ተከታዩን መረጃ አጋርተዉናል
"ድፍረት" በሚባል በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና ያገኘው እና እነ Angelina Jolie"በከፍተኛ ሁኔታ የደገፉት እና የተሳተፉበት ፊልም መሰረቱ ወሪ/ት አበራሽ በቀለ ድሪባ በአርሲ ዞን በተፈጸመባት የጠለፋ ፣የአስገድዶ መድፈር እና የእገታ ሕገ ወጥ ድርጊት አበራሽ ደፋሪውን በራሱ ክላሽንኮፍ ጠብመንጃ መሳሪያ ገድላ እጁን ለፖሊስ በመስጠትዋ ጉዳዩ በኦሮሚያ ፖሊስ ተጣርቶ በኦሮሚያ አቃቤ ህግ አማካይነት በዞን ፍርድ ቤት የወንጀል ክስ ይቀርብባታል ።በዛን ወቅት በሴቶች ላይ በጾታቸው ምክንያት ለሚደርስባቸው ጥቃት የህግ እና ሌሎች ድጋፎች የሚያደርገው እና በውቅቱ በወ/ሮ መአዛ አሸናፊ(የአሁንዋ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ) ይመራ የነበረው "የሴት የህግ ባለሞያዎች ማህበረ"የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት አስገድዶ ሊደፍራት በነበረው ግለሰብ ግድያ የተጠረጠርችውና በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላ የነበረችውን ወ/ሪት አበራሽ በቀልን በጥብቅናና የህግ ምክር አገልግሎት ለመስጠት የሴት የህግ ባለሞያዎች ማህበር ይወስናል ።ጉዳዩን እንዲከታተሉ አሁን በህይወት የሌሉትን ጠበቃ ወ/ሮ እታገኘሁ ለሜሳን ይመድባል ።
ወ/ሮ እታገኘሁ ለሜሳ ይህንን ጉዳይ ለመከታተል ከአዲስ አበባ መኖሪያቸው ገዳዩ ወደሚታይበት ዞን ፍርድ ቤት አሰላ እየተመላለሱ ከፍተኛ ጥረት እና የሞያ ክህሎት በታከለበት ሁኔታ ወሪ/ት አበራሽን ከወንጀሉ ክስ ነጻ መሆኖን ፍርድ ቤት ይወስናል ከእስርም ትፈታለች ።
የወ/ሪት አበራሽ ከወንጀሉ ክስ ነጻ መለቀቅ የጠበቃዋ የወ/ሮ እታገኝ ጥረት መሆኑን እኔ በግሌ በቅርበት አውቃለሁ።አብዛኛው የህጉ ማህበረሰብም ይህንን ያውቃል።የወ/ሪት አበራሽ እውነተኛ ታሪክ በቢቢሲ ዘጋቢ ፊልም የተሰራበት ከመሆኑ ባሻገር "ድፍረት" በሚል ርእስ ፊልም ተሰርቶበት ፊልሙ የተለያዩ ሽልማቶችን ለማሸነፍ በቃ።ይህንን ጉዳይ በከፍተኛ የሞያ ብቃት ለውጤት ያበቁት ጠበቃ እታገኝ ለሜሳ በድንገት ከዚህ አለም በሞት ይለያሉ።
ለማንም ግልጽ ባልሆነ መንገድ ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ይህንን ጉዳይ ለውጤት ያበቁ የህግ ባለሞያ እየተባሉ ሽልማት እና ሙገሳ ሲዥጎደጎድላቸው "የለም እኔ አይደለሁም ወ/ሮ እታገኝ ናት የጉዳዩ ባለቤት እና ለውጤት ያበቃችው"ብለው እውነተኛ ምስክርነት ሲሰጡ እና ሽልማቱ ወደወ/ሮ እታገኝ ወራሾች እንዲተላለፍ ሲያደርጉ አይታዩም ።ይልቁንም በሳቸው ልዩ ጥረት አበራሽ ነጻ እንደወጣች በየአደባባዩ ሲናገሩ ይስተዋላሉ ።እዚህ ዋሽግተን ዲሲም ባለፈው ሲድ የተባለ ድርጅት ሽልማት አበርክቶላቸዋል ። በቅርቡ በኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በጣይቱ ማዕከል ሌላ የሙገሳና የሽልማት ፕሮግራም ተደርጎላቸዋል።የማይገባቸውን ሽልማት እና ክብር በመውሰዳቸው ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ከሌሎች ተከሳሾች ጋር እሳቸው በፕሬዘዳንትነት በሚመሩት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ የፍትሐብሔር መዝገብ ቁጥር 158041 በይግባኝ የፍታብሄር ክስ ቀርቦባቸው ጉዳዩ በችሎት እየተመረመር ይገኛል ።
ክብርት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ባልዋሉበት እና ባላከናወኑት ጉዳይ ክብር እና ሞገስ ሲቸራቸው "ህሊናቸው" ሳይጠይቃቸው እንዴት በጸጋ ይቀበሉታል? የወ/ሮ እታገኝ ወራሾች በወ/ሮ መአዛ ላይ እሳቸው በሚመሩት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡት የፍታሐብሔር ክርክር ያለተጽእኖ አድልዎ ይታይ ይሆን ወይ?