በአማራ ክልል የተሰራው ትልቁ የዘይት ፋብሪካ ስራውን ሊጀምር ወራት ይቀሩታል! ይህ ፋብሪካ አብዛኛውን የአገሪቱን የዘይት ፍጆታ ያሟላ ተብሎ ይጠበቃል::
Posted: 04 Aug 2019, 11:51
በጎጃም በቡሬ አካባቢ በአማራው ባለ ሀብት አቶ በላይነህ ክንዴ በ 500 ሚልዮን ብር ወጪ የተሰራው የዘይት ፋብሪካ የመጀመርያው ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅዋል::
ከስድስት ወር በኃላ ስራውን እንደሚጀምር ተገልፅዋል::
ይህ ፋብሪካ ሲጠናቀቅ የሃገሪቷን 60 ከመቶ የዘይት ፍላጎት እንደሚሸፍን ተነግሯል

ፋብሪካው ባንድ ቀን ወደ 650,000 ሊትር የpalm ዘይት እና 653,332 ሊትር የአኩሪ አተር: የሱፍና የሌሎችን የቅባት እህሎች ዘይት ማምረት ይችላል:: ባጠቃላይ በቀን ከአንድ ሚልዮን በላይ ሊትር ያመርታል ተብሏል:: በተጨማሪ ወደ 120 ሺ ቶን የተቀነባበረ የሰሊጥ ምርት ወደ ውጭ እንደሚልክ ታውቅዋል::
2000 ሰራተኞችንም እንደሚቀጥር ይጠበቃል::
ትልቁ ችግር ግን የመብራት አቅርቦት እንደሆነ ተገልፅዋል!
!
source -amara mass media