አፄ ዳዊት ( ንጉሥ ይበቃል )
አፄ ውድም ፍሬ የተባለው ነዋየ ማርያም በነገሠ በአስረኛው ዘመነ መንግሥቱ በተቅማጥ በሽታ ታሞ ስለሞተ ወንድሙ ዳዊት የተባለው ይበቃል ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ በ 1366 ዓ.ም. ነገሠ። በአፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ሣልስ ሠላማ ወይም ካልዕ ሠላማ የተባለው ጳጳስ በዘመነ ጵጵስናው ኢትዮጵያ ለግብጽ ሙሉ በሙሉ የኃይማኖት ጥገኛና በእስክንድርያ ስር ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ውል እንዲዋዋሉና አፄ ዳዊትን ደህና አድርጎ በመስበኩና በማሳመኑ ግብራቸውንም ገጸ በረከታቸውንም እንዲያቀርቡ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ምእመናን በዘመነ ኦሪት ከቀዳማዊ ምኒልክ ዘመን ጀምሮ በሌዋውያን ካህናት አማካኝነት ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀበሉትን አምልኮተ እግዚአብሔር ሥርአትንና ትእዛዛቶችን በሚፈጽሙበት ጊዜ ለማስተው የተለያዩ ጽሁፎችና ስብከቶች አዘጋጅቶ ነበር ሳይሆን ቀረ። በሳልስ ሠላማ አስፈላጊ እንዳልሆነ ከተሰበኩት መካከል ጥቂቶች ለአብርሃም የታዘዘውን ግዝራት በሙሴ ሕግ የተጻፈውን የመብል ስርአት የእግዚአብሔር ቃላት የተጻፈባቸውን ጽላቶችና ታቦተ ሕጉት በቅዱስተ ቅድሳት መቅደስ ውስጥ ማስቀመጥ በአዲስ ኪዳን ስለተሻረ አያስፈልጉም እያለ አስተምሮአል ጽፎአል፤ ነገር ግን በእየሱስ ክርስቶስ በባለቤቱ ቃል “እኔ ሕግና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም” ባለው መሠረት ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊያት የብሉይ ኪዳንና የአዲስን ኪዳን በተዋህዶ አዋህደው አጽንተው ኑረዋል።
https://yetemonamonew.wordpress.com/201 ... %E1%8A%95/