የሰሞኑ የኤርትራ ጉድ!
Posted: 30 Jul 2019, 07:06
ከኤርትራ የሚሰማው ወሬ ደሞ ገራሚ ነው:: ሰሞኑን በጀርመን ኤርትራኞች ሰላማዊ ሰልፍ አርገዋል:: አገራቸው መብት የሌላቸው ወይም አንድም ተቃውሞ የማያሰሙ ጉዶች: አንድ ኤርትራው እግሩ በጥይት ተመታ ብለው ጩሀታቸውን በጀርመን አሰምተዋል:: ዘረኝነት ነውም ሲሉ ተሰምተዋል::
ሁለተኛ የኤርትራ ወሬ:
አንድ ኤርትራዊ የስምንት ዓመት ኤርትራዊ እስከ እናቱ : በፍጥነት ወደሚበር ባቡር ገፍትሮ ልጁን እንዲሞት አርጎታል:: ምን አይነት ጉድ ነው?
https://bbc.In/2K3emOv
ሶስተኛ ስለ ኤርትራ ወሬ:
በአንድ ኤርትራዊ ወታደር በነበረ በጣም ልብ የሚነካ ፅሁፍ ባጭሩ ይህን ይላል:
በፈረንጆች አቆጣጠር 1976 ኮቲት በሚባል ስፍራ ተወልዶ ያደገው ተስፋጋብር የውትድርና አገልግሎት እንዴት መንፈሳዊ ህይወቱን እንዴት ቀምቶ ወደማያቀው ዓለም እንደወሰደው ይናገራል::
“በ1995 ዓመት መንፈሳዊ ላይ ትምህርት ለማገልገል የምሯራጥ የ19 ዓመት ዲያቆን ነበርኩ::
በዚሁ ዓመት ሕይወቴን የሚለውጥ ነገር ተከሰተ:: የብዙ ሴት ቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና ወንድ ዲያቆናት ስም ዝርዝር የያዘ ወረቀት በየአውራጎዳናዎቹ: በየሱቆቹ ለወራት ተለጥፎ ይነበብ ነበር:: እዚህ ዝርዝር ውስጥ የኔም ስም ነበረበት:: የቤተክርስቲያን አገልጋይ ወደ ውትድርና ብዬ ተደንኩኝ ::
የተጠራንበት ቀን እንደደረሰ ወታደሮች መጥተው እኔና እኩዮቼን በቁጥጥር ስር አደረጉን:: በቅኝ ግዛት ግዜ ያልተደፈሩ ቤተክርስቲያናት በኔ ግዜ መደፈሩ እያዘንኩኝ ወደ ብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ሄድኩኝ::
እዛው በወታደሮች ጥበቃ ለአስራ አንድ ዓመት አሳለፍኩኝ:: ሳዋ ላይ ምንም ነገር ከመጥፎ ነገር የሚከለክልህ ስለሌለ : ለሱስ ተጋለጥኩኝ::
የባድሜ ጦርነት ላይ ተሰለፍኩኝ:; የጥይት ድምፅ ከማያንቀላፋበት : አብረውን ከዘመቱ እኩያ ጉደኞቼን ካጣሁበት የባድሜ ጦርነት ተርፈ ወደ ቤተሰቦቼ ተመለስኩ::
ባድመ ላይ ተማርኬ ስለነበር ደዴሳ ላይ ሁለቱ አገራት ምርኮኞች ሲለዋወጡ ነበር ወደ ኤርትራ የተመለስኩት::
1998 አስር ሰዓት ላይ በትግራይ ማትያስ ምሽግ ላይ ተኩስ ከፈትን:: በሕይወቴ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የወደኩት ያን ግዜ ነበር:: ብዙ ሰው ያን ቀን አለፈ::
ለመጀመሪያ ግዜ የኢትዮጵያ ሰራዊትን ልንገጥም የሄድን ግዜ ሳይገባኝ እናላግጥ ነበር::: የነበረው ጦርነት ደርሶ ፊታቸው ስንደርስ :ቦምብ እንደቆሎ ተወረወ ረብን::ጥይት እንደ ዝናብ ተርከፈከፈብን:: ከፊት ከህዋላ ጉዋደኞቼ ተረፈረፉ: ኦሮማይ ! አበቃ!
ሳልሳይ ወረራ በምንለው የኢትዮጵያ ጦር ባጠቃበት የመጨረሻው ጦርነት ተማርኬ በሕይወት ከቀሩ የሻብያ ሰራዊት አንዱ ነኝ::
ከዚያ በህዋላ ለ11 ዓመት ብሔራዊ ውትድርና ስሰጥ ቆየሁ: በደሞዝ: በእድገት የሚታይ እድገት ባለመኖሩ ተስፋ ቆረጥኩኝ:: ከኤርትራ መልቀቅ አለብኝ አልኩኝ :: ከዚያም ከኤርትራ መንገድ አሳብሬ ትግራይ ገባሁ:: ከአዲስ አበባ እስራኤል ! ”
https://bbc.In/2K4qHC6