Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Maxi
- Member+
- Posts: 5951
- Joined: 06 Mar 2014, 04:33
Post
by Maxi » 25 Jul 2019, 10:04
ሰሞኑን #በሲዳማ ዞን የተለያዩ አከባቢዎች ጥቃት ከተፈፀመባቸው መካከል የጉራጌ እና ስልጤ ተወላጆች ይገኙበታል። በሁለቱ ብሔሮች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ከሌሎች ለየት የሚያደርገው ከደህዴን ሊቀመንበር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል እና ምክትላቸው አቶ #ኤሊያስ_ሸኩር ጋር የተያያዘ መሆኑ ነው።
የሲዳማን ክልልነት ያስተጓጎሉት ሁለቱ የደህዴን አመራሮች ናቸው የሚል እምነት በኤጄቶዎች ዘንድ በስፋት ይንፀባረቃል።
ስለዚህ እነዚህን ሁለት የደህዴን ከፍተኛ አመራሮች ለመበቀል በሚል በአከባቢው በሚኖሩ የስልጤና ጉራጌ ተወላጆች ላይ የከፋ ጥቃት እንደተፈፀመ ለመረዳት ተችሏል። ይህን አስከፊ ድርጊት በአካል ከታዘቡ ዓይን እማኞች በደረሰን መረጃ መሠረት ኤጄቶዎች በስልጤዎች ላይ ጥቃት የሚፈፅሙት "#ሙፈሪያት_ታስጥላችሁ!"፣ በጉራጌ ላይ ደግሞ "#ኤሊያስ_ያስጥላችሁ!" እያሉ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ዛሬ ላይ ብዛት ያላቸው የሲዳማ ዞን አመራሮች ከሃላፊነት መነሳታቸውን ተከትሎ በተለይ በጉራጌና ስልጤ ተወላጆች ላይ የበቀል ጥቃት ሲፈፀምባቸው ስለሚችል በህብረተሰቡና የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ዘንድ አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል።
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 35028
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 25 Jul 2019, 12:31
ይህኮ ሳይታለም የተፈታ ነው። ይህ ብቻ አይደለም ገና ድሮ ከመለስ ጀምሮ ጉራጌ በኢትዮጵያዊነት ሳቢያ በዘርኞች ትርስ የተነከሰበት ሕዝብ ነውኮ። ቴዲ አፍሮኮ በናዝሬት ኮንሰት እንዳያሳይ እንደ ተክለከለ አለኮ። ይህ ሁሉ ደሞ አንድ ሕዝብ ለሚያምንበት ነገር በጽናት የሚከፍለው ዋጋ ነው።
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 35028
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 25 Jul 2019, 13:16
Halfi woyaniew - Ejeto is jail, dude !!