መሪው ራሱን ከህዝቡ ከፍ አድርጎ የማያይ ከሆነ መፈራራትም ሆነ መነዘነጣጠል አይኖርም። ህዝብም መሪውን የራሱ አድርጎ ከልቡ ይቀበላል። የኤርትራ ህዝብ ለኢሳያስ ነፍሱን ይሰጣል::
Posted: 21 Jul 2019, 13:43
ሰሞኑን ካስገረሙኝ ፎቶዎችና ቪዲዎች .. https://www.facebook.com/DendenMedia/vi ... 231867811/
----
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና አቶ ተወልደ ገብረማሪያም በአስመራ ጎዳና ላይ ረጋ ብለው እያወሩ ይጓዛሉ። አንድ ወጣት ከእነርሱ ራቅ ብሎ በስማርት ስልክ ፎቶ ያነሳቸዋል። ሴኩሪቲዎች የልጁን ነገር ቁብ አልሰጡትም። ልጁም ለምንም ነገር ግድ ሳይኖረው ነው ዘና ብሎ ፎቶውን የሚያነሳው (ደግሞ ግማሽ ሰውነትን በመኪና ከልሎ ከጀርባ ፎቶ ማንሳት ያልተለመደ ነገር ነው)።
መሪው ራሱን ከህዝቡ ከፍ አድርጎ የማያይ ከሆነ መፈራራትም ሆነ መነዘነጣጠል አይኖርም። ህዝብም መሪውን የራሱ አድርጎ ከልቡ ይቀበላል። የኤርትራ ህዝብ ለኢሳያስ ነፍሱን ይሰጣል የሚባለው ሰውዬው ከህዝቡ የተለየ ህይወት ስለማይኖሩ ነው።
-----
ሌላ ከአስመራ የመጣልኝ መረጃ አለ።
አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በትግሉ ዘመን የህግሓኤ መሪ ብቻ ሳይሆኑ ሙሉ ወታደርም ነበሩ። ለውጊያ የሚሆን እቅድ ከማውጣትና ዘመቻውን ከመምራት ጀምሮ እንደ አንድ ወታደር ረድፍ ይዞ በመዋጋት ሁሉ ነበሩበት። በሌላ በኩል ደግሞ ግንባሩ የሚተዳደርበትን የራስን መቻል መመሪያ እሳቸውም ይተገብሩት ነበር። ለምሳሌ ኢሳያስ የመኪና መካኒክ ናቸው። የተበላሹ መኪናዎችን በመጠገን ያንቀሳቅሳሉ ( የኢሳቱ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ይህንን በዐይኑ ማየቱን ጽፎ አንብበናል)።
ታዲያ አቶ ኢሳያስ እጀ ብርቱ አናጢ ጭምር ናቸው። በዚህ ሙያም ብዙ ቁሳቁሶችን ሰርተዋል። ከአስመራ የመጣልኝ መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ ኢሳያስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በቤታቸው ተቀብለው ባስተናገዱበት ወቅት ሁሉም እንግዶች የተቀመጡባቸውን ሶፋ፣ ወንበርና በርጩማ የሰሩት እራሳቸው ናቸው።