Page 1 of 1

ያራዳ ልጆች ወግ።ትህነግ እና የአሳ ነባሪ  ሆድ እንዲያጠግቡ ተገፍተው ከትግራይ የወጡ የድሃ ልጆች ጉዳይ።(ትንታጉ ዘወሎ)

Posted: 19 Apr 2019, 15:51
by Tintagu wolloye


የትህነግ መሪወች ልጆች ባህር የሚሻገሩት በአውሮፕላን፣ድሃው የትግራይ ልጅ በሰማጭ ጀልባ የመሆኑ ነገር አይገርምም።ያ ሁሉ ወጣት አሳነባሪ  በልቶት ትህነግ ጸጥ ማለቱስ የጤና ይመስልሃል?

“ለመለስ ኪነተኛው፣እስፖርተኛው፣ጎዳና ተዳዳሪው ሳይቀር እንባ አዋጣ ተብሎ ማልቀሱን ታሳቢ በማድረግ ነው ልበልህ?” የሞተው እኮ የድሃ ልጅ ብቻ ነው?

እና! አየጉድ ማለትም በባንክ ደብተርና በቦርሳ ሚዛን ልኬታ ይመዘን ተባለ እንዴ?አንዳንዱንኮ ነገር አይነግሩንም።

ወዳጀ የሞተው ከትህነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እአንዱ እስካልሆነ ድረስ ትግራይ ውስጥ ሃዘን ተቀመጡ፣አስተዛዝኑ አይባልም።

ዛሬስ እኔም የትህነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ባደረገኝ።

ምን ነካህ?ባለቀ ሰዓት?

ምነው ለቅሶአቸው ያምራል አላልክም አሁን?

እና!

ኑሮየስ አላማረም፣ባይሆን ለቅሶዬ እንዲያምር ነዋ መሆን የፈለግሁት!!

እነሱኮ በዝርፊያ መሰረት ላይ የተገነባው ደልቃቃ ኑሯቸው መቀጨቱ ስለሚያሳዝን ነው ቢለቀስላቸው።ጀብሎ ሆነህ ኖረህ ጀብሎ ሆነህ ለምትሞተው ለአንታ ማን ያዝናል?ተገላገለ ነው ያምባለው!

በእዚህ አይነት ድሆቹ የአሳ ነባሪ  ራት የሆኑት በእዚሁ መልክ “ተገላገሉ” በሚል ይሆን እንዴ  ትህነጎቹም ኢህአድጎቹም ጭጭ ያሉት?

ወዳጀ ይህ ከእኔ አፍ አልወጣም!