Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 35710
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 09 May 2024, 14:47

ከዚህ ቀደም አንድ ሰው ወይም አንድ ሕዝብ ችግር መፍታት የሚያቅተው ለምንድን ነው ብዬ ነበር ። መልሱ ይህ ነው ።

ችግር የምንለው ቃል አንድ የሆነ የአለም ምስል ማለት ነው ። ችግር የምንለው ነገር አንድ አለምን በትክክል የማየትና አንድ ተግባርን በትክክል ለማድረግ አለመቻል ነው ።
ይህ የሚሆነው አለምን (ሪያሊቲን) የሳልንበት ምስል ስሀተት ስለሆነ ነው ። ስለ አለም ያለን ባንጎላችን ውስጥ የሰራነው ፎቶ የተሳሳተ ስለሆነ ነው ። ስለዚህ ትክክልለኛ የሪያሊቲ ሞዴል ባይምሮአቸው ውስጥ የሌላቸው ሰዎች ትክክለኛ ሃሳብ የሌላቸው ናቸው።

ስለዚህ አንድን ችግር መፍታት ያቃተው ሰው ወይም አገር ስለ ችግሩ የተሳሳተ ሃሳብ (ምስል) ያለው ወይም ስለ ችግሩ ምንም ሃሳብ (ምስል) የሌላው ሲሆን ነው ። በሌላ አነጋገር የተሳሳተ አይምሮ ያለው ሰው ማለት ነው። አይምሮ ከምስል የተሰራ ሞዴል ነው ። በአንድ የተሳሳተ ሞዴል አማካይነት አንድን ትክክለኛ ተግባር መስራት አይቻልም።

አንድን ችግር ለመፍታት ትክክለኛ ሞዴልና አይምሮ፣ ትክክለኛ ሃሳብ ምን እንደ ሆነ ማግኘት አለብን ።

የቃላት ስራ ይህን ትክክለኛ ሃሳብ መፍጠር ነው ። ሃሳብ ምስል ነው ። ምስል የሚፈጠረው በቃላት ነው። ስለ አንደ ነገር ትክክለኛ ቃል ካገኘንለት ያ ነገር እንደ ተፈጠረ መቁጠር አለብን ። በመጀመሪያ ቃል ነበረ ። ቃልም አለም ሆነ፣ ቃል ተግባር ሆነ የምንለው ለዚህ ነው ።

ለምሳሌ ጎሳ ፣ ዘር፣ ዘውግ፣ ብሄር ፣ ወገን፣ ብሄረ ሰብ፣ ቡዲን ፣ ፓርቲ የሚባሉት ቃላት አገር መግምቢያ ቃላት አይደሉም! የአገር ሞዴል ፣ የፖለቲካ ስርዓት ሞዴል መስሪያ ቃላት አይደሉም ። አይምሮ የተሰራው በቃላት ነው! በተሳሳተ አይምሮ ችግር አይፈታም ።

በተቃራኔ አገር ማቆሚያ ቃላት ግለሰብ፣ ሕዝብ፣ መንግስት፣ ሕግ፣ ፍትህ፣ መብት፣ ነጻነት፣ ዴሞክራሲ፣ እኩልነት፣ እውነት፣ ትብብር፣ መረዳዳት፣ ሕብረት የመሳሰሉት ናቸው።

የኢትዮጵያ ችግር የሃሳብ ችግር ነው ። የኢትዮጵያ ችግር ያይምሮ ችግር ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 35710
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 11 May 2024, 15:19

ልሂቅ ታላቅ ማለት ነው። ልሂቃን ታላቆች ማለት ነው ። አንድ ሰው ልሂቅ የሚባለው ሊቅ ሲሆን ነው፤ በአንድ ነገር ሊቅ፣ የላቀ፣ ታላቅ ሲሆን ነው።

ኢትዮጵያዊ የሚባሉ ሕዝቦች ከድህነት እስከ ረሃብ፣ ከድንቁርና እስከ ጥንቆላ፣ ከፍርሃት እስከ ድብርት፣ ከጥላታ እስከ አስከፊ ጦርነት፣ ከልዩነት እስከ ዘር ማጥፋት፣ ከሌብነት እስከ አረመኔ ዝርፊያ፣ ከስንፍና እስከ ልመና፣ በእልፍ አአላፍ ችግሮች፣ መከራና ሰቆቃዎች ተደፍቀው፣ ማያ ዐይን አጥተው፣ ማሰቢያ አንጎል ፣ማስተዋያ አይምሮ ተነፍገው አላንዳች አላማና ብሄራዊ ፣ሕዝባዊ ፋይዳ እንደ ዱር እንሰሳ በሚታመሱባት አሳዛኝዋ ኢትዮጵያ እዚም እዛም ራሳቸውን ልሂቃን የሚሉ ሰዎችን ስንሰማ ማፈር አይደልም መሳቀቅ ይገባናል ።

በእውቀትና ጥበብ ዕጦት ሳቢያ በምንም ነገር ላይ ሊቅ (ኤክስፐርት) ያልሆኑ ፣ ምንም አይነት ችግር የማይፈቱ ፣ የሰርተፊኬት ታፔላ የተለጠፈላቸው ኢምሁራን ፣ ኢልሂቃን እውቀት አልባዎችና ጥበብ የለሾችን ልሂቃን እያልን ስለ ልህቀትና ታላቅነት በመስበክ እራሳችንን ባናታልል ይበልጥ በሌሎች ዘንድ ያስከብረናል ።

በኢትዮጵያ ሊሂቃን የሉም!

የኢትዮጵያ ችግር ደሞ ያ ነው!

Horus
Senior Member+
Posts: 35710
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 16 May 2024, 14:15

ሃተታ ቢበዛ በአህያ አይጫንም ። የጎሳ ትርክትና ተረት እንደ አገር ማደራጃ ሃሳብ ለ30 አመት ተወቅጦ ተወቅጦ ይህው ኢትዮጵያ የአለም መሳቂያ መሳለቂያ አድርጓታል ። የጎሳ ትርክትና ተረት አገር አያደራጅም፣ ኢኮኖሚ አይገነባም ፣ ከተማ አይቀይስም፣ ስልጣኔን አይጸንስም ። የጎሳን ትርክትና ተረት የተጋቱት ጎሳዎች እራሳቸው እየፈረሱ እየታመሱ ነው ።

በጎሳ ተረትና ትርክት ሰላም ለዘላለም አይመጣም ። የጎሳ ፖለቲካ የራሱን ጎሳ ይበላል።

የኢትዮጵያ ጥያቄ መፍትሄ ፍትህ ብቻ ነው ።

የሰላም ምንጭና መፍትሄ ፍትህ ብቻ ነው ።

የፍትህ መነሻና መድረሻ የሰው ልጅ ክቡርነትና የግለ ሰብ ልዕልና ብቻ ነው ።

ይህን እጅግ ቀላል ሃሳብ እስከ ሚገባቸው ድረስ የኢትዮጵያ ምሁር ተብዬ ደንቆሮች የጭለማ መታመሳቸውን ይቀጥላሉ ። አለምም በኢትዮጵያ መሳለቋን መሳቀቋን ትቀጥላልውች ።

Horus
Senior Member+
Posts: 35710
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 17 May 2024, 13:53

እንደ ገና፣ ቃላት መፍለጥና ሃረግ መሰንጠቅ እውቀት አይደለም ።

አንድ ግለሰብም ሆነ አንድ ሕዝብ፣ ብሎም አንድ አገር አንድ መንግስት የሚቆመው፣ ካልሆነም የሚወድቀው በ4 ምክንያቶች ነው

(1) እራሱን በትክክል ሲመራና ራሱን በትክክል ሲገዛ ነው ። እራሱን በራሱ የማይመራና የማይገዛ አይደለም የተሳሳተ የሌሎች አሽከርና ተገዥ ነው ።

(2) እራሱን በትክክል የሚከተልና በራሱ ላይ የራሱን ዲሲፕሊን የሚጠብቅ ራስ ታዛዥ ሲሆን ነው ። ዲሲፕሊን አልባ ራሱን በትክክል የማይከተል ደካማ ዉሸታም የሌሎች ደቂቅ ፣ ላቅመ ራስነት ያልደርሰ ሰው አገር ወይም መንግስት ማለት ነው ።

(3) እራሱን በራሱ በትክክል የሚቆጣጠር፣ የሚከታተል ፣ ስርዓታዊ ፣ ስኛታዊ ሲሆንና የሌሎችን ቁጥጥርና አለቃነት የማይፈልግ እራሱን ፖሊስ አድራጊ መሆን ነው ። እራሱን መቆጣጠር የማያውቅና የማይችል ስድና ሴራ አልባ ለስርዓታዊ ሕይወት ያልበቃ ሰው ፣ አገር ወይም መንግስት ነው።

(4) እራሱን በራሱ በትክክል ስህተቱን የሚያርም ከቁጥር 1 እስከ 4 ድረስ በንቃት ራሱን እና ተግባሩን የሚያውቅ ክህሎታዊ ፣ ጥበባዊ (intelligent) ሰው፣ ሕዝብ ፣ አገር ወይም መንግስት ሲሆን ነው ። የራሱን ስህተት የማያውቅ ፣ ስህተቱን የማረም ችሎታና አስተውሎት የሌለው ከንሰሳ የማይልቅ ሰው ወይም መንግስት ነው ።

ዛሬ ላይ በመንግስት ወምበር ላይ ቂጥጥ ብለው 120 ሚሊዮን ሕዝብ በራዕይ፣ ፐርፐዝና መሪነት እጦት እየታመሰ ስለ ልሂቅነትና አስተውሎት፣ ስለክህሎትና ሰው ሰራሽ ኢንተለጀንስ ሲቀባጥሩ ማሳቅ አይደለም ያሰቅቃል ።

ይህን ያስተዋልው ጥቁር አሜሪካዊ ወጣት አምባሳደር ነው 3 ሺ ዘመን የኖርነውን ሕዝብ እንዴት መኖር እንዳለብን ሌክቸር ሊያደርገን የደፈረው! እጅግ እጅግ ያሳስናል የወረድንበት ዝቅጠት ጥልቀት ።


Fiyameta
Senior Member
Posts: 17151
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Fiyameta » 26 May 2024, 03:36



Once upon a time there existed in the Balkans a country called Yugoslavia, comprised of 6 ethnicities with each having their own Kilils, namely Bosnia and Herzegovina, Croatia, Macedonia, Kosovo, Montenegro, Serbia and Slovenia, that were glued together by Ethnic Federalism, with the Serbs being the dominant ethnic group ruling the country with the help of world super power.

When tensions simmering under the surface in Yugoslavia erupted into major violence that threatened the peace and stability of Europe, dissolving the country became the only solution to end the violence and restore peace in the Balkan. The region has since been experiencing peace and stability after Yugoslavia dissolved in January of 1990 along ethnic fault lines.

The price of peace is cheaper than the price of war. But countries like Yugoslavia that believed war was the ultimate price of peace, they unfortunately had to dissolve in order to find peace. :|

Horus
Senior Member+
Posts: 35710
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 31 May 2024, 21:32

ፊያሜታ፣
ኢትዮጵያና ዩጎዝላቪያ እንደ ሰማይና ምድር የተለያዩ አገሮች ናቸው ። የሚያመሳስላቸው ንጉስ ኃይለ ስላሴና ማርሻል ቲቶ በገለልተኛ ውጭ ጉዳይ መስማማታቸው ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ችግሯን ተገንዝባ ለችግሯ መፍትሄ፣ በጦርነት ፣ በትግል ፣ በሰላም፣ በምክክር፣ በጸሎት ለመፍታት ሌት ተቀን እየለፉ ነው።

ኢትዮጵያ አገራዊ አጀንዳ ፣ብሄራዊ አላማ፣ ራዕይና የታላቅነት ሕልም ሰንቃ በመፋጨት ላይ ያለች፣ ግዙፍ ዳይናሚክ ፣ ታዳዲ ፣ ተለዋጭ አገር ናት!

የአንተ ኤርትራ ምን ላይ ነው ያለችው? ገና አገር ሳትሆን በመፍረስ ላይ ነች! እንደ አርክቲክ በረዶ ግግር ክምር ፍሪዝ አድርጋ የአንድ ስሁት ዲክታተር አምላኪና አሽከር ሁና ያለም መሳቂያ ቦታ ነች ። ግብዝ የራሱን ጉድፍ አያይም እንዲሉ ሕይወትክን ሙሉ ኢትዮጵያ እስክትወድቅ ጠብቀህ ወዚያኛው አለም ልታሸልብ ነው።

ኢትዮጵያ ምትባለዋ ባቡር ፌርማታ ከለቀቀች ሰንብቷል!

Fiyameta
Senior Member
Posts: 17151
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Fiyameta » 31 May 2024, 22:12

ሌላ ኢትዮጵያ የለችም።







ሌላ ኢትዮጵያ የለችም።







Last edited by Fiyameta on 01 Jun 2024, 02:20, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 35710
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 01 Jun 2024, 02:04

ፊያሜታ፣
ግዜህን ምን ላይ እንደ ምታጠፋ የሚነግረኝ ኤርትራ ያለባት ችግር ምን እንደ ሆነ ነው ።

Fiyameta
Senior Member
Posts: 17151
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Fiyameta » 01 Jun 2024, 02:18

Horus wrote:
01 Jun 2024, 02:04
ፊያሜታ፣
ግዜህን ምን ላይ እንደ ምታጠፋ የሚነግረኝ ኤርትራ ያለባት ችግር ምን እንደ ሆነ ነው ።
Despite my deeply held belief, and my professed Eritrean values and ideals, that all things are possible, I have learned that some people can be tamed but not domesticated. So, all things considered, taming the savage beasts has been my main preoccupation. :oops: :oops:


Horus
Senior Member+
Posts: 35710
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 20 Jun 2024, 01:08

FOUR ESSENTIAL ELEMENTS OF A GREAT NATION

Strong institutions and governance
Economic prosperity and opportunity
Social well-being and equality
Cultural vibrancy and global engagement

እነዚህን ያገኘኋቸው ጉግል ላይ ነው ። እነሱም በቀጥታ ለዘመናት የኢትዮጵያ አጀንዳ የምላቸው 4 አላማዎች ናቸው ። ገጽ 1 ተመልከቱ

Horus
Senior Member+
Posts: 35710
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 28 Jun 2024, 23:08

TALKING OF SWOT ANALYSIS - WHAT IS THE CURRENT SWOT ANALYSIS OF ETHIOPIA?

(1) WHAT ARE ETHIOPIA'S STRENGTHS?
(2) WHAT ARE ETHIOPIA'S WEAKNESSES?
(3) WHAT ARE ETHIOPIA'S OPPORTUNITIES?
(4) WHAT ARE THE THREATS ETHIOPIA IS FACING?

Horus
Senior Member+
Posts: 35710
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 02 Jul 2024, 22:17

ብሄረተኝነት የዝንጀሮዎች መቀመጫ ነው! ቤተልሔም ታፈሰ !


Dama
Member
Posts: 4367
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Dama » 02 Jul 2024, 22:47

Never knew someone can get high, get intoxicated and suffer hallucinations in a compelling absence of reality to force the thought

Horus
Senior Member+
Posts: 35710
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 19 Jul 2024, 16:24

ደንቆሮ የወያኔ ትግሬ ተገንጣዮች ያጨማለቁት ናዕት ያልቦካ ሞፎ የዋጠች ባለ ክልል ጎሳ ፖለቲከኛ ሁላ የዋጠችው እርጥብ ሊጥ ሆድዋን ጎርብጦ ውስጧን በጥንብጦ የራሷን ጎሳ እርስ በርስ ከፋፍሎ ፣ ከዚና ከዚያ ጎሳ አዋግቶ እያወደማት እንኳ መንቃት ያቃተው በድን ንኡስ ከበርቴ ገና ከዚህ የባሰ ውድመትና ውድቀት ይጠብቀዋል ። በጎሳ የተደራጀ ጎሳ ሁሉ እራሱ በአመጽና ሁከት ወዳሚ ነው ። ይህ ሳይንስ ነው ።

Dama
Member
Posts: 4367
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Dama » 19 Jul 2024, 16:34

Troubling philosophical views

Dama
Member
Posts: 4367
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Dama » 19 Jul 2024, 23:11

Right wrote:
01 Feb 2024, 16:06
የአገር መቆሚያ ብሄር ሳይሆን ግለሰብ ነው።
Absolutely correct. All the things Ethiopians are now fighting primitively for ethnicity, geography, materialism are nothing but the creation of human’s dysfunctional psychology. Ethnicity, colour, race, name etc are all labels that has no bearing on the true identity of individuals. The label Oromo can’t walk, talk or breathe.

Prof Horus- thank you for this very helpful educative analysis.
Prof of ilqit. Hope he doesn't live to see his apocalypse

Fiyameta
Senior Member
Posts: 17151
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Fiyameta » 20 Jul 2024, 19:07

What is Ethiopia? :| :|

Ethiopia is a Neo-colonial experiment whose aim is to keep Africans in a perpetual cycle of aid-dependency, poverty, illiteracy and never-ending wars. If this experience is successful, the process is to be replicated across Africa until every country in the continent is molded in the image of hungry Ethiopia.

The key to making this experiment a success however depends on the Neo-colonial powers' ability to pervert the Ethiopian people into becoming instrument of their own oppression, and willing participants in the Neo-colonial agenda of subjugating other Africans who seek to attain total freedom, dignity and justice, as has been the case during the last 75 years.





For instance, during a 1989 town hall meeting where Tegadalay Isaias Afewerki and his comrades met with the Eritrean Diaspora community, a man from Tigray attending the event asked "...Why has it taken you Eritreans 30 years to gain your independence? What is your problem?", to which Tegadaly Isaias, after a brief pause, responded with his trademark wit and grin on his face "... if the conflict was between Eritrea and successive Ethiopian regimes, it wouldn't have taken us 30 years to resolve, but it is the persistence of super-power politics in our region and their 30 years-long meddling in our own affairs that has prolonged the Eritrean struggle for independence."

Of course, the audience burst into laughter, knowing that you don't have to be rocket scientist to know that the world powers that prevented Eritrea from gaining its independence in the 1950s, were the same powers that were arming, feeding and supporting the servile Ethiopian regimes because they felt their Neo-colonial experiment was threatened by the emergence of Africans that never kneel down.

Following their failed experiment in 1991, the Neo-colonial powers unveiled a new experiment called Ethnic Federalism to keep Ethiopia divided along Ethnic lines, where a minority regime propped up by foreign aid and military aid can easily lord over the majority without facing any resistance. This experiment had worked very well during the 27 years the agame were in power in Ethiopia, but it was discovered later in 2018 that it couldn't be maintained, as major ethnic groups vying for supremacy found new ways to coming to power without waging an armed struggle.

Ethiopia will continue to be a Neo-colonial experiment until it is led by sane and level-headed people who are willing to make life sacrifices for the good of the people. But, for now, this is the real Ethiopia: A country of Lions led by Donkeys. :P



Horus
Senior Member+
Posts: 35710
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 21 Jul 2024, 03:46

ፊያሜታ፣
ኤርትራ ስትንቀዠቀዥ አጉል ተገንጥላ መላ ሕዝቧ ያውሮፓ መቀለጃን የአለም እስር ቤት jail birds የሆኑባት ያለም መሳለቂያ የአንድ ዲክታተር የግል kingdom city state ኢትዮጵያ ከምታክል ግዙፍና የተባረከች ምድር ጋር አነጻጽሬ ካንተ ጋር አፍ ብካፈት እራሴን የማቀለው!!

አንተ ግ ን ሕይወትክን ሁሉ ኢትዮጵያ ተሳድበህ ሞተህ ትረሳለህ ! እንኳን አንተን የሚያክል ዝምብ ጉንዳን ቀርቶ ያንተ ጌታ ግብጽን አምበርክካ ልክ ያስገባች አገር ናት ኢትዮጵያ! ያባይ ግድብ በመስከረም ያበቃል! ከዚያ በኋላ ግብጽ የተባለች ሙልፍጥ በኢትዮፕያ ላይ አፏን ትዘጋለች !

አንተ ገና ካውሮፓ እስር ቤቶች ውጣና ያኔ እንደ ሰው እናወራለን! ዛሬ አንተ የነጮች መቀለጃ ነህ ! አገር አልባ የስደት ልጅ!



Post Reply