Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11363
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

አገዛዙ የፋኖን ክንድ መቋቋም አቅቶት ከባድ ኪሳራን እየተከናነበ ባለበት ወቅት በሌላኛው ጎን ደግሞ ከሕወሓት ጋር ጦርነት በመጀመሩ በርካታ ወታደሮቹ ከድተው እንዲወጡ ምክኒያት ሆኗል።

Post by MINILIK SALSAWI » 02 Feb 2026, 10:02

አገዛዙ የፋኖን ክንድ መቋቋም አቅቶት ከባድ ኪሳራን እየተከናነበ ባለበት ወቅት በሌላኛው ጎን ደግሞ ከሕወሓት ጋር ጦርነት በመጀመሩ በርካታ ወታደሮቹ ከድተው እንዲወጡ ምክኒያት ሆኗል።

በራያ ግንባር ዛሬ ማርፈጃውን 7 ወታደሮች ፋኖን ሲቀላቀሉ በርካቶች ደግሞ ትጥቃቸውን ጥለው ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄዳቸው ታውቋል።

በተመሣሣይ ትናንት በስቲያ ከሁለት ጋንታ በላይ ወታደሮች ከቆቦ ከተማ ጠፍተው መውጣታቸውን ጣቢያችን መረብ ሚዲያ መዘገቡ አይዘነጋም።

ከፋኖ ጋር እየተካሄደ በሚገኘው ውጊያ አከርካሪው የተሰበረው መከላከያ ሰራዊቱ፡ ይህን በድል ሳይወጣ ሌላ አዲስ ጦርነት በመጀመሩ ለመማረክ እንኳን እድል እንደማያገኝ ስለተረዳ በተስፋ መቁረጥ ስሜት ተሞልቶ እየተበተነ ይገኛል።

ከአላማጣ ከተማ ሸሽተው ወደ ቆቦ ከተማ ከገቡት የአገዛዙ ወታደሮች መካከል "የብልፅግና ወንበር ለማስቀጠል አንሞትም" ያሉ ሰባት የአገዛዙ ወታደሮች ፋኖን ተቀላቅለዋል።

በሰሜን ምስራቅ ዕዝ 802ኛ ክ/ጦር 2ኛ ሬጅመንት 2ኛ ሻንበል አባላት  እና የ11ኛ ዕዝ 83ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ሬጅመንት የቃኝ  አባላት የነበሩ ሰባት ወታደሮች "ከወንድሞቻችን ጋር አንዋጋም፡ የብልፅግናን እድሜ ለማስቀጠል አንሞትም" በሚል ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክ/ጦርን ስለመቀላቀላቸው ነው የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ ያስታወቀው።

በተመሣሣይ ትናንት በስቲያ ከሁለት ጋንታ በላይ ወታደሮች ከቆቦ ከተማ መጥፋታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።


የሚኒሻ ስምሪት ኃላፊው  ከእነ አጃቢዎቹ ጎንደሬ በጋሻውን ክፍለ ጦርን ተቀላቀለ።

ኦህዴድ መራ*ሹ የብልፅግና ስርዓት አገልጋይ የነበሩ ወንበር አስጠባቂ  የሰራዊት አባላት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ  ንቅናቄ (አፋብን) ምስረታን ተከትሎ  እንደ እንቧይ ካብ እየፈ*ረሱ  የፋኖን ሀይሎች እየተቀላቀሉ  ይገኛሉ።

ዛሬ ጥር  25/2018 ዓ/ም የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ስምሪት ሀላፊ የሆነው አቶ  ጀጃው ንጉሴ ሁለት  አጃቢዎቹን በማስከተል 2 ክላሽ 1 ፋል መሳሪያ ከበርካታ ተተኳሾች ጋር በመያዝ "ከዚህ በኃላ  ከአለቆቼ  ተልዕኮ በመቀበል  የአማራን ህዝብ ማስጠፋት፣  ማስገደል ፣ ማፈናቀል ፣ማዘረፍ እና ማስጨፍጨፍ   ይብቃኝ በማለት  ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ ከተፈረደበት  የአማራ ህዝብ  ጎን ተሰልፌ  የብልፅግናን ስርዓት  ለማስወገድ  ስል  ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር  አሀድ የሆነውን ዳግማዊ ቴውድሮስ ብርጌድን ተቀላያለሁ" ብሏል ።

አቶ  ጀጃው ንጉሴና  አጃቢዎቹ  ወደ ፋኖ ሲቀላቀሉ የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ሊቀ ትጉሀን ስሙር መክብብ እና የክፍለ ጦሩ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ አዝመራው ካፒታል (ዶክተር ) እና ሌሎች  የክፍለ ጦሩ አመራሮችና አባላት በተገኙበት  የእንኳን ደህና መጣችሁ ደማቅ የጀግና  አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

አሁን ላይ  በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ውስጥ  ከፍተኛ  የሆነ ድንጋጤና አለመተማመን የተፈጠረ ሲሆን  የሚኒሻ አባላት   ስምሪት ሙሉ ለሙሉ  ቁሞ  ማን መቼ  ምን መሳሪያ  ይዞ  ይጠ*ፋል የሚል ስጋት አይሏል ።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ  ንቅናቄ በላይ ዕዝ የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!










MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11363
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: የፋኖ ኃይሎች ተጋድሎ፣ ድል እና የአውደ ግንባር ውሎዎች ልዩ አሁናዊ መረጃዎች እና ዘገባዎች

Post by MINILIK SALSAWI » 05 Feb 2026, 03:59

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በተሳተፉበት ውይይት ለዓመታት በታጣቂወች ታግተው የነበሩ ሴቶችን ማስለቀቅ ተችሏል።

በመተከል ቀጠና በለተያዬ ጊዜ በነበሩ አገዛዙ በፈጠራቸው ግጭቶች ምክንያት በርካታ አማራወች ሲፈናቀሉ፣ ሲጨፈጨፉ እና ሲታገቱ የቆዩ መሆኑ ይታወቃል። ሊቀመንበሩ በቀጠናው ካሉ ታጣቂወች ጋር ባደረጉት ውይይት በባለፉት ዓመታት በተከታታይ በተከሰቱ በእነዚህ ግጭቶች አጋጣሚ እስከ አራት ዓመታት ድረስ ታግተው የቆዩ አስር ያህክል ሴት ወጣቶችን ለማስለቀቅ ተችሏል።

በቀጠናው ከሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች ኃይሎች ጋር ቀናትን የወሰደ ውይይት ያደረጉት አርበኛ ዘመነ ካሴ እህቶቻችንን ከታገቱበት ቦታ ተረክበው ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው ሸኝተዋቸዋል።

በእለቱም አርበኛ ዘመነ ካሴ ተከታዩን መልዕክት አስተላፈዋል።

"እኛ አማራዎች ሰው ከሚፈጥረው የፖለቲካ ክፋትና ፀረ አማራ ርእዮት ጋር እንጅ ከሰው ልጆች ጋር ፀብ የለንም።ሰው ክቡር ነው። ርእዮታችን የሚቀዳውም ከዚህ የአስተሳሰብ ባህር ነው።እና ማንም ህዝብ ወገናችን ነው። (በዚህ ጉዳይ የጉምዝ ህዝብም)። ስለዚህ በመተከል በጉምዝና የአማራ ህዝብ መካከል፥ በሽናሻና የአማራ ህዝብ መካከል፥ በቤኒሻንጉልና የአማራ ህዝብ መካከል መገዳደልን ሊዘራ የሚሞክረውን የረጅም ጊዜ የጠላት አስተሳሰብ እየነቀልነው በቦታው ፍቅርንና አብሮነትን እየተከልን ነው።በዚህም የተነሳ ከድርጅቶች ጋር ጥሩ መቀራረብ ፈጥረናል።

በመሆኑም በተለያዬ ጊዜ በተነሱ ግጭቶች ምክንያት በጉምዝ ሃይሎች ከስራ ቦታቸው እየተያዙ እስከ አራት አመታት ታግተው የቆዩ አስር የአማራ ልጆችን ማስመለስ ችለናል። በዚህ ወቅት እህቶቻችን ተረክበን ወደ ቤተሰቦቻቸው እየላክን እንገኛለን።ይቀጥላል።"

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተለያዬ ማንነት ካላቸው ኃይሎች ጋር የሚያደርገውን የአጋርነት እና የትብብር ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በዚህ ረገድ ድርጅታችን በኢትዮጵያ ህልውና፣ በህዝቦች አብሮነት፣ እና በአገዛዙ የጋራ ጠላትነት ላይ የተመሰረቱ ተጨባጭ ስራወችን አጠናክሮ የሚሰራ ይሆናል።

የአማራ ህዝብ የሰላም፣ የአንድነት፣ የአብሮነት እሴቶችን በሚያጎለብት መንገድ በሁሉም ማዕዘናት ለሚኖረው ህዝባችን ደህንነት አስፈላጊዉን ሁሉ ማድረጋችን ይቀጥላል። https://t.me/merejainformation/16233






MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11363
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: የፋኖ ኃይሎች ተጋድሎ፣ ድል እና የአውደ ግንባር ውሎዎች ልዩ አሁናዊ መረጃዎች እና ዘገባዎች

Post by MINILIK SALSAWI » 06 Feb 2026, 01:11

በስቦ መምታት የውጊያ ታክቲክ የጠላት ብልፅግና ወታደርን ወሽመጥ በመቁረጥ ውጤታማ ድል ተመዘገበ!

በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ  ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ  አማራ ኮር 1   ባለሽርጡ ክፍለጦር ላይ ጥቅታ ለማድረስ ከጉቢሳ  ወደ ኮለቦ፣ ከጭሰ አባሊማ ወደ ሲልኮ፣ከጊራና ወደ ጉባ ፣ከመርሳ ወደ ሀብሩና ፋጂ የተንቀሳቀሰው የጠላትን ሀይል  በቀን 26/05/2018 ከኮለቦና ሩጋ ያለውን የጠላት ሀይል ስቦ በማስገባት መነዮ ቀሊና ላይ ምሽት 1:30 ላይ የጠላትን ሀይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ።

የባለሽርጡ ክፍለጦርን ሊያጠቃና የክፍለጦሩን ነባር ይዞታዎች ሊወር የመጣው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በአምስት አቅጣጫ ለማፈን ቢሞክርም የጠላትን የጥፋት እቅድ ቅዠት በማድረግ 50 ሙትና 78 ቁስለኛ በማድረግ ከትላንት  ከጥዋቱ 12:30 እስከ ዛሬ 27/05/2018 ዓ.ም በቆየ አውደ ውጊያ የጠላትን ከበባ ያለምንም መስዋዕትነት በአርበኛ እንድሪስ ጉደሌና በሌሎች በሳል የክፍለጦሩ ወታደራዊ ጠበብቶች  በመስበር በጥላት ላይ ከፍተኛ ስብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።

በዚህ አውደ ውጊያ የተበሳጨው የጠላት ሀይል በደቡብ ወሎ ዞን ተወለደሬ ወረዳ ሲልኮ እየተባለ በሚጠራው ቦታ 450 የሚደርሱ ወጣቶችን፣ አርሶ አደሮችን እና የቀን ሰራተኛዎችን በማፈን ስልጠና ሰልጥናችሁ አገራችሁን ትጠብቃላችሁ በሚል ሰበብ ወደ ማጓሪያ ቀጠና አስገብቶ  ፋኖን ማረኩ በሚል የሀሰት ዶክመንተሪ ዝግጂት ላይ ይገኛል።
በተያያዘም በሀይል ላፈናቸው ንፁሀን በየቤቱ እየገባ የግል ታጣቂ ግለሰቦችን መሳሪያ ለማስወረድ ድንገተኛ ፍተሻና ድብደባ እያካሄደ ይገኛል።

©በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ



Post Reply