-
የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በኮሮናቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር በነበራቸው ንክኪ ምክንያት በቀጣዮቹ ቀናት ራሳቸውን አግለው እንደሚቆዩ አስታወቁ።
-
ዋና ዳይሬክተሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት በኮሮናቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንደበራቸው ገልጸዋል።
ዶክተርቴድሮስ አድሃኖም የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የኮሮና ቫይረስ ሰንሰለቶችን በመስበር ነው ያሉ ብለዋል።
-
የአለም ጤና ድርጅትን የመሩ የመጀመሪያው አፍሪካዊ የሆኑት ዶክተር ቴድሮስ ‘’የጤና መመሪያዎችን ማክበራችን በጣም አስፈላጊ ነው” ብለዋል፡፡
በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የገለጹት ዶክተር ቴድሮስ ምንም አይነት ምልክት እንዳላሳዩና በዓለም የጤና ድርጅት መመሪያዎች አማካኝነት በቀጣዮቹ ቀናት ራሳቸውን አግለው እንደሚቆዩ ተናግረዋል።
-
ስራቸውን ከቤታቸው ሆነው እንደሚያከናውኑም በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ አመልክተዋል።
የ55 ዓመቱ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እ.አ.አ 2017 በተካሄደው የዓለም የጤና ድርጅት ባካሄደው 70ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ድርጅቱን ለአምስት ዓመት በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ መመረጣቸው የሚታወስ ነው።



