Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 02 Aug 2020, 11:28

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ረጅም ጊዜ ሊቆይ እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ
*************
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ረጅም ጊዜ ሊቆይ ስለሚችል አገሮች የሚሰጡት ደካማ ምላሽ ከፍተኛ መዘዝ ሊያስከትል እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት ቅዳሜ ዕለት አስጠንቅቋል።
የድርጅቱ ኮሚቴ ከስድስት ወር በፊት በሽታውን የዓለም ወረርሽኝ ብሎ ከፈረጀ ወዲህ ባካሄደው ግምገማ ላይ በሰጠው መግለጫ፣ በተለይ ቫይረሱ በአገሮች ላይ በሚያደርሰው ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጫና የተነሣ “የሚሰጠው ምላሽ ደካማነት” የከፋ መዘዝ ሊያመጣ ይችላል ብሏል።
ኮሚቴው ዓርብ ዕለት ያካሄደው ስብሰባ ወረርሽኙ ተከስቶ ዓለም አቀፍነቱ ከታወጀ እ.አ.አ ጥር 2020 ወዲህ አራተኛው ነው።
“የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19 ያለው አደጋ በጣም ከፍተኛ ነው ማለቱንም” መግለጫው አመልክቷል።
“ወረርሽኙ ረጅም ጊዜ ሊቆይ ስለሚችል በሽታውን ለመከላከል በዓለም አቀፍ ደረጃ ማኅበረሰቡ ዘላቂ የሆነ ጥረት ማድረግ እንደሚገባም” መግለጫው ጠቁሟል።
ኮሚቴው አገራት የተረጋገጡ የኮቪድ-19 መከላከለያ መድኃኒቶች እና ክትባቶች ማዘጋጀት እንዲችሉ የዓለም ጤና ድርጅት እገዛ እንዲያደርግ አሳስቧል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ወደ ስብሰባው ሲገቡ የወረርሽኙ ተፅዕኖ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ የሚችል ነው ማለታቸው ተዘግቧል።
በምዕተ ዓመት አንዴ የሚከሰት ይህን መሰል ወረርሽኝ ተፅዕኖ በሚቀጥሉት አሥርት ዓመታት ውስጥ የሚዘልቅ ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19 ከ680 ሺህ በላይ ሰዎችን ሕይወት የነጠቀ ሲሆን፣ ከ18 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ በበሽታው መያዛቸውን እስራኤልናሽናልኒውስ ዘግቧል።


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 02 Aug 2020, 13:41

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 707 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ28 ሰዎች ህይወት አልፏል።
በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 406 ሰዎች አገግመዋል።


https://mereja.com/amharic/v2/313269



MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 02 Aug 2020, 15:45

WORLDWIDE UPDATE

Coronavirus Cases: 18,152,049
Deaths : 690,953
Recovered: 11,413,385


Active Cases

Currently Infected Patients : 6,047,711
in Mild Condition : 5,981,814 (99%)
Serious or Critical : 65,897 (1%)


https://www.worldometers.info/coronavirus/#countries

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 03 Aug 2020, 04:23

South Sudan

》8 New cases confirmed in the last 24 hours.
》2,437 the accumulative figures
》1,195 recovered
》47 death from Coronavirus

COVID-19 latest updates


Global cases pass 18 million
US cases surpass 4.6 million
UK to roll out tests that work in 90 minutes


https://aje.io/kly9v


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 03 Aug 2020, 05:20

በአለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 18 ሚሊየን አለፈ

በዛሬው እለት የወጣ መረጃ እንደሚያሳየው በአለማችን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 18 ሚሊየን ተሻግሯል።
በሌላ በኩል 11 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ያገገሙ ሲሆን 6 መቶ 90 ሺህ ደግሞ በቫይረሱ ህይወታቸው ማለፉን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡
በአሜሪካ ቫይረሱ እንደአዲስ ማገርሸቱ ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ በከተማም ሆነ በገጠር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
ከነጩ ቤተመንግስት የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት 4 ነጥብ 68 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ155 ሺህ በላይ ሰዎች የሚሆኑት ደግሞ በሞት ተነጥቀዋል፡፡
የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት ሲባል የስሪላንካ ፕሬዝዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ የፓርላማው ምርጫ እንዲተላለፍ መወሰኑም ገልፀዋል፡፡
የሩስያ ጤና ሚኒስትር በሩስያ የበርካታ ሰዎች የምርመራ ውጤት አስደንጋጭነት ጠቅሰው በአገሪቱ 306 ሺህ በቫይረሱ ተይዘው 46 ሺህ ለሞት ተዳርገዋል ብለዋል፡፡
ብራዚል በበኩሏ አዳዲስ 25 ሺህ 800 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 5 መቶ 41 ሞት በማስመዝገብ አጠቃላይ ከ2 ነጥብ 73 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ከ94 ሺህ ሰዎች በላይ መሞታቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 03 Aug 2020, 05:57

የኮሮናቫይረስ ምርመራ ውጤት በ90 ደቂቃ

በዩናትድ ኪንግደም የኮሮናቫይረስን ምርመራ ውጤትን በ90 ደቂቃዎች ውስጥ የሚያሳውቅ መመርመሪያ ቁስ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደ ሥራ ሊገባ ነው። የዩኬ መንግሥት እንዳስታወቀው ይህ የምርመራ ዘዴ ኮቪድ-19ን ከሌሎች ወቅትን ጠብቀው ከሚመጡት ጉንፋን መሰል በሽታዎች ይለያል። እስካሁን በበርካታ የዓለማችን ክፍል የኮቪድ-19 የምርመራ ውጤቶች የሚወጡት በ24 ሰዓታት ውስጥ ነው።

https://bbc.in/2PlvLUs



ጋምቢያ ሶስት ሚኒስትሮቿ በኮሮና ቫይረስ ተጠቁ።

እንደ ጋምቢያ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት መግለጫ ሶስት የካቢኔው ሚኒስትሮች በኮቪድ 19 መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡
የፋይናንስ ሚኒስትሩ፣ የነዳጅና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ፣ የግብርና ሚኒስትሩ በኮሮና መጠቃታቸው ተረጋግጧል፡፡
ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው ባለፈው ሳምንት ምክትል ፕሬዝዳንታቸው ኢሳቱ ቱሬይ በኮሮና መጠቃታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ለይተዋል፡፡
የጋምቢያ መንግስት የፊት መሸፈኛ ማስኮችን ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች አስገዳጅ ያደረገ ሲሆን ማንኛውም ማህበራዊ ስብስቦችን እንደከለከለ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡በጋምቢያ እስካሁን 498 ሰዎች በኮሮና ሲጠቁ 9 ያህል ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 03 Aug 2020, 08:14



በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከግማሽ ሚሊየን አልፏል

በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከግማሽ ሚሊየን መብለጡ ተገለፀ፡፡
በሃገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 511 ሺህ 485 የደረሰ ሲሆን ÷8 ሺህ 366 ሰዎችም ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው፡፡
በዚህም ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን ግብፅ፣ናይጄሪያ እና ጋና ተከታዩን ደረጃ ይይዛሉ፡፡
በግብፅ 94 ሺህ 483 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 4 ሺህ 865 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
በናይጄሪያ ደግሞ 43 ሺህ 841 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን÷ 888 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ነው የተባለው፡፡
እንዲሁም በጋና 37 ሺህ14 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው 182 የሚሆኑት ለህልፈት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡
እንደ ወርልድ ኦ ሜትር መረጃም በአጠቃላይ በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ1 ሚሊየን የተጠጋ ሲሆን በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርም 20 ሺህ 350 ደርሷል፡፡

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 03 Aug 2020, 09:20

ኬንያዊቷ ነርስ ልጇን ከተገላገለች በኋላ በቫይረሱ ሕይወቷ አለፈ

ኬንያዊቷ ነርስ የመጀመሪያ ልጇን ከተገላገለች በኋላ በኮቪድ-19 ሕይወቷ ማለፉ ተገለፀ።
ነርሷ በቫይረሱ ተይዛ በሆስፒታል የሕክምና ክትትል እያደረገች ነበር።
የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ማሪያን አዎር አዱምቦ የተባለችው ነርስ፤ ባጋጠማት ህመም ሳቢያ በምዕራብ ናይሮቢ በሚገኝ ሆስፒታል ገብታ የነበረ ሲሆን መጀመሪያ ላይ ስትመረመር ከቫይረሱ ነፃ እንደነበረች ተረጋግጧል።
ከዚያም የጤና ሁኔታዋ ተባብሶ ወደ ሌላ ሆስፒታል ስትወሰድ፣ በቫይረሱ መያዟ ታውቋል።
ነፍሰጡሯ ነርስ ሕክምናዋን እየተከታተለች የመጀመሪያ ልጇን ከተገላገለች በኋላ ነበር ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የገባችው። ይሁን እንጂ ሕይወቷ ሊተርፍ አልቻለም።

https://bbc.in/3fwu5SN


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 03 Aug 2020, 09:35

ZAMBIA

Daily COVID19 update:in the last 24hrs,we recorded 233 new cases. Sadly, we also report 1 death (MHSRIP) from the Levy Centre, a patient with severe pneumonia. The cumulative number of cases now stands at 6,580 with 4,701 recoveries and 171 deaths (52 classified as COVID deaths)


COVID19 WEST AFRICA



LIBYA

Total covid19 cases in Libya as of yesterday 3837. Active cases 3131, recoveries 623 and deaths 83.
Yesterday 146 new cases and 3 deaths.



SENEGAL


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 03 Aug 2020, 10:14

Over 950,000 confirmed COVID19 cases on the African continent - with more than 610,000 recoveries & more than 20,000 deaths cumulatively.

View country figures & more with the WHO African Region COVID-19 Dashboard:

https://arcg.is/XvuSX




MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 03 Aug 2020, 10:36

የኮሮና ወረርሽኝ የዓለማችን ከባድ ፈተና ሆኖ ይቀጥላል፦ የዓለም ጤና ድርጅት

ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክትባት የማግኘት ተስፋ ቢኖርም ፍቱንነቱ የተረጋገጠ መፍትሔ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊገኝ እንደማችል እና በሽታው የዓለማችን ከባድ ፈተና ሆኖ ሊቀጥል እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
እስካሁኑ ሰዓት በዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ18 ሚሊዮን በላይ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ከ688 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም እና የድርጅቱ ተቋማት ኃላፊ ማይክ ሪያን፣ ሁሉም ሰው ኮሮናን ለመከላከል የተቀመጡትን የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግን፣ ርቀት መጠበቅን፣ እጅን በውኃ እና በሳሙና መታጠብን እንዲሁም መመርመርን የመሳሰሉትን የጤና መጠበቂያ መርሆዎች በአግባቡ እንዲተገብር አሳስበዋል።
"ለዓለም ሕዝብ እና መንግሥታት የማስተላልፈው መልእክት ግልጽ ነው፣" ያሉት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ የዓለም የአጋርነት ምልክት መሆን አለበት ብለዋል።


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 03 Aug 2020, 10:58

ሲንጋፖር ወደ ለይቶ ማቆያ የሚገቡትን በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ልትከታተል ነው

በመኖሪያ ቤታቸው እራሳቸውን ለ14 ቀናት ለይተው እንዲቆዩ የሚታዘዙ ሰዎችን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ መጠቀም እንደሚጀምር የሲንጋፖር መንግሥት አስታውቋል። እራሳቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ለይተው እንዲያቆዩ የሚታዘዙት ሰዎች ሁልጊዜም መሳሪያውን ይዘው እንዲንቀሳቀሱ ይገደዳሉ። ከዚህ ቀደም የጤና ባለስልጣናት ወደለይቶ ማቆያ የገቡ ሰዎችን እንቅስቃሴ የሚከታተሉት በስልክ ጥሪዎች ነበር።

https://bbc.in/31bXlJl


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 03 Aug 2020, 11:13

ደቡብ አፍሪካ - ራማፎሳ ለኮቪድ-19 የተመደበ በጀትን የሚመዘብሩ ግለሰቦችን አስጠነቀቁ

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ለኮሮናቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር የተመደበን የሕዝብ ሃብት በሚበዘብዙና “ጅቦች” ሲሉ የጠሯቸው ግለሰቦች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠነቀቁ።

ይህ የፕሬዝዳንቱ ማስጠንቀቂያ ትኩረቱን ያደረገው የመንግሥት ኃብትን በሚመዘብሩ ባለስልጣናት፣ በኮሮናቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎችና፣ የእርዳታ ምግብን በድብቅ የሚያከማቹ የአካባቢ አስተዳዳሪዎች ላይ ነው።

“በየእለቱ የዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ ካለው ቀውስ ለማትረፍ መጣር የጥንብ አንሳ ባህሪ ነው። ልክ የተጎዳውን ሰለባውን እንደሚከብ ጅብ መሆን ነው” ብለዋል ፕሬዝዳንት ራማፎሳ።

“ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ያለምንም ርህራሄ በዘረፋ መሰማራታቸውን አስተውለናል” ሲሉም አክለዋል።

https://bbc.in/2XoVdg1


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 03 Aug 2020, 11:23

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 03 Aug 2020, 11:34

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6907 የላብራቶሪ ምርመራ 583 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ26 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ 330 ሰዎች አገግመዋል።


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 03 Aug 2020, 12:11

በኖርዌይ የአንዲት መርከብ ተሳፋሪዎችና ሠራተኞች በኮሮናቫይረስ ተያዙ

በኖርዌይ የመዝናኛ መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ቢያንስ 40 መንገደኞችና ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ኤምኤስ ሮልስ አሙንድሰን በተባለችው መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች መንገደኞች ደግሞ ለይቶ ማቆያ ገብተው የምርመራ ውጤታቸውን እየተጠባበቁ እንደሆነ የመርከቧ ባለንብረት ተናግረዋል።

ሁርቲግሩትን የተባለ የኖርዌይ ድርጅት ንብረት የሆነችው መርከብ በትሮምሶ ወደብ ያረፈችው ባሳለፍነው አርብ ነበር።

በዚህም ሳቢያ ድርጅቱ ሁሉንም የመዝናኛ መርከቦቹን እንዳይንቀሳቀሱ አግዷል።

Read More https://www.bbc.com/amharic/53640749


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 03 Aug 2020, 14:18

በነሐሴ ወር የመጀመሪያዎቹ 2 ሳምንታት 200 ሺህ የኮሮና ቫይረስ ናሙናዎችን ለመመርመር ዝግጅት እንደተደረገ ጤና ሚንስትር ሊያ ታደሠ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡ የሀገሪቱን ምርመራ አቅምም በቀን አሁን ካለበት 11 ሺህ ወደ 15 ሺህ ለማሳደግ ታቅዷል፡፡ በሀገሪቱ በዚህ ሳምንት 3 ተጨማሪ መመርመሪያ ላቦራቶሪዎች ሥራ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል፡፡ አሁን ሥራ ላይ ያሉት 46 ላቦራቶሪዎች ብቻ ናቸው፡፡


Post Reply