Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11472
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Jun 2020, 04:55

በአንድ ጀንበር ከመኖሪያ ቤትነት ወደ ሆስፒታልነት፡፡
ከ17ቱ የቤተሰብ አባላት 11 የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡


17 የቤተሰብ አባላት በአንድ ጣሪያ ሥር ሕይወትን በተለመደው መልክ ይመራሉ፡፡ ምንም እንኳን የዚህ ታሪክ መቼት በህንድ ቢሆንም ነገ የኢትዮጵያውያን ዕጣ ፋንታ ላለመሆኑ ዋስትና የለምና ትምህርት እንዲሆን ልንነግራችሁ ወደድን፡፡ ሙኩል ጋርግ የ57 ዓመት አጎቱ ሚያዝያ 16/2012 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰማቸው የመጣው ትኩሳት ለቤተሰቡ ስጋት አልነበረም፡፡ በ48 ሰዓታት ውስጥ ከ17ቱ ሁለት ተጨማሪ የቤተሰብ አባላት ተመሳሳይ ሕመም ይስተዋልባቸው ጀመር፤ አሁንም ከአራት ወራት ጨቅላ እስከ 90 ዓመታት የዕድሜ ባለፀጋ አንድ ጣሪያ ሥር ያስጠለለው ቤት እውነታውን መቀበል ከብዶታል፡፡
ከሚጠበቁት የኮሮናቫይረስ ዋና ዋና ምልክቶች ተከታታይ ሳል እና ትኩሳት በታማሚዎቹ ላይ ቢስተዋልም እነጋርግ ግን ‘‘ጉንፋን ይሆናል እንጂ ኮሮና ነው’’ ብለው ማሰብ የፈለጉ አይመስሉም፡፡ ከዚህ ቀደም አምስትና ስድስት የቤተሰቡ አባላት በተመሳሳይ በጉንፋን ይጠቁ ስለነበር አሁንም ኮሮናቫይረስ ይሆናል ብለው አልተሸበሩም፡፡ ነገር ግን በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ተጨማሪ አምስት የቤተሰቡ አባላት የሚያሳዩት የሕመም ስሜት ቤተሰቡ ውስጥ አንዳች የስጋት ድባብ ፈጠረ፡፡
ነገሮች እንደተጠበቁት ቀላል አልሆኑም፡፡ በአጎት ተጀምሮ ከቤተሰቡ አባላት አስሩ የተሰማቸው የሕመም ስሜት ከተራ ጉንፋንነት አልፎ ኮሮና መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ አክስት መተንፈስ እስከመቸገር ደርሰው ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ፡፡ ህንድ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል በጣለችው የእንቅስቃሴ ዕገዳ ምክንያት በአንድ ጣሪያ ስር ሆነው የተለመደ ሕይወትን ከሚመሩት 17 የቤተሰብ አባላት አስራ አንዱ የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፡፡ በዚህ መልኩ በአንድ ጀንበር ቤቱ ወደ ሆስፒታልነት ተቀየረ፡፡
የጋርግ አጎት ገበያ አትክልት ተራ ወይም ግሮሰሪ በወጡበት ወቅት ለቫይረሱ ሳይጋለጡ እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡ አነጋጋሪው ጉዳይ ግን በተመሳሳይ መልኩ ከፍተኛ ቁጥር የቤተሰብ አባላት በአንድ ጣሪያ ስር መኖር አዲስ ባልሆነባት ህንድ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት በምን አልፎ ስኬታማ ይሆናል? የሚለው ነው፡፡ ለአብነት የነጋርግን ቤተሰብ ብንጠቅስ 17 ቤተሰብ የጋራ መጸዳጃ ቤት፣ ማዕድ ቤትና በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ እስከ ሦስት መኝታዎችን ያቀፈ ነው፡፡ እናም በእንደዚህ ዓይነት ቤተሰብ ውስጥ ጥንቃቄ የበለጠ ፈታኝ ይሆናል፡፡ የእነጋርግ ቤተሰብ ከሕክምና ባለሙያዎች ጋር በስልክ እና በስካይፒ ለረጅም ሰዓታት እየተነጋገሩ እየተረዳዱ ነው፡፡
ምንም እንኳን በቫይረሱ ከተያዙት ስድስቱ የልብ፣ የስኳር እና ግፊት ሕመም ቢኖርባቸውም በመጨረሻም ቤተሰቡ እየተረዳዳ ችግሩን ማለፍ ችሏል፡፡ የቤተሰብ ጠቃሚነት ለዚህ ወቅት ነውም ተብሎለታል፡፡
ከመጋቢት 16/2020 ዓ.ም አንስቶ ዜጎቿ በቤት እንዲቆዩ ዕገዳ የጣለችው ህንድ በተወሰነ ደረጃ እንቅስቃሴ የፈቀደችው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ነበር፡፡ ነገር ግን 40 በመቶ የሚሆኑት ህንዳውያን ሕይወትን የሚገፉት በተጨናነቀ ሁኔታ በአንድ ጣሪያ ስር ከሦስት እና አራት በላይ የቤተሰብ አባላት ሆነው ነው፡፡ ጥናቶች የሚያመላክቱትም በህንድ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከቀሪው ዓለም በተለየ መልኩ በስፋት የሚስተዋለው በቤተሰብ አባላት ውስጥ መሆኑን ነው፡፡ የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት የእንቅስቃሴ ዕገዳው በተጣለበት ወቅት አንድ የቤተሰቡ አባል በቫይረሱ ከተያዘ ቀሪው ተጠቂ መሆናቸውን ነው፡፡
ይህ ለኢትዮጵያውያን የሚያስተምረው አንድ ነገር አለ፡፡ ኢትዮጵያውያን ከቡና እስከ ማኅበር፣ ከጸሎት እስከ ዱአ፣ ከሐዘን እስከ ደስታ በተሳሰረ መስተጋብር ውስጥ ያሳልፋሉ፡፡ ይህ በቤት፣ በጎረቤት እና በመንደር ውስጥ አሁንም ያልቆመ ማኅበራዊ መስተጋብር ነው፡፡ የአንድ ግለሰብ በቫይረሱ መያዝ የቤተሰብ አባላት መጎዳት፤ የቤተሰብ ጉዳት የሰፈር ከዚያም የማኅበረሰብ እያለ ትናንት ካየናቸው ሀገራት ያልከፋ ጉዳት ላለመፈጠሩ እርግጠኞች አይደለንም፡፡
ጉዳዩን የከፋ የሚያደርገው ደግሞ የሀገሪቱ የምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴ ማገር በሆነው የአርሶ አደሩ ቀየ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት አናሳ ነው፡፡ በማኅበረሰቡ ዘንድ ያለው የግንዛቤ ደረጃም “የከተማ በሽታ ነው” ከሚል ያልዘለለ በመሆኑ ተጨማሪ ግንዛቤ እና ተደማሪ ጥረትን ይጠይቃል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ





MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11472
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Jun 2020, 08:30

በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት በስህተት ቫይረሱ የለብህም ከተባለ ከቀናት በኋላ የተነገረው ውጤት የሌላ ሰው መሆኑ ተገልጾ እሱን ጨምሮ ከእርሱ ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉ በርካታ ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸው ተነገረ።ወጣቱ ህመም ተሰምቶት ወደ የግል የጤና ማዕከል ሁለት ጊዜ ሄዶ እንደነበረ የመንዲ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ገመቹ ጉዲና ለቢቢሲ ተናግረዋል።

Read More : https://bbc.in/2MMvnNi




በትግራይ ክልል ኤርትራውያን ስደተኞችን ከሚያስተናግዱ 4 የስደተኛ መጠለያ ሰፈሮች አንዱ በሆነው አዲ ሐሩሽ ኮሮና ቫይረስ ገብቷል ተባለ




MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11472
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Jun 2020, 08:43

Somalia

> New cases confirmed today: 48
> Benadir:19
> Somaliland:17
> Puntland:8
> Galmudug:2
> Hirshabelle:2

> Male:34
> Female:14
> Recovery:19
> Death:1

Total confirmed cases: 2,416
Total recoveries: 489
Total deaths:85



MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11472
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Jun 2020, 09:08

Kenya -- 105 positive cases from a sample of 2,273 tested over the last 24 hours
which brings the total number of confirmed positive cases to 3,094

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11472
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Jun 2020, 09:28

'ኮሮናቫይረስ' ህጻናት በብዛት የተጠቀሙት የዓመቱ ቃል ነው ተባለ

የመዝገበ ቃላት ባለሙያዎች ኮሮናቫይረስ ሕጻናት አብዝተው የሚጠቀሙት የዓመቱ ቃል መሆኑን አስታወቁ፡፡
ባለሙያዎቹ ይህን ያሉት ለቢቢሲ የህጻናት የፈጠራ ጽሁፍ ውድድር የቀረቡ ከ130 ሺህ በላይ ታሪኮችን ከተነተኑ በኋላ ነው፡፡
የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕም ከሌሎች ግለሰቦች በላቀ በ134 ሺህ 709 ታሪኮች ላይ ተጠቅሰዋል፡፡

https://bbc.in/3cPCZt5

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11472
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Jun 2020, 09:51

ኮሮናቫይረስ ሁለቴ ሊይዘን ይችላል?

ስለ ኮሮናቫይረስ በርካታ ጥያቄዎች እየተሰነዘሩ ነው። ቫይረሱ አንዴ ከያዘን በኋላ በድጋሚ ሊይዘን ይችላል? በበሽታው አንዳንዶች ለምን ከሌሎች በባሰ ይጠቃሉ? ወረርሽኙ ሁሌም ክረምት ላይ ይከሰት ይሆን? ክትባት ቫይረሱን ለመከላከል ውጤታማ ይሆናል? በሽታውን እንዴት በቁጥጥር ስር አውለን ወደፊት እንቀጥላለን? በሽታውን የመከላከል አቅም አዳብረዋል የሚል ማረጋገጫ ያገኙ ሰዎች ወደ ሥራ ገበታቸው መመለስ ይችሉ ይሆን? ወዘተ. . .

ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል በሽታውን የመከላከል አቅም የማዳበር (ኢሚዩኒቲ) ጉዳይ ዋነኛው ቢሆንም አጥጋቢ ምላሽ የለውም።

ሰውነታችን ኮሮናቫይረስን የመከላከል አቅም እንዴት ያዳብራል?
በሽታን የመከላከል አቅም ሁለት ደረጃ አለው። የመጀመሪያው ሰውነት ወራሪ ነገር ሲገጥመው በመዋጋት የሚሰጠው ምላሽ ሲሆን፤ ‘ኢኔት ኢሚዩን ሪስፖንስ’ ይባላል።

በዚህ ወቅት ሰውነት ኬሚካል ያመነጫል። ነጭ የደም ሕዋሳትም ጉዳት የደረሰበትን ሕዋስ ያጠፋሉ።

ይህ ለኮሮናቫይረስ ብቻ ሳይሆን ለማንኛውን በሽታ ሰውነት የሚሰጠው ምላሽ ነው። ኮሮናቫይረስ እንዳይዘን የማድረግ አቅምም የለውም።

ሰውነታችን እንደ ኮሮናቫይረስ አይነት በሽታ ሲገጥመው የሚሰጠው የመከላከያ ምላሽ ‘አዳፕቲቭ ኢምዩን ሪስፖንስ’ ይባላል።

ቫይረሱ ላይ ያነጣጠሩ ፀረ እንግዳ አካላት (አንቲቦዲስ) የሚፈጠሩበት ሂደት ሲሆን፤ በቫይረሱ የተጠቁ ሕዋሳትን ለይቶ የሚያጠቃ ‘ቲ ሴል’ ያመነጫል።

ሰውነት ኮሮናቫይረስ ላይ ያነጣጠሩ ፀረ እንግዳ አካላት ለማመንጨት እስከ አስር ቀን እንደሚወስድበት ጥናቶች ያሳያሉ። በሽታው ክፉኛ ያጠቃቸው ሰዎች ጠንካራ የመከላከል አቅም ያዳብራሉ።

ይሄኛው በሽታን የመከላከል ምላሽ (አዳፕቲቭ ኢምዩን ሪስፖንስ) በጣም ጠንካራ ከሆነ በቀጣይ በበሽታው ላለመያዝ ይረዳል።

የኮቪድ-19 መጠነኛ ምልክት የታየባቸው ወይም ከነጭራሹ ምልክት ያላሳዩ ሰዎች፤ በሽታውን በበቂ ሁኔታ መከላከል የሚያስችል አቅም ስለማዳበራቸው የታወቀ ነገር የለም።

በሽታን የመከላከል አቅም ምን ያህል ጊዜ ይቆያል?

ሰውነታችን አንዳንድ በሽታዎችን ያስታውሳል አንዳንዶቹን ደግሞ ይረሳል።

ለምሳሴ ሰውነታችን ኩፍኝን ፈጽሞ አይረሳም፤ ስለዚህ በሕይወት ዘመናችን ከአንድ ጊዜ በላይ ኩፍኝ አይዘንም።

አንዳንድ በሽታዎችን ግን ሰውነታችን ይዘነጋቸዋል። እንደ ምሳሌ የሕጻናት መተንፈሻ አካል በሽታዎችን ማየት እንችላለን። ልጆች በተደጋጋሚ በእነዚህ በሽታዎች ይያዛሉ።

አዲሱ ኮሮናቫይረስ (Sars-CoV-2) መሰራጨት የጀመረው በቅርቡ ስለሆነ የሰው ልጅ ለምን ያህል ጊዜ በሽታውን የመከላክለ አቅም እንደሚያዳብር ገና አልታወቀም።

ግን የሌሎች ስድስት አይነት ኮሮናቫይረሶችን ባህሪ በማየት መገመት ይቻላል።

ከቫይረሱ አይነቶች አራቱ፤ እንደ ጉንፋን አይነት ምልክት ያላቸው ሲሆን፤ በሽታን የመከላከል አቅም የሚገኘውም ለአጭር ጊዜ ነው። ስለዚህም አንዳንዶች በዓመት ሁለቴ ሊያዙ ይችላሉ።

ከኮሮናቫይረስ አይነቶች ሁለቱ እጅግ አደገኛ ናቸው። ሳርስ ወይም ‘አክዩት ሪስፓይራቶሪ ሲንድረም’ እና መርስ ወይም ‘ሚድል ኢስት ሪስፓይራቶሪ ሲንድረም’ የሚያስከትሉት እኒህ ናቸው።

ለነዚህ በሽታዎች የሰው ልጆች ፀረ እንግዳ አካላት (አንቲቦዲስ) የሚያመርቱትም ከጥቂት ዓመታት በኋላ ነው።

የህክምና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ፖል ሀንተር እንደሚሉት፤ ጥያቄው መሆን ያለበት በሽታውን የመከላከል አቅም እናዳብራለን? የሚለው ሳይሆን በሽታውን የመከላከል አቅም ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል? የሚለው ነው ይላሉ።

“ለእድሜ ልክ የሚሆን በሽታ የመከላከል አቅም እንደማናዳብር እርግጥ ነው። የሳርስ ፀረ እንግዳ አካላት ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው እስከ ሁለት ዓመት የሚቆይ በሽታ የመከላከል አቅም ሊገነባ ይችላል።”

አንድ ሰው በበሽታው በድጋሚ ቢያዝም እንደ መጀመሪያው ጊዜ አይጠናበትም።

በሽታው ሁለቴ ይዞን ይሆን?

በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለቴ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች እንዳሉ ተዘግቧል።

አንዳንዶቹ ዳግመኛ በቫይረሱ የተያዙ ሲሆኑ፤ የተቀሩት ቫይረሱ በሰውነታቸው ውስጥ ተደብቆ ከጊዜ በኋላ ዳግመኛ በሽታው የተገኘባቸው ናቸው።

ከበሽታው እንዳገገሙ ከተነገራቸው ሰዎች መካከል ትክክለኛ ምርመራ ሳይደረግ ‘አገግማችኋል’ የተባሉ እንዳሉም ተመራማሪዎች ይስማማሉ።

የሰው ልጆች በሽታውን የመከላከል አቅም አዳብረው እንደሆነ ለማወቅ ሆነ ተብሎ በቫይረሱ ሁለቴ እንዲያዙ ባይደረግም፤ ዝንጀሮዎችን በሽታውን በማስያዝ ጥናት እየተካሄደ ነው።

ዝንጀሮዎቹ በሦስት ሳምንት ልዩነት ሁለቴ በበሽታው እንዲያዙ ተደርጎ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ የበሽታው ምልክት አልታየባቸውም።

‘አንቲቦዲስ’ ካለን በሽታውን መከላከል እንችላለን?

ስለዚህ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። አንዳንድ አገሮች በሽታውን የመከላከል አቅም አዳብረዋል ላሏቸው ሰዎች ማረጋገጫ ‘ፓስፖርት’ መስጠታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት የማይደግፈውም ለዚህ ነው።

ፀረ እንግዳ አካላት እንዳላቸው የተረጋገጠ ሰዎች ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ ያደረጉ አገሮች አሉ። በተለይም ለአረጋውያን እንክብካቤ ለሚሰጡና ለህክምና ባለሙያዎች ይህ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።

ሆኖም ግን በሁሉም ህሙማን ላይ ፀረ እንግዳ አካላት ቢገኝም ሁሉም አኩል አይደሉም። ኮሮናቫይረስን መግታት የሚችሉት ‘ኒውትራላይዚንግ አንቲቦዲስ’ የሚባሉት ናቸው።

ቻይና ውስጥ ከቫይረሱ ባገገሙ 175 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ የ30 በመቶው ‘ኒውትራላይዚንግ አንቲቦዲስ’ ዝቅተኛ መሆኑን አሳይቷል።

በተጨማሪም በ ‘አንቲቦዲስ’ ሰውነታችን ቢጠበቅም እንኳን፤ ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰው ልናስተላልፍ እንችላለን።

በሽታን የመከላከል አቅም ጠቃሚ ነው?

በሽታን የመከላከል አቅም ጉዳይ በኮቪድ-19 በተደጋጋሚ እንያዛለን? ከተያዝንስ በምን ያህል ጊዜ ልዩነት ነው? ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።

ሰዎች በተወሰነ ደረጃ ቢሆንም በሽታውን የመከላከል አቅም ካዳበሩ የበሽታውን አደገኛነት ይቀንሰዋል።

ስለ ሰውነታችን በሽታን የመከላከል አቅም ግንዛቤ ካዳበርን ማን ለበሽታው ተጋላጭ እንደሆነ፣ በሽታውን ሊያስተላልፍ የሚችለው ማን እንደሚሆን ለማወቅ ይረዳል። እንቅስቃሴ ላይ የተጣለውን ገደብ ለማላላትም ያግዛል።

በእርግጥ ለረዥም ጊዜ የሚዘልቅ በሽታን የመከላከል አቅም ማዳበር ከባድ ነው። ይህም ክትባት ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት ሊያከብደው ወይም ክትባቱ በምን ያህል ጊዜ ልዩነት መወሰድ አለበት የሚለውን ሊለውጠው ይችላል።

አንድ ሰው በበሽው ተይዞ አልያም ክትባት ካገኘ በኋላ ለምን ያህል ጊዜ የሚቆይ በሽታን የመከላከል አቅም ማዳበር ይችላል? ለሚለው ጥያቄ መልስ ሲገኝ የቫይረሱን ስርጭት መግታት የሚቻልበትንም መንገድ ያመላክታል።

ከላይ የተነሱት ጥያቄዎች ገና መልስ ያልተገኘላቸው ናቸው።

Source - BBC

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11472
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Jun 2020, 10:04

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 859 ደረሰ




MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11472
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Jun 2020, 10:41

CoronaVirus and Ethiopian Election

Ethiopian PM’s term extended as election delayed for virus

Ethiopia’s prime minister faces an extra year or more in office after lawmakers voted Wednesday to extend their mandates and hold the national election nine to 12 months after health authorities determine it’s safe.

Some in the opposition have objected to delaying the vote for the coronavirus as no one knows when the pandemic will end or whether the government of Prime Minister Abiy Ahmed will seek further postponements.

Wednesday’s decision is necessary “as long as COVID-19 continues to pose a health risk,” the Ethiopian News Agency quoted lawmakers with the upper house of parliament as saying. They approved the recommendation of the Constitutional Inquiry Committee that had sought a solution as mandates were set to end in October. The vote had been scheduled for August.

Read More : https://apnews.com/e202fdb50bcfcb5b44012dad56d51293


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11472
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Jun 2020, 10:49

በኮሮና ቫይረስ ከሚያዙት ሰማንያ በመቶ የሚሆኑት ምንም አይነት የበሽታውን ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ

ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም

በዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት መሰረት ሰማንያ በመቶ የሚሆኑት የኮሮና ቫይረስ ቢኖርባቸውም እንኳን የበሽታውን ምልክቶች ላያሳዩ ይችላሉ። ይህ ማለት ግን ቫይረሱን አያስተላልፉም ማለት አይደለም፡፡ ምልክቶቹን ባለማሳየታቸው በረካታ ሰዎችን የማግኘትና ወረርሽኙን የማስፋፋት እድላቸው ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሽታው ቀሪውን ሃያ በመቶ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ አምስት በመቶ የሚሆኑት የጽኑ ህሙማን ክትትል ያስፈልጋቸዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወደ ሃገራችን ከገባበት ከመጋቢት 04 /2012 ዓ.ም ጀምሮ ዕለት-በዕለት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ከሁለት ሺህ አምስት መቶ (2500) በላይ ደርሰናል፡፡ በምናደርጋቸው መዘናጋቶች ቀላል የማይባል ክቡር የሰው ልጅ ህይወትም እያለፈ እንደሚገኝም ልብ ልንል ይገባል፡፡
በድንገት ህይወታቸው የሚያልፉ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ሲደረግላቸው በውስጣቸው ቫይረሱ እንዳለባቸው ይገለፃል ፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የበርካታ ሰዎች ጥያቄ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡በዚህም ዙሪያ በኮቪድ-19 አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የክሊኒካል ኬዝ-ቲም ዩኒት አስተባባሪ ዶክተር ሚኪያስ ተፈሪ ይህ ሊሆንበት የሚችልባቸውን ምክንያቶች ሲዘረዝሩ፤ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ በውስጣቸው እያለባቸው የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነታቸው ዝቅተኛ ሆኖ ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል፤ ሌሎቹ የኮሮና ቫይረስ በውስጣቸው ኖሮባቸው ምልክቶችን ሳያሳዩ በድንገት በሌሎች የጤና ችግሮች ምክንያት ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል ፣ በምርመራ ወቅት የሚወሰደው ናሙና እስኪደርስ ድረስ ቫይረሱ እንዳለባቸው ሳይታወቅ ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል ከዚህ በተጨማሪ በአጭር ጊዜ ውስጥ ድንገተኛ በሆነ ህመም መባባስ ምክንያት በበሽታው ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል ብለዋል፡፡

በጤና ሚኒስቴር በተላለፈው መሰረት ህይወቱ የሚያልፍ ማንኛውም ሰው አስክሬኑ እንዲመረመር እየተደረገ ይገኛል፡፡የአስክሬን ምርመራ በሚደረግበት ግዜ የኮሮና ቫይረስ እንዳለበት ከታወቀ ወረርሽኙ በቀላሉ ወደ ህበረተሰቡ እንዳይዛመት ያግዛል፡፡በአስክሬን እጥበት፤በግነዛ፤በስረዓተ-ቀብር እና በመሳሰሉት ስራዎች ላይ በቀጥታ ተሳታፊ የሚሆኑ ሰዎች በቀላሉ በቫይረሱ የመያዝ እድል ይኖራቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ደግሞ በቀጥታ ከማሕበረሰቡ ጋር ስለሚቀላቀሉ ወረርሽኙ የመስፋፋት እድሉን ያባብሰዋል ብለዋል ዶክተር ሚኪያስ ፡፡

ይህ መደረጉ በቤት ለቤት እና በጤና ተቋማት በሚደረገው ምርመራና ልየታ ወቅት ምልክቱን ስላላሳዩ ያላገኘናቸውን ሰዎችም ጭምር ወረርሽኙ ከዚህም በባሰ ሁኔታ ሳይሰፋ ለመለየት እያገዘ ይገኛል ፡፡

ስለዚህ አሁንም ህብረተሰቡ እጁን በንፁህ ውሃና ሳሙና በተደጋጋሚ በመታጠብ፤የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም ፤ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለንን አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዲሁም ግዴታ ካልሆነ በስተቀር ከቤት ባለመውጣት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመቆጠጠር ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋፅኦ መወጣት ይኖርብናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ከምልክቶቹ አንዱን ቢሰማዎት በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን [email protected] በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ጤና ሚኒስቴር
Please wait, video is loading...

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11472
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Jun 2020, 11:04

INDIA: In last 24 hours, Delhi has tested 5,464 samples for coronavirus and reported 1,366 new cases.For the first time since coronavirus outbreak, number of recovered patients exceeded the number of active cases. India's virus epicenter Mumbai has now 'reported' more coronavirus cases than China's virus epicenter Wuhan.

Brazil reports 32,091 new cases of coronavirus and 1,272 new deaths.
Total of 739,503 cases and 38,406 deaths

Germany extends warning against international travel until August 31.

Indonesia reports 1,241 new cases of coronavirus, 34,316 cases in total.
Indonesia's largest daily increase by far.

Bangladesh reports 3,190 new cases of coronavirus, 74,865 cases in total.
Bangladesh's largest daily increase so far.

10 Most COVID19 Deaths in Asia,

Iran 8,425
India 7,745
Turkey 4,729
China 4,634
Pakistan 2,255
Indonesia 1,959
Philippines 1,027
Bangladesh 1,012
Japan 916
Saudi Arabia 783

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11472
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Jun 2020, 11:07

Here are the countries ranking by COVID19 safest, according to the Deep Knowledge Group study :

1 Switzerland
2 Germany
3 Israel
4 Singapore
5 Japan
6 Austria
7 China
8 Australia
9 New Zealand
10 South Korea

The study is based on 130 quantitative and qualitative parameters as well as over 11,400 data points in categories such as quarantine efficiency, monitoring and detection, health readiness and government efficiency.



https://www.forbes.com/sites/johnkoetsi ... 82d13268c5

Switzerland is the safest country in the world right now for COVID-19. South Sudan is, according to a massive 250-page report, the most dangerous nation.

https://www.dkv.global/covid-safety-[deleted] ... 00-regions



MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11472
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Jun 2020, 11:44

COVID-19 updates:

• Africa’s cases surpass 200,000
• India reports nearly 10,000 cases in one day
• Pangolin removed from list of traditional medicines in China


https://aje.io/hq2dm



WHO says Pakistan should reimpose lockdown to curb COVID-19 https://aje.io/5ltal

The UK is predicted to see the biggest economic downturn out of all OECD countries amid COVID-19 https://aje.io/mpgc3

The Olympic Games, which have been postponed for a year due to the coronavirus pandemic, will not be done with grand splendour says CEO of Tokyo 2020 https://aje.io/t7vkb


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11472
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Coronavirus International updates

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Jun 2020, 12:01

Please wait, video is loading...

Post Reply