Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4656
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: A few takes from President Isaias' interview.

Post by Meleket » 24 Jul 2025, 09:24

እኔ እቀድማለሁ እኔ እበልጣለሁ የሚለው ‘ሜንታሊቲ’ ጥቅም የለውም። ትግርኛ ሆነ አማርኛ ከግዕዝ የተወለዱ መንትዮች ግን ደግሞ የትግረ ታናሾች ናቸው ማለቱ፡ ለሓቅ የቀረበ ስለሆነ፡ እንዲያ ማለቱ ሳይሻል አይቀርም። ለምን ብትል ከትግርኛም ሆነ ከአማርኛ ይልቅ ለጥንታዊው የቀጠናችን ቋንቋ ለግዕዝ የትግረ ቋንቋ ነው የሚቀርበው።

ራቢንን ለምን ገደሉ? ዓብድልቃድር ከቢሬን ለምን ገደሉ? ጀነራል ሓዬሎምን ለምን ገደሉ? ኢንጅነር ስመኘውን ለምን ገደሉ? ሓጫሉን ለምን ገደሉ? ጀነራል አሳምነውን ለምን ገደሉ? ጀነራል ሰዓረን ለምን ገደሉ? ጀነራል ገዛኢን ለምን ገደሉ? ዶክተር ኣምባቸውን ለምን ገደሉ? ወዘተን ለምን ገደሉ? ወልደአብ ወልደማርያምን ለምን ለመግደል ሞከሩ? አስፍሃ ወልደሚካኤልን ለምን ለመግደል ሞከሩ? ጀነራል ስምዖን ገብረድንግልን ለምን ለመግደል ሞከሩ? ጀነራል ስብሓት ኤፍሬምን ለምን ለመግደል ሞከሩ? ወዘተ ማለት ምንም ፋይዳ የለውም። እነዚህ ሰዎች ከመገደላቸው በፊት ‘ካልጠረጠሩ ተመነጠሩ’ የሚለውን ፈሊጥ በማንገብ፡ መጠንቀቅ ነው ፋይዳ ያለውና የነበረው። እንዲህ የሚገድሉና የሚያስገድሉ የዞረባቸው ቦተሊከኞች፡ በሃሳብ ልዕልና የማያምኑ፡ በሰለጠነ መንገድ መወያየት የሚያንገሸግሻቸው፡ እኛ ብቻ ነን ትክክል ብለው የሚያስቡ፡ የወንድማቸውን የተለየ ድምጽ ለመስማት ጀሮ የሌላቸው፡ እኔን ብቻ ይድላኝ የሚሉ አካላት ሊሆኑ ይችላሉ። ማንም ተራ ቂም የቋጠረ ሰውም ይህን እኩይ ተግባር ማከናወንም ይችላል።

ቁምነገሩ ወደቦቻችንን ማልማትና ለአካባቢውና ለቀጠናው ንግድ ማእከል ማድረግ ላይ ነው። በዚህ ጉዳይ ያንተ ምልከታ ምንድን ነው? ወደቦቻችን እንዳለፉት ዓመታት ሆነው እንዲቀጥሉ ነውን የምትሻው? ዘሜ Zmeselo ‘ዓቢሰብ” ወዲ ዓበይቲ!
Zmeselo wrote:
24 Jul 2025, 08:30
1. Since tgrgna is older than amargna, you should advise them to learn it instead.

2. I don't know.

If they're ሓደ ልቢ ሓደ ህዝቢ, why did they kill Rabin?


Meleket wrote:
24 Jul 2025, 07:13
ይህን የመወያያ መድረክ ላበረከተልን ለታላቁ የዲሞክራሲና ሃሳብን በነጻ የመግለጽ ኣርበኛ፡ ለኤልያስ ክፍሌ ክብር፡ እንዲሁም ለመጪዉ የአፍሪካ ቀንድ “ሪጅናል ኢንተገረሽን’ እንደ ኣንድ የመግባብያ ቋንቋነት፡ ከምእራባዉያን ቋንቋዎች ይልቅ ኣማርኛ ያገለግል ይሆናል ብለን በማሰብ፡ በተጨማሪም ከጐረቤቶቻችን ካማሮች ጋርም ስትጣመድ ቋንቋዉን አውቀሀው ብትቆይ ሊያገለግልህ ይችላል በማለት ነው።

እስራኤሎች እንደ ኤርትራዉያን ሃገራቸውን በሚመለከት ጉዳይ “ሓደ ልቢ ሓደ ህዝቢ” የሚለውን አመለካከት ኣያምኑበም እያልክ ነውን? ወዳጃችን ዘሜ Zmeselo ‘ዓቢሰብ’ ወዲ ዓበይቲ! ኢራን ከራሻ ጋር ተማክራ ዩራኒየም ኣከማችታ፡ ኒውክሌር ብትሰራ፡ ራሻን ላለማስቀየም፡ “ሓላል ይግበረላ” ብለው ዝም ያላሉ በለና ኣብዛኞቹን እስራኤሎች! እስራኤል ለብሄራዊ ጥቅሜ ይረዳል ካለች ኢሳያስን ከብርቱ ህመሙ ከሰመመኑም አንቅታ ታክማለች፡ የአካባቢዉን ወደቦችም በቀጥታ ይሁን እንደተባለው በቀኝ ኣዙር ከየሃገራቱ ጋር አበልጽጋ ልትጠቀምበት ታስብ ይሆናል። ይህ ደግሞ ምንም ችግር የለውም። የኢሜሬት መሪዎች ሆኑ የሌላ ሃገር መሪዎች ያላቸውን ጸጋ ኣስተባብረው ለህዝባቸው የተሻለ ህይወት ለመፍጠር ሲፍጨረጨሩ ይታያል። ቻይናስ ብትሆን በቢልዮኖች የሚቆጠር መዋእለ ንዋይ በቀጠናው ሃገራት (በኤርትራም ጭምር) ኣፍስሳ 'ኢምፓዬር' ለመመስረት ኣይደለም እንዴ እየጣረች ያለችው? ሁሉም ለጥቅሙ እንዲያ ነው የሚያደርገው። እኛ ሃገራችን ኤርትራ የወደብ ጸጋዋን የባህር ጸጋዋን ለምን ባግባቡ ኣልምታ የቀጠናዉን ንግድ ማእከልና ኣካል በማድረግ አልተጠቀመችበትም? የቀይባህር ዘበኝነት ብቻ ምን ትርጉም ኣለው? ልዑላዊ የባህር ጸጋዋን በሙሉ ኣበልጽጋና ኣስፋፍታ ትጠቀምበት ሃገራችን ኤርትራ ነው እያልን ያለነው ወዳጃችን ዘሜ Zmeselo ‘ዓቢሰብ’ ወዲ ዓበይቲ! ምን እስኪሆን ነው ቆማ የምትጠብቀው፡ ኣቦ ወደቦች ኣካባቢ እድገት ማዬት የሚሹ በሪጅናል ኢንተገሬሽን የሚያምኑ ዜጉች ብዙዎች ናቸውና፡ ጉዳዩ በትኩረት ቢታሰብበት መልካም ነው።
Zmeselo wrote:
24 Jul 2025, 06:01
Why are you speaking to me in Amharic?

Do you think Rabin & the Likudniks are the same, for instance?


Meleket wrote:
24 Jul 2025, 05:39
“የኤሚሬትሱ Sheikh Zaid (1918-2004) የነበሩ መልካም ሃሳብ የነበራቸው መሪ ናቸው። አሁን ያሉት ግን እኩይ የመስፋፋት ሃሳብ ነው ያላቸው!” እዬተባለው ነው። እስራኤሎች 1993 ላይ መልካም ሃሳብ ነበራቸው አሁን ግን የመስፋፋት ሃሳብ ኣላቸው ማለት ይቻላልን? እነ ዘሜ Zmeselo ዓቢሰብ ወዲ ዓበይቲ እስቲ ትንሽ ማብራርያ። በነገራችን ላይ እታች የጠቀስነው ጽሑፍ ይዞታዉ ሆነ እውነትነቱ ጸሓፊዎችን ነው የሚመለከተው።
https://www.facebook.com/photo.php?fbid ... 6768206925


Eritrean Press
December 11, 2014 •
When The Israelis Came To The Rescue Of President Isaias Afewerki

Photo: Isaias in Israeli hospital in 1993

On January 7, 1993, just a few months before Eritrea's referendum for independence were to take place, Isaias went into a coma and almost lost his life when he was stricken with a severe case of cerebral malaria. He was immediately flown by the US Air Force to Israel for treatment.

Mebrahtu Tewelde
"By U.S Air Force?" where did you get this news? he went by the U.N Air plane. At that time the late U.N secretary Butros Kali was in visit in Eritrea. when he know that the president is in critical condition,he late his plane to take him to Isreal

Zmeselo wrote:
23 Jul 2025, 14:47
....
• President Isaias extols the wise leadership of the late President of the Emirates, Sheikh Zaid. He slams the country’s current destabilizing role in the region, in coordination with Israel, France and the United States.
....

Post Reply