Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum


almaze
Member+
Posts: 7665
Joined: 15 Dec 2013, 03:38

Re: የመደመር ትዝታዋች From Eritreans' perspectives.

Post by almaze » 11 Oct 2024, 21:04


Meleket
Member
Posts: 4614
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የመደመር ትዝታዋች From Eritreans' perspectives.

Post by Meleket » 12 Oct 2024, 03:38

የያኔውን ፍጻሜ እንዲህ ቋጥረነዋል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
Meleket wrote:
19 Jun 2018, 03:00
ውዳሴ ዘአብይ

ያ ዲያብሎስ ቀንቶት እኛኑ አጣልቶ፣
ኢትዮጵያና ኤርትራን እርስበርስ አባልቶ፣
ሁሌ ጠዋት ማታ ሲያሰማን ቀረርቶ፣
ምስኪኖች ሲያነቡ ከበሮ ሊደልቅ፣
ሰብአዊ ፍጡርን እንዲሁ ሲያሳቅቅ፣
ስንት ንጹሓንን በእስር ሲያማቅቅ፣
ምህረት ሰላም ፍቅርን ከኛ ዘንድ ሊያርቅ፣
ህዝቦች ደም ሲያነቡ እሱ ግን ሲሳለቅ፣
ብዙሃን ታርዘው እርሱ ሲሞላቀቅ፣
ሳይታክት መስራቱን እኛኑ ሊያናቁት፣
ጉዳዮች ጠማዞ ወስልቶ ሲተብት፣
ሊዘራ ክፍፍል ሁሌ ሲንገታገት፣
የሱን ተንኮል ደባ በውኑ ያጤኑት፣
ወጣቱ አስተዋዩ የኛው ትውልድ ወካይ፣
ብልሁ መካሪ አንደበተ አማላይ፣
በሓቅ የሚመሩት የትህትና አገልጋይ፣
ያነገቡት ራእይ መርሁ መደመር፣
በቅንነት ገስጋሽ በቃል ሆነ ተግባር፣
ሀሰተኛን ሁላ በቃላቸው ዘራይ፣
ከጎናቸው አለን ከኚህ ወጣት ጠቅላይ!

የክፍሉን ስራ የቤቱንም ስራ አሳይመንቱን ሁሉ፣
አጣጥሞ ሚሰራ ተግባሩን ከቃሉ፣
እንደርስዎ አላየንም በጦብያ በሙሉ።
እግዜር ከርስዎ ጋር ነው እንመሰክራለን፣
እድሜ ለኤልያስ እንጽፈዋለን፣
አይናችን እያየ መች ዝም እንላለን?

ቢወራጭ ቢወራጭ የዲያብሎስ መንጋ፣
እርሶ ይነዱታል በእውነት አለንጋ፣
ሽዎች ንጹሃንን ከሲኦል መንጋጋ፣
ሚንከራተቱትን ፍትህን ፍለጋ፣
ልብ አሳርፈዋል በቆላም በደጋ።

ይህንን ታዝበን ስንል አብይ በርቱ፣
ሓቅን ስለያዙ ሐሰትን ሲረቱ፣
የምህረት ተግባርዎ ቀንም ሆነ ማታ፣
ርቱዕ አንደበትዎ ሚሰጠን እርካታ፣
ሰላምን ሰባኪ ከጦርነት ፈንታ፣
ዘመንዎ እንደሚሆን የሰላም የእርጋታ፣
በሁላችን ዘንድም ስለዘሩ ደስታ፣
ህዝብን አክብረዋል ያክብርዎት ጌታ።

ትልቅ ጆሮ ሰጥተው ለህዝቡ ስሞታ፣
ትዕግስትን አንግበው ለህዝብ አቤቱታ፣
እውነተኛ መልስን በተርታ በተርታ፣
ለሚልዮኑ ህዝብ ስለሆኑ ዋልታ፣
ስንል እንደኖርነው ናና ማራናታ፣
አንድዬ ራሱ ነው የስዎ መከታ፣
አያሳፍርዎም ያ የሚያምኑት ጌታ።

አንዱ አንዱን እንዲያየው ሁልግዜ የጎሪጥ፣
ሌሎችን የማሞኝ እኔ ብቻ ነኝ ብልጥ፣
ሲል እንዳልነበረ ዲያብሎስ ያ ቆሪጥ፣
ሁሉንም አስማሚ እውነቱን በመግለጥ፣
በየዋህ አንደበት ትዕቢትን በማቅለጥ፣
ዘመን እንዲያበቃ ዘመነ መርመጥመጥ፣
ምህረት የሰብኩ አልፈው እሳት ረመጥ፣
የመደመር መርህ ከሁሉ የሚበልጥ፣
ምንኛ ደስ ይላል ይህ የእርስዎ ፈሊጥ።

እኒያ ደም መጣጮች ምነው ወሬ አበዙ፣
እኒያ የቀን ጅቦች ምነው ወሬ አበዙ፣
ዛሬም አሉባልታን እንዲሁ ሚነዙ፣
ጉዳይ አወሳስበው ነገር ሊያጠነዙ፣
ግጭቶች ለመፍጠር ከሚቅበዘበዙ፣
ለህግ የበላይነት ምናለ ቢገዙ?
ልኩን ነገሯቸው ነገር ሳያንዛዙ፣
እንዲህ የእርሶ ዓይነቶች ተደምረው ይብዙ።

viewtopic.php?f=17&t=159593
Meleket wrote:
27 Jun 2018, 09:59
በአጤዎች ዘመን በነበረ አገጣጠም ስልት የተገጠመ ሰሞንኛ ኤርትራዊ ግጥም
የሚከተለው ግጥም በነ አጤ ቴዎድሮስና አጤ ምኒልክ ዘመን የአገጣጠም ስልት ስለ ደጉ ጠቅላይ አብይ የተገጠሙ ስንኞች ይገኙበታል፣ “ምኒልክ ተነስቶ ባያነሳ ጋሻ”፣ በሚለው ቅላጼ “አብይ ተነስቶ ባይሰብክ ፍቅር” እያላችሁ፤ እንዲሁም “መቅደላ ተራራ ጩሀት በረከተ” በሚለው አነባበብ “ቦሌ ኤርፖርት ላይ እልልታው ቀለጠ፣” እያላችሁ እስቲ አንብቡት። እይታችንንም አክለንበታል፣ ግጥምና ሓቅን አፍቃሪዎች ኮምኩሙ!

አብይ ተነስቶ ባይሰብክ ፍቅር፣
የአበሻ ዕጣ ሁሌም ነበር ፉክክር።

አብይ ተነስቶ ባይሰብክ መደመርን፣
እርስበርስ ባለቅን እየተደማማን ።

ጠቅላይ አብይ መጥቶ ሰላም ፍቅር ባይል፣
ቤተመንግስት ነበር ያ ክፉ ሳጥናኤል።

ቦሌ ኤርፖርት ላይ እልልታው ቀለጠ፣
የ20 ዓመቱ ግርዶሽ ውጤቱ ጣፈጠ፣
የስዩምን እራስ እየበጠበጠ፣
የገብሩን ጨጓራ እየመላለጠ፣
የእውነቱ ሰዓት ይሀው አገጠጠ፣
የመለከቱ ድምጥ ጦቢያ ተደመጠ፣
አዲስ አበባ ላይ እውነት ተገለጠ።

የኤርትራ እንግዶች ቤተመንግስት ገቡ፣
ዝንቦቹ ሲወጡ መጣ መሰል ንቡ፣
በማለት ልገጥም ብዕሬን ባነሳ፣
አብይ-ሰው ተው አለኝ ቂምበቀልን እርሳ፣
እኔስ ለአብይ ስል ሁሉን እረሳለሁ፣
ቅንነት ደግነት በውስጡ ስላየሁ።

የአበባ ጉንጉን አንገት ላይ ቢደረግ፣
ሙዚቀኛው ሁሉ ወጥቶ ቢውረገረግ፣
ቄሱም ሆኑ ሼኩ ቢደረደር በረድፍ፣
ጸሐፊው ከያኒው አትሌቱ ቢሰለፍ፣
እስከዛሬ ምነው ያላዩት ያንን ግፍ፣
እንዲያውም አብሶ ያሉት ዘራፍ ዘራፍ፣
ቀን እንጂ ቃል ግና ፍጹም እንደማያልፍ፣
ዘንግተው እንዲሁ ይልቅ ከመለፍለፍ፣
“ነውር ነው!” ያላሉ እየከፈቱ አፍ፣
ዝም ብለውስ ያዩት ያይናቸውን ጉድፍ፣
ይህን ዝባዝንኬ የሚያደርስ ከምዕራፍ፣
አንድ አብይ ተገኘ ጉድፍ የሚያራግፍ፣
ብርሃን ሚፈነጥቅ ጨለማን የሚገፍ፣
ውሸትን አውግዞ እውነት የሚለፍፍ።

ይህ የድንበር ብይን ካልተተገበረ፣
ኤርትራዊ ሁሉ እንደተጭበረበረ፣
ዘላለም እንዳይኖር ቂም እንደቋጠረ፣
ቁርሾው እንዳይቀጥል እየተካረረ፣
በዛም በዚም ፍቱት ካለ የታሰረ፣
ፍርዱን ተግብሩና ማንም አልከሰረ።


ኩልዅም ዘይኾንኩም ገሌኹም ተጋሩ፣
እንታይ ዲኹም ኾንኩም ወትሩ ተዕገርግሩ፣
እስከ ውርዝይ በሉ ንሕጊ አተግብሩ፣
አብ ገዛእ ሃገርኩም ቀሲንኩም ክትነብሩ፣
ግብርኹም ሚዛንኩም ክትሓስሩ ክትከብሩ፣
ክሳብ መዓስ ደኣ ከተደናግሩ!
ቅንዕና ካብ አብይ እስከ ተመሃሩ፣
እንተከአልኩሞ ምስኡ ተደመሩ።

ለክፉም ለደጉ ይከተብ ታሪኩ፣
ሰይጣኑ እንዲለይ ይታወቅ መልአኩ፣
ጠንቅቀው እንዲያውቁት ትውልዶች ሲተኩ።
viewtopic.php?f=17&t=160263&sid=500291c ... 0e886f6aa9
ማዕቀብ እገዳ ካብ ተላዕለ ደጊም

ማዕቀብ እገዳ ካብ ተላዕለ ደጊም፣
ብፍቕሪ ብህድገት እስከ ንሰዓዓም፣
ቅርሕንቲ ኣወጊድና መብጽዓና ንዕመም፣
እቲ ሃሳዲና ይምላእ እቲ ዓይኑደም፣
ይቕረ ክንበሃሃል እስከ ንቀዳደም፣
ናብ ደገ ዘይኮነስ ናብ ሃገር ንሳግም።

ደቂ ኤሩሽኾር ዓቢ ምስ ንእሽቶ፣
ካብ ዓዲ እንዳማትና ናብ ዓድና ንእቶ፣
ባህ አይበሎ ሓሳድ ሕድሕድ ንፈታቶ።

እቶም ጸላእትና እቶም ዘይሓንኹ፣
ህዝቢ ዚጥብሩ ተንኮል ዚሕርንኹ፣
ብሰላሕታ ወራር እንተተንፈሐኹ፣
ፈንጠርጠር እንተበሉ ናብ ዓዲ ኪሶልኩ፣
ኣብ ዓዱ ኣሎ ጅግና ከውድቆም ሓሊኹ።

ትልዝብ ኣቢልና ተፋቂርና ሕድሕድ፣
ሓርነት ኣዊጅና ንእሱር ንቕዩድ፣
ሕጂውን ከምትማል ንሓዝ ነታ ክሳድ፣
ብፍቅሪ ሟሚቕናስ ብስኒት ንሰውድ፣
ጸላኢ ስምረትና ‘እንጦርጦስ’ ይውረድ።

ደቂሃላል መሬት ፈለማ እሞ ንስመር፣
ዶብና ተሐንጺጹ በወግዒ ይሰመር፣
ሽዑ ንምርምሮ ጉዳይ ናይ “መደመር”!

ካብ’ቲ ግርሕነትና’ስ ሕጂዃ ንመሃር!
ጉድ ከየምጽኡልና እቶም ታሕተዎት ሰፈር።


ኣስላማይ ክስታናይ ተጋዳላይ ገባር፣
ከምቲ መብጸዓና ሰሚርና ብሓባር፣
ሕድሪ ጀጋኑና ኣብ ሃገር ነተግብር፣
ዶብና እናስመርና ሕድሕድ ንጠማመር።

ህዝቢ ንመንግስቲ ጸኒዑ ዘጽነዐ፣
ሎቅመጽመጽ ከይበለ ብንዋይ ከይሰድዐ፣
ሳላ ዝተጸመመ ዘረባ ብድዐ፣
ሳላ እታ እምነቱ ንመትከል ዘይከድዐ፣
ልቦና ህዝብና ብሓቂ ተርነዐ፣
ኣብ ልዕሊ ክብሩ’ውን ክብሪ ተደረዐ።

ኢዋኡ በዳሊና እዝጊ ጸሊኡሉ፣
ወትሩ ናብሕስረቱ ኮሊሉ ኮሊሉ፣
ሳላ ጽንዓት ሕዝቢ ዝበደሀ ኩሉ፣
ፈጋግር ዞባና እቶም ተዃላሉ፣
ብመከተ ህዝቢ ምስ ተዐዃለሉ፣
እምነትን ጽንዓትን ካብ ልቢ ፈልፊሉ፣
ኣሎኹ ምስ በላ ንኤረይ ሓላሉ፣
ምስክር ኢዩ ኾይኑ ኩሉ ፈናቂሉ፣
ሓርበይናዊት ኣደ ደጊም ዓልልሉ።


ሳዕስዕሞ ሓዳርኻ ኣይትረስዕ!
ብዘይ ሃገር ክብረት የሎን!

15 Nov 2018, 02:33


almaze
Member+
Posts: 7665
Joined: 15 Dec 2013, 03:38

Re: የመደመር ትዝታዋች From Eritreans' perspectives.

Post by almaze » 12 Oct 2024, 19:44


almaze
Member+
Posts: 7665
Joined: 15 Dec 2013, 03:38

Re: የመደመር ትዝታዋች From Eritreans' perspectives.

Post by almaze » 12 Oct 2024, 20:42


almaze
Member+
Posts: 7665
Joined: 15 Dec 2013, 03:38

Re: የመደመር ትዝታዋች From Eritreans' perspectives.

Post by almaze » 15 Oct 2024, 20:42


almaze
Member+
Posts: 7665
Joined: 15 Dec 2013, 03:38

Re: የመደመር ትዝታዋች From Eritreans' perspectives.

Post by almaze » 16 Oct 2024, 17:59


almaze
Member+
Posts: 7665
Joined: 15 Dec 2013, 03:38

Re: የመደመር ትዝታዋች From Eritreans' perspectives.

Post by almaze » 19 Oct 2024, 18:32



almaze
Member+
Posts: 7665
Joined: 15 Dec 2013, 03:38

Re: የመደመር ትዝታዋች From Eritreans' perspectives.

Post by almaze » 29 Oct 2024, 20:43



Meleket
Member
Posts: 4614
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የመደመር ትዝታዋች From Eritreans' perspectives.

Post by Meleket » 05 Jun 2025, 08:43

እኛ የመደመር ግዜም “ድንበራችንን መሬቱ ላይ ኣስምሩ” በምንልበት ወቅት ኣንዳንዶች ደግሞ እንዲህ ይሉ ነበር!
( ͡° ͜ʖ ͡°) wrote:
17 Jan 2020, 01:48
ክቡር የኤርትራው ፕሬዚደንት ~ ወያኔን ስለጣልክልን እጅግ በጣም እናመሰግናለን።

ለማንኛዉም ከጥቂት ግዜ በኋላ ‘ጽምዶም’ መዘባበቻ እንዳይሆን፡ ቁምነገር ስሩበት፡ ኣዎን ድንበራችንን መሬት ላይ ወርዳችሁ ምልክት ኣድርጉበት፡ ለዓመታትና ለዘመናት ሰላም የተነፈጋቸው የድንበር ላይ ህዝቦቻችን ሰላምን እንዲጎናጸፉ ይሁን!

ለፈገግታ ያህል ኣንድ ጥያቄ እንጠይቅ፡ ፎቶሾፑ ላይ እንደሚነበበው "ህዝባዊ ወያነ ትግራይ" ወደ 'ድንጋይ' ተመልሷልን?
:mrgreen:

Axumezana
Senior Member
Posts: 17460
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የመደመር ትዝታዋች From Eritreans' perspectives.

Post by Axumezana » 05 Jun 2025, 19:32

Axumezana contributed on the destruction of መደመር with this!


[/quote]

Meleket
Member
Posts: 4614
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የመደመር ትዝታዋች From Eritreans' perspectives.

Post by Meleket » 07 Jun 2025, 02:23

ወዳጃችን ኣዅሱመጫላ መቼም ይህንን ካርታ ስታዘጋጅ የኣኵሱም የደብረኣባይ እንዲሁም የማኅበረ ዴጎ ‘ሊቃዉንት’ ድጋፍ ኣድርገውልህ እንደሆነ እንጠረጥራለን፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
Axumezana wrote:
05 Jun 2025, 19:32
Axumezana contributed on the destruction of መደመር with this!

( ͡° ͜ʖ ͡°) wrote:
17 Jan 2020, 01:48
ክቡር የኤርትራው ፕሬዚደንት ~ ወያኔን ስለጣልክልን እጅግ በጣም እናመሰግናለን።
...
ለማንኛዉም ከጥቂት ግዜ በኋላ ‘ጽምዶም’ መዘባበቻ እንዳይሆን፡ ቁምነገር ስሩበት፡ ኣዎን ድንበራችንን መሬት ላይ ወርዳችሁ ምልክት ኣድርጉበት፡ ለዓመታትና ለዘመናት ሰላም የተነፈጋቸው የድንበር ላይ ህዝቦቻችን ሰላምን እንዲጎናጸፉ ይሁን!

ለፈገግታ ያህል ኣንድ ጥያቄ እንጠይቅ፡ ፎቶሾፑ ላይ እንደሚነበበው "ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ" ወደ 'ድንጋይ' ተመልሷልን?
:mrgreen:

Post Reply