Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40425
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ ኦሮሞ አገዛዝ ኢትዮጵያን አንድ ሳያደርግ ስልጣን ላይ መቆየትም ሆነ በዲፕሎማሲ አንድ እርምጃ ፈቀቅ ማለት አይችልም! ይህ ሳይንስ ነው!

Post by Horus » 25 Feb 2024, 00:33

selam,
የኢትዮጵያ ጥቅም አቢይ ተሳሳተ አልተሳሳተ አይለወጥም። ነገ አንተ መንግስት ብትሆን ይህ ያንተ ችግር ነው የሚሆነው። አቢይ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን እጅግ በጣም የምንፈልገው ነገር ነው ። መንግስት የሚወድቀው እንደዚያ ነው ። ያ ማለት ነገ ሕዝብ የሚደግፈው መንግስት ቢመጣ እንኳ የወደብና የብሄራዊ መከላከያ ችግር ቁጥር 1 ችግሩ ነው ። ስለዚህ ኢትዮጵያ ደካማ አገር እንድትሆን ከሚመኙ አብሮ አቢይን መምታት ስህተት ነው። የግዥ መደብን ከስልጣን ማባረድ አንድ ነገር ነው ። የገዥ መደብን ለማዳከም ኢትዮጵያን እስትራተጂካሊ ማዳከም ግዙፍ የመሪነት ስህተት ነው ። የኦሮሙማ ችግር ውስጥ መግባት በጣም ጥሩ ነው ፤ ያኔ ነው ወይ የሚለወጡት ወይም የሚወድቁት ። የሚሆነውም ይህ ነው ። ግን ግብጽና ሱማሌ የሚያደራጁት ኢትዮጵያን መክበብ አቢይን ሳይሆን ኢትዮጵያን ነው ከበው እያዳከሙን ያለው። ሳይንሱ ይህ ነው ።

Post Reply