Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15358
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አበረ፥ ባንዳነትን፥ እንዳቀነቀነ፥ ልደተ፥ ክርስቶስ፥ መድረሱ፥ ነው።

Post by Abere » 24 Dec 2023, 19:01

ሰላምን ለማውረድ - ቀላል ነው መንገዱ፤
የዜጋ ቄራዎች የጎሳ ክልሎች በዐዋጅ ይታገዱ፤

ስለ ዐብይ ዘመን ማን ነው ሜትሪዎሎጅው?
ፋና ነው EBC ወይስ ትግቲቪ - ይህንን ያወጀው?
30 ዓመት ዋሹን አሁንስ በቃቸው!

ግርማዊነታቸ ሜትሮሎጅ አቁመው - ደመወዝ ሲከፍሉ፤
ከሚዎን ሲነዱ ሞገስ ተጎናጽፈው፤
ጆሮዋን ቀስራ ስትከንፍ አህያ አይተው ተመልክተው፤
አቁም መኪናየን ተመልከት ዋሪድትን ነጎድጓድ ሊመጣ ነው፥
ነገሩን ካፋቸው ወዲያ ሳይጨርሱ፥
ሁላቸው በአንድ ላይ በዝናብ እራሱ፥
የሚትሮሎጅ ነገር ቅጥፈት እራት ቁርሱ።

የዛሬን ዕጣውን ቢያውቅ እኮ ወያኔ፤
ማይ ካዲራ ሰሜን ዕዝ አይሞክርም ያኔ።

የአብይ አህመድ ዘመን ቀኑ የደረሰ፥
ጉድ ጓዱ የተማሰ ልጡ የራሰ፤
መምሬ ወይ ሼሁ ይቀብረዋል እንጅ ፈጥኖ የደረሰ።

ወይ አክሱምወኢዛና - እኔ ምኔን ልርዳህ?
የሞተ ወያኔን ቆፍሬ አላወጣው አውጥቼ አላሳይህ።
ቆርጦ የጣለውን ፈጣሪ በክፋቱ፤
ከየት ይገኝ ወይን መልፋት ነው በከንቱ።

ትናንት ላይ ቁመህ ሙታን ወያኔን ያለ አስመስለህ፤
እንድሁ በሜዳ አሻንጉሊት ይዘህ በሞተ ህልም አለም ከንቱ ትጽናናለህ።

አክሱም እርምህን አውጣ፤ አቁም ማልቀስህን፤
ይቅርብህ! ይቅርብህ! ይኸ ሞኝነትህ።

እኔም እልህ አለሁ -እግዜር እርሱ ያጥናህ ፤
ፋኖ ጌታህ ሁኖ ከጥፋት አስጥሎ -ለንስሃ ያብቃህ።

Post Reply