-
Sam Ebalalehu
- Member
- Posts: 3639
- Joined: 23 Jun 2018, 21:29
Re: አገኘሁ ተሻገር የሚባል ሹል - የወያኔ ዕጢ
እንደ መለሰ አረዳድ " ፌዴራሊዝም" ማለት የኢትዮጵያ ህገመንግስት ኢትዮጵያን ለመበታተን የተነደፈ ስልት ነው። ይህንን " ቅዱስ" አሳብ ,Eden , ያለምንም እፉረት ለ ኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አጫውቶታል። ይህን ላስታውስሽ የፈለኩት ትግራይ ለኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ፌደራሊዝምን የቸረ ነው የሚለው መፈክርሽ ላይ እርምት እንድታረጊ ነው። መለሰ እንዳሰበው ከመላ ጎደል ሆኖለታል። ዛሪ በአለም ላይ ያለማቋረጥ አንድ ዜጋ ሌላውን ዜጋ በብሄር ልዩነት ብቻ የሚገድልበት አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ዛሪ በአለም ላይ ፓለቲከኞች , የ ሚዲያ ሰዎች , የ ሀይማኖት ሰዎች በአጠቃላይ ድፍን ኢትዮጵያ በብሄር ሲወነጃጀል የሚኖርባት አገር ኢትዮጵያ ብቻ ነች። እስካሁን አልፈረሰችም። የአብዛኛው የ መለሰ እና ጎዶቹ አላማ ግን እየተሳካ ነው።