Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member+
Posts: 5087
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: Ancient City of Adulis

Post by Meleket » 26 Apr 2022, 03:33

“መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ” የሚሉት የሃበሻ ፈላስፎች “ስምን መልአክ ያወጣዋል” እንዲሉ፡ የሃዳሯ ቆንጂትን ተመራማሪዎቹ “ሉሲ” ማለትም “ብርሃኗ” ብለው ስም ሲያወጡላት እንዲሁ በዘፈቀደ የተሰጣት ስም ሳይሆን፡ ኣምላክ በጥበቡ ያጎናጸፋት ስም መሆኑ ይገባናል። :mrgreen:

ኣደ ሉሲ ማለትም ከግዜ ብዛት ተቆልምሞ አዱሊስ ቢባልም፡ ትርጉሙ ‘የሉሲ ኣናት ማለት የብርሃን እናት’ እንደማለት መሆኑን ከቁምነገር አዘሉ ቀልድ አጢነናል። የብርሃን እናት ላይ ከደረስን ሌላዉን ፈላስፎች ተፈላሰፉበት። መቸም ጉደኛዋ ሃገራችን ኤርትራ፡ እዛው ከአዱሊስ ብዙም ሳይርቅ “እም ኩሉ” የሚባል ታሪካዊ ቀዬም ኣላት፡ “የሁሉ እናት” እንደማለት ነው በግዕዙና በትግርኛው ጥምረት ሲተረተርና ሲተነተን። ታዲያ “የሁሉ እናት” እንዲሁም “የብርሃን እናት” እያሉ ነበር ስም የሚያወጡት የኛ ቀደምቶች። እዛው አዱሊስ አካባቢ ቀደምቶቻችን “ገደም” ብለውም ስም ያወጡለት ተራራም ኣለ ፡ ገዲም ማለት ራሱ ቃሉ ቀደምት ማለት ነው ትርጉሙ፤ ጥንት ያኔ ተራራው ገዳም ሆኖ አገልግሎም ሊሆን ይችላል። መቼም የታሪካዊዋን የእምበረሚን ታሪክ እዚህ ላይ ገልጠንላችሁ ነበር። https://mereja.com/forum/viewtopic.php? ... A#p1096664

ያለ ባለቤቱ አይነድም እሳቱ” እንዲሉ፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ አዱሊስን፣ ዙላን፣ አብዱርን፣ ቦያን፣ እምኵሉን ገደምንና እምበረሚን አስጎበኘናችሁ አይደል:mrgreen: መጪውን የዒድ በዓል ምክንያት አድርገንም ‘የሰሃባዎች መስጊድ’ ማለትም የነብዩ መሓመድ ቀደምት ተከታዮች በስደት ቀይባህርን በተሻገሩ ወቅት ሰርተውታል የሚባለውን በአፍሪካ ምድር አንዳንዶች እንደሚሉትም ከዓለምም ጭምር የመጀመሪያው መስጊድንም በምናብ እናስጎበኘናችኋን። ሌላ ግዜ የሃገራችንና የሃገራችሁ ድንበር በቅጡ ሲሰመርና ሲካለል ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በአካል ያስጎበኟችኋል። እስከዚያው በኤርትራዊ ጭዋነትና ኩራት እንዲሁም ትህትናም ጭምር መልካም መልካሙን ሁሉ እንመኘላችኋለን፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች
:mrgreen:

Post Reply